Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዮሐንስ 19:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ደግ​ሞም ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ ገባና ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን፥ “አንተ ከወ​ዴት ነህ?” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ግን ምንም አል​መ​ለ​ሰ​ለ​ትም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ወደ ግቢው ተመልሶ ኢየሱስን፣ “ከየት ነው የመጣኸው?” በማለት ጠየቀው፤ ኢየሱስ ግን ምንም አልመለሰለትም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ተመልሶም ወደ ገዢው ግቢ ገባና ኢየሱስን “አንተ ከየት ነህ?” አለው። ኢየሱስ ግን ምንም መልስ አልሰጠውም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ወደ ግቢው ገባና ኢየሱስን “አንተ ከየት ነህ?” ሲል ጠየቀው። ኢየሱስ ግን ምንም አልመለሰለትም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ተመልሶም ወደ ገዡ ግቢ ገባና ኢየሱስን፦ “አንተ ከወዴት ነህ?” አለው። ኢየሱስ ግን አንድ እንኳ አልመለሰለትም።

Ver Capítulo Cópia de




ዮሐንስ 19:9
18 Referências Cruzadas  

እርሱ ግን በመ​ከ​ራው ጊዜ አፉን አል​ከ​ፈ​ተም፤ እንደ በግ ወደ መታ​ረድ ተነዳ፤ የበግ ጠቦ​ትም በሸ​ላ​ቾቹ ፊት ዝም እን​ደ​ሚል፥ እን​ዲሁ አፉን አል​ከ​ፈ​ተም።


ኢየሱስ ግን ዝም አለ። ሊቀ ካህናቱም “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ የሆንህ እንደ ሆነ እንድትነግረን በሕያው እግዚአብሔር አምልሃለሁ፤” አለው።


በዚያን ጊዜ የገዢው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ ገዢው ግቢ ውስጥ ወሰዱት፤ ጭፍራውንም ሁሉ ወደ እርሱ አከማቹ።


በብዙ ነገ​ርም መረ​መ​ረው፤ እርሱ ግን አን​ድስ እንኳ አል​መ​ለ​ሰ​ለ​ትም።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ከቀ​ያፋ ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ ወሰ​ዱት፤ አይ​ሁድ ግን ፈጽሞ ስለ ነጋ የፋ​ሲ​ካ​ውን በግ ሳይ​በሉ እን​ዳ​ይ​ረ​ክሱ ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ አል​ገ​ቡም።


ጲላ​ጦ​ስም እን​ደ​ገና ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ ገብቶ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ጠራና፥ “የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ አንተ ነህን?” አለው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ይህን የም​ት​ና​ገር ከራ​ስህ ነውን? ወይስ ስለ እኔ የነ​ገ​ረህ ሌላ አለን?” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


ጲላ​ጦ​ስም፥ “እን​ግ​ዲያ አንተ ንጉሥ ነህን?” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ራስህ ትላ​ለህ፤ እኔ ስለ​ዚህ ተወ​ለ​ድሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ለእ​ው​ነት ልመ​ሰ​ክር ወደ ዓለም መጣሁ፤ ከእ​ው​ነት የሆነ ሁሉ ቃሌን ይሰ​ማ​ኛል” አለው።


ጲላ​ጦ​ስም፥ “ለእ​ኔም አት​ነ​ግ​ረ​ኝ​ምን? ልሰ​ቅ​ልህ ሥል​ጣን እንደ አለኝ፥ ወይም ልፈ​ታህ ሥል​ጣን እን​ዳ​ለኝ፥ አታ​ው​ቅ​ምን?” አለው።


ጲላ​ጦ​ስም ይህን ነገር ሰምቶ እጅግ ፈራ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ ስለ​ራሴ ብመ​ሰ​ክ​ርም ምስ​ክ​ር​ነቴ እው​ነት ነው፤ ከየት እን​ደ​መ​ጣሁ፥ ወዴት እን​ደ​ም​ሄ​ድም አው​ቃ​ለ​ሁና፤ እና​ንተ ግን ከየት እንደ መጣሁ ወዴት እን​ደ​ም​ሄ​ድም አታ​ው​ቁም።


የእ​ነ​ርሱ ጥፋት፥ የእ​ና​ን​ተም ሕይ​ወት ይታ​ወቅ ዘንድ የሚ​ቃ​ወ​ሙን ሰዎች በማ​ና​ቸ​ውም አያ​ስ​ደ​ን​ግ​ጧ​ችሁ።


ሴቲ​ቱም ወደ ባልዋ መጥታ፥ “አንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፤ መል​ኩም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ እጅግ የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግጥ ነበረ፤ ከወ​ዴ​ትም እንደ መጣ ጠየ​ቅ​ሁት፥ እር​ሱም ስሙን አል​ነ​ገ​ረ​ኝም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios