Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዮሐንስ 19:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እና​ቱ​ንና የሚ​ወ​ደ​ውን ደቀ መዝ​ሙ​ሩን ቆመው ባያ​ቸው ጊዜ እና​ቱን፥ “አንች ሆይ፥ እነሆ፥ ልጅሽ” አላት።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በዚያም ኢየሱስ እናቱንና የሚወድደውም ደቀ መዝሙር አጠገቧ ቆሞ ሲያያቸው እናቱን፣ “አንቺ ሴት ሆይ፤ ልጅሽ ይኸው” አላት፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ኢየሱስም እናቱንና ይወደው የነበረውንም ደቀመዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን “አንቺ ሴት ሆይ! እነሆ ልጅሽ” አላት።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ኢየሱስ እናቱንና የሚወደውን ደቀ መዝሙር አጠገቡ ቆመው ባያቸው ጊዜ፥ እናቱን “እናቴ ሆይ! እነሆ፥ ልጅሽ!” አላት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን፦ “አንቺ ሴት፥ እነሆ ልጅሽ” አላት።

Ver Capítulo Cópia de




ዮሐንስ 19:26
6 Referências Cruzadas  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይወ​ደው የነ​በረ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ አንዱ በጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ አጠ​ገብ ተቀ​ምጦ ነበር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አንቺ ሆይ ካንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አል​ደ​ረ​ሰም” አላት።


ፈጥ​ናም ወደ ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስና ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ይወ​ደው ወደ ነበ​ረው ወደ​ዚያ ወደ ሌላዉ ደቀ መዝ​ሙር መጥታ፥ “ጌታ​ዬን ከመ​ቃ​ብር ወስ​ደ​ው​ታል፤ ወዴ​ትም እንደ ወሰ​ዱት አላ​ው​ቅም” አለ​ቻ​ቸው።


ጴጥ​ሮ​ስም መለስ ብሎ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ይወ​ደው የነ​በ​ረ​ውን ያን ደቀ መዝ​ሙር ሲከ​ተ​ለው አየ፤ እር​ሱም ራት ሲበሉ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ አጠ​ገብ የነ​በ​ረ​ውና “ጌታ ሆይ፥ አሳ​ልፎ የሚ​ሰ​ጥህ ማነው?” ያለው ነው።


ስለ​ዚህ ነገር ምስ​ክር የሆነ፥ ስለ እር​ሱም ይህን የጻፈ ይህ ደቀ መዝ​ሙር ነው፤ ምስ​ክ​ር​ነ​ቱም እው​ነት እንደ ሆነ እኛ እና​ው​ቃ​ለን።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ይወ​ደው የነ​በረ ያ ደቀ መዝ​ሙ​ርም ለጴ​ጥ​ሮስ፥ “ጌታ​ችን ነው እኮ” አለው፤ ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ጌታ​ችን እንደ ሆነ በሰማ ጊዜ የሚ​ለ​ብ​ሰ​ውን ልብስ አን​ሥቶ በወ​ገቡ ታጠቀ፤ ራቁ​ቱን ነበ​ርና ወደ ባሕር ተወ​ረ​ወረ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios