Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዮሐንስ 17:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 አሁን ግን ወደ አንተ እመ​ጣ​ለሁ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ደስ​ታዬ ፍጹም ይሆን ዘንድ ይህን በዓ​ለም እና​ገ​ራ​ለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “አሁን ወደ አንተ መምጣቴ ነው፤ ነገር ግን ደስታዬ በእነርሱ ዘንድ የተሟላ እንዲሆን፣ አሁን በዓለም እያለሁ ይህን እናገራለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 አሁንም ወደ አንተ እመጣለሁ፤ በእነርሱም ዘንድ ደስታዬ የተፈጸመ እንዲሆንላቸው ይህን በዓለም እናገራለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 አሁን እኔ ወደ አንተ መምጣቴ ነው፤ በዓለም ላይ ሳለሁ ይህን የምናገረው ደስታዬ በእነርሱ ዘንድ ፍጹም እንዲሆን ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 አሁንም ወደ አንተ እመጣለሁ፤ በእነርሱም ዘንድ ደስታዬ የተፈጸመ እንዲሆንላቸው ይህን በዓለም እናገራለሁ።

Ver Capítulo Cópia de




ዮሐንስ 17:13
17 Referências Cruzadas  

እር​ሱም፥ “ሂዱ፤ የሰ​ባ​ው​ንም ብሉ፤ ጣፋ​ጩ​ንም ጠጡ፤ ለእ​ነ​ዚ​ያም ምንም ለሌ​ላ​ቸው እድል ፈን​ታ​ቸ​ውን ላኩ፤ ዛሬ ለጌ​ታ​ችን የተ​ቀ​ደሰ ቀን ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀይ​ላ​ችን ነውና አት​ዘኑ” አላ​ቸው።


ከእ​ነ​ርሱ ዘንድ ምኞ​ቱን የሚ​ፈ​ጽም ሰው ብፁዕ ነው፤ ጠላ​ቶ​ቹን በአ​ደ​ባ​ባይ በተ​ና​ገረ ጊዜ እርሱ አያ​ፍ​ርም።


አም​ላ​ኬና ንጉሤ አንተ ነህ፤ ለያ​ዕ​ቆብ መድ​ኀ​ኒ​ትን ያዘ​ዝህ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ወጣ፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ደ​ሚ​ሄድ ባወቀ ጊዜ፥


ደስ​ታዬ በእ​ና​ንተ ይኖር ዘንድ፥ ደስ​ታ​ች​ሁም ፍጹም ይሆን ዘንድ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ።


በእ​ኔም ሰላ​ምን እን​ድ​ታ​ገኙ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ፤ በዓ​ለም ግን መከ​ራን ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን ጽኑ፤ እኔ ዓለ​ሙን ድል ነሥ​ቼ​ዋ​ለ​ሁና።”


እን​ግ​ዲህ በዓ​ለም አል​ኖ​ርም፤ እነ​ርሱ ግን በዓ​ለም ይኖ​ራሉ፤ እኔም ወደ አንተ እመ​ጣ​ለሁ፤ ቅዱስ አባት ሆይ፥ እነ​ዚ​ህን የሰ​ጠ​ኸ​ኝን እንደ እኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ በስ​ምህ ጠብ​ቃ​ቸው፤


ሙሽራ ያለ​ችው ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚ​ሰ​ማው የሙ​ሽ​ራው ሚዜ ግን በሙ​ሽ​ራው ቃል እጅግ ደስ ይለ​ዋል፤ የእኔ ደስታ አሁን ተፈ​ጸ​መች።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ጥቂት ቀን አብ​ሬ​አ​ችሁ እኖ​ራ​ለሁ፤ ከዚ​ህም በኋላ ወደ ላከኝ እሄ​ዳ​ለሁ።


መን​ፈስ ቅዱ​ስም በደቀ መዛ​ሙ​ርት ላይ ሞላ፤ ደስም አላ​ቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ጽድ​ቅና ሰላም፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም የሆነ ደስታ ነው እንጂ መብ​ልና መጠጥ አይ​ደ​ለ​ምና።


የመ​ን​ፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕ​ግ​ሥት፥ ምጽ​ዋት፥ ቸር​ነት፥ እም​ነት፥ ገር​ነት፥ ንጽ​ሕና ነው።


የእ​ም​ነ​ታ​ች​ን​ንም ራስና ፈጻ​ሚ​ውን ኢየ​ሱ​ስን እን​ከ​ተ​ለው፤ እርሱ ነው​ርን ንቆ፥ በፊ​ቱም ስላ​ለው ደስታ በመ​ስ​ቀል ታግሦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዙፋን ቀኝ ተቀ​ም​ጦ​አ​ልና።


ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን እንጽፍላችኋለን።


እንድጽፍላችሁ የምፈልገው ብዙ ነገር ሳለኝ በወረቀትና በቀለም ልጽፈው አልወድም፤ ዳሩ ግን ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ወደ እናንተ ልመጣ አፍ ለአፍም ልናገራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios