Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢዮብ 8:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ረሱ ሁሉ ፍጻ​ሜ​አ​ቸው እን​ዲሁ ነው፤ የዝ​ንጉ ሰውም ተስፋ ትጠ​ፋ​ለች፤

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እግዚአብሔርን የሚረሱ መጨረሻቸው እንዲህ ነው፤ አምላክ የለሽ ኑሮ የሚኖሩም ሁሉ ተስፋቸው ትጠፋለች።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እግዚአብሔርን የሚረሱ ሁሉ ፍጻሜአቸው እንዲሁ ነው፥ የአምላክ አልባ ሰውም ተስፋ ይጠፋል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እግዚአብሔርን የሚረሱ ሰዎች ሁሉ ፍጻሜአቸው ልክ እንደዚሁ ነው፤ እግዚአብሔር የለም የሚሉ ሰዎች ተስፋቸው ይቈረጣል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እግዚአብሔርን የሚረሱ ሁሉ ፍጻሜአቸው እንዲሁ ነው፥ የዝንጉም ሰው ተስፋ ይጠፋል።

Ver Capítulo Cópia de




ኢዮብ 8:13
25 Referências Cruzadas  

የኃ​ጥ​ኣን መድ​ኀ​ኒ​ታ​ቸው ታል​ቃ​ለች። ተስ​ፋ​ቸ​ው​ንም ያጣሉ፥ የዝ​ን​ጉ​ዎች ዐይ​ኖ​ችም ይጠ​ፋሉ።”


ዝንጉ ሰው በፊቱ አይ​ገ​ባ​ምና እርሱ መድ​ኀ​ኒት ይሆ​ን​ል​ኛል።


ለኃ​ጥ​ኣን ሁሉ ሞት ምስ​ክ​ራ​ቸው ነው፥ እሳት የጉቦ ተቀ​ባ​ዮ​ችን ቤት ይበ​ላል።


ጤን​ነት ከሥ​ጋው ትር​ቃ​ለች። መከ​ራው ትጸ​ና​ለች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይበ​ቀ​ለ​ዋል።


የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞች ደስታ ታላቅ ሰልፍ ነው፥ የዝ​ን​ጉ​ዎ​ችም ደስታ ጥፋት ነው።


“ግብ​ዞች ግን በል​ባ​ቸው ቍጣን ያዘ​ጋ​ጃሉ፤ እር​ሱም ባሰ​ራ​ቸው ጊዜ አይ​ጮ​ኹም።


ገና በሥሩ ሳለ፥ ሳይ​ቈ​ረ​ጥም፥ ውኃ የማ​ይ​ጠጣ ተክል ሁሉ ይደ​ር​ቃል።


ኃጥ​ኣን እን​ዲህ አይ​ደ​ሉም፥ እን​ዲህ አይ​ደ​ሉም። ነገር ግን ነፋስ ከገጸ ምድር ጠርጎ እን​ደ​ሚ​ወ​ስ​ደው ትቢያ ናቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቤተ መቅ​ደሱ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዙፋኑ በሰ​ማይ ነው፤ ዐይ​ኖ​ቹም ወደ ድሃ ይመ​ለ​ከ​ታሉ፤ ቅን​ድ​ቦ​ቹም የሰው ልጆ​ችን ይመ​ረ​ም​ራሉ።


ኀጢ​አ​ተ​ኞች ወደ ሲኦል ይመ​ለሱ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ረሱ አሕ​ዛ​ብም ሁሉ።


ደስታ ከጻድቃን ጋር ትኖራለች፤ የኃጥኣን ተስፋ ግን ትጠፋለች።


ጻድቅ ሰው በሞተ ጊዜ ተስፋውን አያጣም፥ የክፉዎች ትምክሕታቸው ግን ትጠፋለች።


ኀጢአተኛ በተገለበጠበት ይጠፋል፥ የጻድቃን ቤቶች ግን ጸንተው ይኖራሉ።


በጽ​ዮን ያሉ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ፈሩ፤ መን​ቀ​ጥ​ቀጥ ዝን​ጉ​ዎ​ችን ያዘ፤ እሳት እን​ደ​ሚ​ነ​ድድ የሚ​ነ​ግ​ራ​ችሁ ማን ነው? የዘ​ለ​ዓ​ለም ሀገ​ር​ንስ የሚ​ነ​ግ​ራ​ችሁ ማን ነው?


አንቺ ግን ሰማ​ያ​ትን የፈ​ጠ​ረ​ውን፥ ምድ​ር​ንም የመ​ሠ​ረ​ታ​ትን ፈጣ​ሪ​ሽን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረስ​ተ​ሻል፤ ያጠ​ፋሽ ዘንድ ባዘ​ጋጀ ጊዜ ከአ​ስ​ጨ​ና​ቂው ቍጣ የተ​ነሣ ሁል​ጊዜ ቀኑን ሁሉ ፈር​ተ​ሻል፤ ይቈ​ጣሽ ዘንድ መክ​ሮ​አ​ልና፤ አሁን የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቅሽ ቍጣው የት አለ?


እኔም፦ ኀይ​ሌን፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዘንድ ያለ​ውን ተስ​ፋ​ዬን አጣሁ።


ከሁለትም ይሰነጥቀዋል፤ እድሉንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።


ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ያወ​ጣ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳ​ት​ረሳ ተጠ​ን​ቀቅ።


“ዛሬ እኔ አን​ተን የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛ​ዙ​ንና ፍር​ዱን፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ባለ​መ​ጠ​በቅ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳ​ት​ረሳ ተጠ​ን​ቀቅ፤


ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ያወ​ጣ​ህን፥


አም​ላ​ክ​ህ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽሞ ብት​ረሳ፥ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት ብት​ከ​ተል፥ ብታ​መ​ል​ካ​ቸ​ውም፥ ብት​ሰ​ግ​ድ​ላ​ቸ​ውም፥ ፈጽሞ እን​ደ​ም​ት​ጠፋ እኔ ዛሬ​ውኑ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን አስ​መ​ሰ​ክ​ር​ብ​ሃ​ለሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios