Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዮሐንስ 21:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ከሙ​ታን ተለ​ይቶ ከተ​ነሣ በኋላ ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሲገ​ለ​ጥ​ላ​ቸው ይህ ሦስ​ተኛ ጊዜዉ ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እንግዲህ ኢየሱስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ ሲታይ ይህ ለሦስተኛ ጊዜ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ኢየሱስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ ሲገለጥላቸው ይህ ሦስተኛው ጊዜ ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ኢየሱስ ከሞት ከተነሣ ወዲህ ደቀ መዛሙርቱ ሲያዩት ይህ ሦስተኛ ጊዜ ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ኢየሱስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ ሲገለጥላቸው ይህ ሦስተኛው ጊዜ ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de




ዮሐንስ 21:14
6 Referências Cruzadas  

ከዚህም በኋላ ከእነርሱ ለሁለቱ ወደ ባላገር ሲሄዱ በመንገድ በሌላ መልክ ተገለጠ፤


ኋላም በማዕድ ተቀምጠው ሳሉ ለዐሥራ አንዱ ተገለጠ፤ ተነሥቶም ያዩትን ስላላመኑአቸው አለማመናቸውንና የልባቸውን ጥንካሬ ነቀፈ።


ያም ከሳ​ም​ንቱ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን በመሸ ጊዜ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ አይ​ሁ​ድን ስለ ፈሩ ተሰ​ብ​ስ​በው የነ​በ​ሩ​በት ቤት ደጁ ተቈ​ልፎ ሳለ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መጥቶ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ቆመና፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን” አላ​ቸው።


ከስ​ም​ንት ቀን በኋ​ላም ዳግ​መኛ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ በው​ስጡ ሳሉ፥ ቶማ​ስም አብ​ሮ​አ​ቸው ሳለ በሩ እንደ ተዘጋ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መጣ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ቆመና፥ “ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን” አላ​ቸው።


ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በጥ​ብ​ር​ያ​ዶስ ባሕር አጠ​ገብ ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ እን​ደ​ገና ተገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም ተገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው።


ሕማ​ማ​ትን ከተ​ቀ​በለ በኋላ ብዙ ተአ​ም​ራት በማ​ሳ​የት አርባ ቀን ሙሉ እየ​ተ​ገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው፥ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥ​ትም እየ​ነ​ገ​ራ​ቸ​ውና እያ​ስ​ተ​ማ​ራ​ቸው ሕያው ሆኖ ራሱ​ን​ገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios