Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዮሐንስ 16:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ያን​ጊ​ዜም እኔን የም​ት​ለ​ም​ኑኝ አን​ዳች የለም፤ እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በስሜ አብን ብት​ለ​ም​ኑት ሁሉን ይሰ​ጣ​ች​ኋል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 በዚያ ቀን ከእኔ ምንም አትለምኑም፤ እውነት እላችኋለሁ፤ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 በዚያን ቀንም ከእኔ ምንም ነገር አትለምኑም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 “በዚያን ቀን ከእኔ ምንም አትለምኑም፤ እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ አብን በስሜ ብትለምኑት ሁሉን ነገር ይሰጣችኋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 በዚያን ቀንም ከእኔ አንዳች አትለምኑም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል።

Ver Capítulo Cópia de




ዮሐንስ 16:23
22 Referências Cruzadas  

“እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ሳይ​ጠሩ እመ​ል​ስ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ገናም ሲና​ገሩ እነሆ፥ አለሁ እላ​ቸ​ዋ​ለሁ።


አምናችሁም በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ፤” አላቸው።


“ለምኑ፤ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፤ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፤ ይከፈትላችሁማል።


እኔ በአብ እን​ዳ​ለሁ፥ አብም በእኔ እን​ዳለ፥ እና​ን​ተም በእኔ፥ እኔም በእ​ና​ንተ እን​ዳ​ለሁ ያን​ጊዜ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


የአ​ስ​ቆ​ሮቱ ሰው ያይ​ደለ ይሁ​ዳም፥ “ጌታ ሆይ፥ ለዓ​ለም ያይ​ደለ ለእኛ ራስ​ህን ትገ​ልጥ ዘንድ እን​ዳ​ለህ የተ​ና​ገ​ር​ኸው ምን​ድን ነው?” አለው።


ቶማ​ስም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ የም​ት​ሄ​ድ​በ​ትን የማ​ና​ውቅ እን​ግ​ዲህ መን​ገ​ዱን እን​ዴት እና​ው​ቃ​ለን?” አለው።


በእ​ኔም ብት​ኖሩ ቃሌም በእ​ና​ንተ ቢኖር የም​ት​ሹ​ትን ሁሉ ትለ​ም​ና​ላ​ችሁ፤ ይደ​ረ​ግ​ላ​ች​ሁ​ማል።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ሊጠ​ይ​ቁት እን​ደ​ሚሹ ዐውቆ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ጥቂት ጊዜ አለ፤ አታ​ዩ​ኝ​ምም፤ ደግ​ሞም ጥቂት ጊዜ አለ፤ እን​ደ​ገ​ናም ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ” ስለ አል​ኋ​ችሁ፥ ስለ​ዚህ ነገር እርስ በር​ሳ​ችሁ ትመ​ራ​መ​ራ​ላ​ች​ሁን?


ያን​ጊዜ በስሜ ትለ​ም​ና​ላ​ችሁ፤ እኔም ስለ እና​ንተ አብን እለ​ም​ነ​ዋ​ለህ አል​ላ​ች​ሁም፤


አሁን አንተ ሁሉን እን​ደ​ም​ታ​ውቅ፥ ማንም ሊነ​ግ​ርህ እን​ደ​ማ​ትሻ ዐወ​ቅን፤ በዚ​ህም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ወጣህ እና​ም​ና​ለን።”


እርሱ መር​ቶ​ና​ልና፤ ሁለ​ታ​ች​ን​ንም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ወደ አባቱ አቅ​ር​ቦ​ና​ልና።


ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios