Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ዮሐንስ 12:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ነፍ​ሱን የሚ​ወ​ዳት ይጥ​ላ​ታል፤ በዚህ ዓለም ነፍ​ሱን የሚ​ጥ​ላ​ትም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ይጠ​ብ​ቃ​ታል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ነፍሱን የሚወድድ ያጣታል፤ በዚህ ዓለም ነፍሱን የሚጠላ ግን ለዘላለም ሕይወት ይጠብቃታል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ነፍሱን የሚወድ ያጠፋታል፤ ነፍሱንም በዚህ ዓለም የሚጠላ ለዘለዓለም ሕይወት ይጠብቃታል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ሕይወቱን የሚወድ ያጠፋታል፤ በዚህ ዓለም ሕይወቱን የሚጠላ ግን ለዘለዓለም ሕይወት ይጠብቃታል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ነፍሱን የሚወድ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም በዚህ ዓለም የሚጠላ ለዘላለም ሕይወት ይጠብቃታል።

Ver Capítulo Cópia de




ዮሐንስ 12:25
13 Referências Cruzadas  

ከፀ​ሐ​ይም በታች የተ​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ በእኔ ላይ ክፉ ነውና ሕይ​ወ​ትን ጠላሁ፥ ሁሉም ከንቱ፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


ነፍሱን የሚያገኝ ያጠፋታል፤ ነፍሱንም ስለ እኔ የሚያጠፋ ያገኛታል።


ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል።


ስለ ስሜም ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል፤ የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል።


ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታልና፤ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን ያድናታል።


“ወደ እኔ የሚ​መጣ፥ ሊከ​ተ​ለ​ኝም የሚ​ወድ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን፥ ሚስ​ቱ​ንና ልጆ​ቹን፥ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንና እኅ​ቶ​ቹን፥ የራ​ሱ​ንም ሰው​ነት እንኳ ቢሆን የማ​ይ​ጠላ ደቀ መዝ​ሙሬ ሊሆን አይ​ች​ልም።


ነፍ​ሱን ሊያ​ድ​ናት የሚ​ወድ ይጣ​ላት፤ ስለ እኔ ነፍ​ሱን የሚ​ጥ​ላ​ትም ያድ​ና​ታል።


ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የጸ​ጋ​ውን ወን​ጌል እን​ዳ​ስ​ተ​ምር ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የተ​ቀ​በ​ል​ሁ​ትን ሩጫ​ዬን እን​ድ​ጨ​ር​ስና መል​እ​ክ​ቴ​ንም እን​ድ​ፈ​ጽም ነው እንጂ ለሰ​ው​ነቴ ምንም አላ​ስ​ብ​ላ​ትም።


ጳው​ሎስ ግን መልሶ፥ “ለምን እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ? እያ​ለ​ቀ​ሳ​ችሁ ልቤን ትሰ​ብ​ሩ​ታ​ላ​ችሁ፤ እኔ እኮ ተስፋ የማ​ደ​ር​ገው መከ​ራ​ንና እግር ብረ​ትን ብቻ አይ​ደ​ለም፤ እኔ ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ሞ​ትም ቢሆን የቈ​ረ​ጥሁ ነኝ” አለ።


ሴቶ​ችም እንደ ትን​ሣኤ ቀን ተነ​ሥ​ተ​ው​ላ​ቸው ሙታ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ተቀ​በሉ፤ ተፈ​ር​ዶ​ባ​ቸው የሞ​ቱም አሉ፤ የም​ት​በ​ል​ጠ​ውን ሕይ​ወት ያገኙ ዘንድ ሊድኑ አል​ወ​ደ​ዱ​ምና።


እነርሱም በበጉ ደም በምስክራቸውም ቃል ድል ነሡት፤ ነፍሳቸውንም እስከ ሞት ድረስ አልወደዱም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios