Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢዮብ 27:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እርሱ ብርን እንደ አፈር ቢሰ​በ​ስብ፥ ወር​ቅ​ንም እንደ ጭቃ ቢያ​ዘ​ጋጅ፥

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ብርን እንደ ዐፈር ቢከምር፣ ልብስንም እንደ ሸክላ ጭቃ ቢያከማች፣

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እርሱ ብርን እንደ አፈር ቢከምር፥ ልብስንም እንደ ጭቃ ቢያዘጋጅ፥

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ክፉ ሰው ብርን እንደ ዐፈር ሊያጋብስ፥ ልብስንም እንደ ሸክላ ሊከምር ይችላል፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እርሱ ብርን እንደ አፈር ቢከምር፥ ልብስንም እንደ ጭቃ ቢያዘጋጅ፥

Ver Capítulo Cópia de




ኢዮብ 27:16
15 Referências Cruzadas  

ንጉ​ሡም ብሩ​ንና ወር​ቁን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ ድን​ጋይ እን​ዲ​በዛ አደ​ረ​ገው፤ የዝ​ግ​ባም እን​ጨት ብዛት በቆላ እን​ደ​ሚ​በ​ቅል ሾላ ሆነ።


“እርሱ ባለ​ጠጋ አይ​ሆ​ንም፤ ሀብ​ቱም አይ​ጸ​ናም፤ ጥላ​ው​ንም በም​ድር ላይ አይ​ጥ​ልም፤


የተ​ዋ​ረዱ ሰዎች ልጆ​ቹን ያጠ​ፋሉ፤ እጆ​ቹም የኀ​ዘን እሳ​ትን ያቀ​ጣ​ጥ​ላሉ።


በዓ​ለቱ ቋጥኝ ላይ ለራ​ስህ መዝ​ገ​ብን ታኖ​ራ​ለህ። የሶ​ፎ​ርም ወርቅ እንደ ጅረት ድን​ጋይ ይሆ​ን​ል​ሃል።


ለእ​ር​ሱም የቀ​ሩት ፈጽ​መው ይሞ​ታሉ። ለመ​በ​ለ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የሚ​ያ​ዝ​ን​ላ​ቸው የለም።


ይህን ሁሉ ጻድ​ቃን ይወ​ስ​ዱ​ታል። ሀብ​ቱ​ንም ቅኖች ይከ​ፋ​ፈ​ሉ​ታል።


ወይም ወር​ቅን ካበዙ፥ ቤታ​ቸ​ው​ንም ብር ከሞሉ አለ​ቆች ጋር፥


ደግ ሰው ለልጅ ልጅ ያወርሳል፥ የኀጢአተኞች ብልጽግና ግን ለጻድቃን ይደልባል።


እርሱ በፊቱ ደግ ለሆነ ሰው ጥበ​ብ​ንና ዕው​ቀ​ትን፥ ደስ​ታ​ንም ይሰ​ጠ​ዋል፤ ለኀ​ጢ​አ​ተኛ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደግ ለሆነ ይሰጥ ዘንድ እን​ዲ​ሰ​በ​ስ​ብና እን​ዲ​ያ​ከ​ማች ጥረ​ትን ይሰ​ጠ​ዋል። ይህ ደግሞ ከንቱ፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


እነዚህ ሁሉ፦ ለእርሱ ያልሆነውን ወደ እርሱ ለሚሰበስብ መያዣውንም ለራሱ የሚያበዛ ወዮለት! እስከ መቼ ነው? እያሉ ምሳሌ አይመስሉበትምን?


እናንተ በመክቴሽ የምትኖሩ ሆይ፥ የከነዓን ሕዝብ ሁሉ ጠፍተዋልና፥ ብርም የተሸከሙ ሁሉ ተቈርጠዋልና አልቅሱ።


ጢሮስም ምሽግን ለራስዋ ሠርታለች፥ ብሩንም እንደ አፈር ጥሩውንም ወርቅ እንደ መንገድ ጭቃ አከማችታለች።


“ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤


ሀብታችሁ ተበላሽቶአል፤ ልብሳችሁም በብል ተበልቶአል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios