Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢዮብ 15:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ከጨ​ለማ በም​ንም አያ​መ​ል​ጥም፤ ነፋ​ስም ቅር​ን​ጫ​ፎ​ቹን ያደ​ር​ቃ​ቸ​ዋል፥ አበ​ባ​ዎ​ቹም ይረ​ግ​ፋሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ከጨለማ አያመልጥም፤ ቅርንጫፎቹን ነበልባል ያደርቃቸዋል፤ በእግዚአብሔርም እስትንፋስ ይወሰዳል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ከጨለማ አይወጣም፥ ነበልባሉም ቅርንጫፎቹን ያደርቃቸዋል፥ አበባዎቹም ይረግፋሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ከጨለማ ማምለጥ አይችልም፤ የእሳት ነበልባል ቅርንጫፎቹን እንዳደረቃቸውና አበባዎቹም በነፋስ እንደ ረገፉበት ዛፍ ይሆናል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ከጨለማ አይወጣም፥ ነበልባሉም ቅርንጫፎቹን ያደርቃቸዋል፥ አበባዎቹም ይረግፋሉ።

Ver Capítulo Cópia de




ኢዮብ 15:30
25 Referências Cruzadas  

ከጨ​ለማ ተመ​ልሶ እን​ዲ​ወጣ ተስፋ የለ​ውም፥ ለሰ​ይ​ፍም ኀይል ፈጽሞ ተዳ​ር​ጎ​አል።


ለአ​ሞ​ራ​ዎ​ችም ምግብ ሆኖ ተሰ​ጥ​ቶ​አል በድን ሆኖ እን​ደ​ሚ​ቈ​ይም እርሱ ራሱ ያው​ቃል። የጨ​ለማ ቀንም እንደ አውሎ ነፋስ ትወ​ስ​ደ​ዋ​ለች።


ለኃ​ጥ​ኣን ሁሉ ሞት ምስ​ክ​ራ​ቸው ነው፥ እሳት የጉቦ ተቀ​ባ​ዮ​ችን ቤት ይበ​ላል።


ሥሩ ከበ​ታቹ ይደ​ር​ቃል፤ ፍሬ​ውም ከላዩ ይረ​ግ​ፋል።


ከብ​ር​ሃን ወደ ጨለማ አር​ቀው ያፈ​ል​ሱ​ታል።


ጨለማ ሁሉ ይጠ​ብ​ቀ​ዋል፤ ዕፍ የማ​ይ​ባል እሳ​ትም ይበ​ላ​ዋል፤ እን​ግ​ዳም ቤቱን ያጠ​ቃ​ዋል።


በእ​ው​ነት ሀብ​ታ​ቸው ጠፋ፥ የቀ​ረ​ው​ንም እሳት በላች።


ይህ በሕ​ዋ​ሳት ሁሉ የሚ​ነ​ድድ እሳት፥ የገ​ባ​በ​ት​ንም ሁሉ ከሥር የሚ​ነ​ቅል ነውና።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ይጠ​ፋሉ፥ በቍ​ጣ​ውም መን​ፈስ ያል​ቃሉ።


በቀን ጨለማ ያገ​ኛ​ቸ​ዋል፥ በቀ​ት​ርም ጊዜ በሌ​ሊት እን​ዳሉ ይር​መ​ሰ​መ​ሳሉ።


ነገር ግን ለድ​ሆች በጽ​ድቅ ይፈ​ር​ዳል፤ ለም​ድ​ርም የዋ​ሆች በቅ​ን​ነት ይበ​ይ​ናል፤ በአ​ፉም ቃል ምድ​ርን ይመ​ታል፤ በከ​ን​ፈ​ሩም እስ​ት​ን​ፋስ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ያጠ​ፋ​ዋል።


ከቀ​ድ​ሞም ጀምሮ የማ​ቃ​ጠያ ስፍራ ተዘ​ጋ​ጅ​ታ​ለች፤ ለን​ጉ​ሥም ተበ​ጅ​ታ​ለች፤ ጥል​ቅና ሰፊም አድ​ር​ጎ​አ​ታል፤ እሳ​ትና ብዙ ማገዶ ተከ​ም​ሮ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃ​ጥ​ለ​ዋል።


ስለ​ዚህ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ሁን አጨ​ድ​ኋ​ቸው፤ በአ​ፌም ቃል ገደ​ል​ኋ​ቸው፤ ፍር​ዴም እንደ ብር​ሃን ይወ​ጣል።


በዚያን ጊዜ ንጉሡ አገልጋዮቹን ‘እጁንና እግሩን አስራችሁ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል፤’ አለ።


በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል ‘እናንተ ርጉማን! ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።


የመንግሥት ልጆች ግን በውጭ ወደ አለው ጨለማ ይጣላሉ፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”


ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው እነዚህ ውሃ የሌለባቸው ምንጮች በዐውሎ ነፋስም የተነዱ ደመናዎች ናቸው።


የገዛ ነውራቸውን አረፋ እየደፈቁ ጨካኝ የባሕር ማዕበል፥ ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው የሚንከራተቱ ከዋክብት ናቸው።


አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios