Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢዮብ 27:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ሥቃይ እንደ ጎርፍ ታገ​ኘ​ዋ​ለች፤ በሌ​ሊ​ትም ዐውሎ ነፋስ ትነ​ጥ​ቀ​ዋ​ለች።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ድንጋጤ እንደ ጐርፍ ድንገት ያጥለቀልቀዋል፤ ዐውሎ ነፋስም በሌሊት ይዞት ይሄዳል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ድንጋጤ እንደ ጐርፍ ታገኘዋለች፥ በሌሊትም ዐውሎ ነፋስ ትነጥቀዋለች።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ድንጋጤ እንደ ጐርፍ በድንገት ይደርስበታል፤ በሌሊትም ዐውሎ ነፋስ ይነጥቀዋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ድንጋጤ እንደ ጐርፍ ታገኘዋለች፥ በሌሊትም ዐውሎ ነፋስ ትነጥቀዋለች።

Ver Capítulo Cópia de




ኢዮብ 27:20
17 Referências Cruzadas  

በዚ​ያ​ችም ሌሊት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ መጣ፤ ከአ​ሦ​ራ​ው​ያ​ንም ሰፈር መቶ ሰማ​ንያ አም​ስት ሺህ ገደለ፤ ማለ​ዳም በተ​ነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉ በድ​ኖች ነበሩ።


የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግጥ ድም​ፅም በጆ​ሮው ነው፤ በደ​ኅ​ን​ነ​ትም ይኖር ዘንድ ተስፋ በሚ​ያ​ደ​ር​ግ​በት ጊዜ ጥፋት ይመ​ጣ​በ​ታል።


መከራ በዙ​ሪ​ያው ታጠ​ፋ​ዋ​ለች፤ ብዙ ጠላ​ቶ​ችም ከእ​ግሩ በታች ይመ​ጣሉ።


“ሆዱን ቢያ​ጠ​ግብ፥ የመ​ዓት መቅ​ሠ​ፍት ይጨ​መ​ር​በ​ታል፤ የሕ​ማ​ሙም ሥቃይ ይጸ​ና​በ​ታል።


እንደ ሕልም ይበ​ር​ራል፤ እር​ሱም አይ​ገ​ኝም፤ ሲነ​ጋም እን​ደ​ማ​ይ​ታ​ወቅ እንደ ሌሊት ራእይ ይሰ​ደ​ዳል።


በነ​ፋ​ስም ፊት እንደ ገለባ፥ አውሎ ነፋ​ስም እን​ደ​ሚ​ወ​ስ​ደው ትቢያ ይሆ​ናሉ።


ጊዜ​ያ​ቸው ሳይ​ደ​ርስ ተነ​ጠቁ፤ መሠ​ረ​ታ​ቸ​ውም እንደ ፈሳሽ ውኃ ፈሰሰ።


እርሱ በውኃ ፊት ላይ በርሮ ያል​ፋል፤ እድል ፋን​ታ​ውም በም​ድር ላይ የተ​ረ​ገ​መች ናት፤


የሚ​ጮ​ኸ​ው​ንና ሰውን የማ​ይ​ሰ​ማ​ውን ከንቱ ነገር ያገ​ኘ​ዋል፥ በድ​ሆች ላይ ክፉ አድ​ር​ጎ​አ​ልና።


ቃላ​ቸው ወደ ምድር ሁሉ ወጣ። ነገ​ራ​ቸ​ውም እስከ ዓለም ዳርቻ ደረሰ።


ከሌ​ሊት ግርማ፥ በመ​ዓ​ልት ከሚ​በ​ርር ፍላጻ፥


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ እኩለ ሌሊት በሆነ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ፋን ከተ​ቀ​መ​ጠው ከፈ​ር​ዖን በኵር ጀምሮ እስከ ውኃ ቀጅዋ ምር​ኮኛ በኵር ድረስ፥ በግ​ብፅ ምድር በኵ​ሩን ሁሉ፥ የእ​ን​ስ​ሳ​ው​ንም በኵር ሁሉ መታ።


“በመ​ከ​ራዬ ሳለሁ ወደ አም​ላኬ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኽሁ፤ በሲ​ኦ​ልም ሆድ ውስጥ የጩ​ኸ​ቴን ድምፅ ሰማኝ፤ ቃሌ​ንም አዳ​መ​ጥህ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios