Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዮሐንስ 18:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የእኔ መን​ግ​ሥት ከዚህ ዓለም አይ​ደ​ለ​ችም፤ መን​ግ​ሥ​ቴስ በዚህ ዓለም ብት​ሆን ኖሮ ለአ​ይ​ሁድ እን​ዳ​ል​ሰጥ አሽ​ከ​ሮች በተ​ዋ​ጉ​ልኝ ነበር፤ አሁ​ንም መን​ግ​ሥቴ ከዚህ አይ​ደ​ለ​ችም” ብሎ መለ​ሰ​ለት።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ኢየሱስም፣ “የእኔ መንግሥት ከዚህ ዓለም አይደለም፤ ቢሆንማ ኖሮ አይሁድ እንዳይዙኝ አገልጋዮቼ በተከላከሉልኝ ነበር፤ አሁን ግን መንግሥቴ ከዚህ አይደለም” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ኢየሱስም መልሶ “መንግሥቴ ከዚህ ዓለም አይደለችም፤ መንግሥቴ ከዚህ ዓለም ብትሆን ኖሮ፥ ወደ አይሁድ እንዳልሰጥ ሎሌዎቼ ይዋጉልኝ ነበር፤ ነገር ግን መንግሥቴ ከዚህ አይደለችም” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ኢየሱስ “የእኔ መንግሥት ከዚህ ዓለም አይደለችም፤ መንግሥቴ ከዚህ ዓለም ብትሆን ኖሮ በአይሁድ ባለሥልጣኖች እጅ እንዳልወድቅ ሎሌዎቼ በተዋጉልኝ ነበር፤ መንግሥቴ ግን ከዚህ ዓለም አይደለችም” ሲል መለሰ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ኢየሱስም መልሶ፦ “መንግሥቴ ከዚህ ዓለም አይደለችም፤ መንግሥቴስ ከዚህ ዓለም ብትሆን፥ ወደ አይሁድ እንዳልሰጥ ሎሌዎቼ ይዋጉልኝ ነበር፤ አሁን ግን መንግሥቴ ከዚህ አይደለችም” አለው።

Ver Capítulo Cópia de




ዮሐንስ 18:36
14 Referências Cruzadas  

አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፣ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፣ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፣ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫንይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።


ወይስ አባቴን እንድለምን እርሱም አሁን ከዐሥራ ሁለት ጭፍሮች የሚበዙ መላእክት እንዲሰድልኝ የማይችል ይመስልሃልን?


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አንተ ሰው፥ በእ​ና​ንተ ላይ አካ​ፋ​ይና ዳኛ አድ​ርጎ ማን ሾመኝ?” አለው።


ጲላ​ጦ​ስም መልሶ፥ “እኔ አይ​ሁ​ዳዊ ነኝን? ለእኔ አሳ​ል​ፈው የሰ​ጡህ ወገ​ኖ​ች​ህና ሊቃነ ካህ​ናት አይ​ደ​ሉ​ምን? Aረ ምን አድ​ር​ገ​ሃል?” አለው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መጥ​ተው ነጥ​ቀው ሊያ​ነ​ግ​ሡት እን​ደ​ሚሹ ዐወ​ቀ​ባ​ቸ​ውና ብቻ​ውን ወደ ተራራ ሄደ።


እና​ንተ ሥጋዊ ፍር​ድን ትፈ​ር​ዳ​ላ​ችሁ፤ እኔ ግን በማ​ንም አል​ፈ​ር​ድም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ጽድ​ቅና ሰላም፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም የሆነ ደስታ ነው እንጂ መብ​ልና መጠጥ አይ​ደ​ለ​ምና።


ሁሉን በሕይወት በሚጠብቅ በእግዚአብሔር ፊት፥ በጴንጤናዊውም በጲላጦስ ዘንድ መልካሙን መታመን በመሰከረ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት አዝሃለሁ፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios