Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤርምያስ 50:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 ስለ​ዚህ የዱር አራ​ዊት ከተ​ኵ​ላ​ዎች ጋር ይቀ​መ​ጡ​ባ​ታል፤ ሰጎ​ኖ​ችም ይቀ​መ​ጡ​ባ​ታል፤ ሰውም ከዚያ ወዲያ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም፤ እስከ ልጅ ልጅም ድረስ የሚ​ኖ​ር​ባት የለም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 “ስለዚህ የምድረ በዳ አራዊትና የጅብ መኖሪያ፣ የጕጕትም ማደሪያ ትሆናለች፤ ከእንግዲህ ወዲህ ማንም አይኖርባትም፤ ከትውልድ እስከ ትውልድም የሚቀመጥባት አይገኝም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 ስለዚህ በባቢሎን የምድረ በዳ አራዊት ከተኩላዎች ጋር ይቀመጡባታል፥ ሰጐኖችም ይቀመጡባታል፤ ሰውም ከዚያ ወዲያ ለዘለዓለም አይቀመጥባትም፥ እስከ ልጅ ልጅም ድረስ የሚኖርባት የለም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 “ስለዚህ የዱር አራዊት ከቀበሮችና ከሰጎኖች ጋር በባቢሎን ይኖራሉ፤ እንዲሁም እስከ መቼም ድረስ ከትውልድ እስከ ትውልድ የሰው መኖሪያ አትሆንም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 ስለዚህ የምድረ በዳ አራዊት ከተኩላዎች ጋር ይቀመጡባታል፥ ሰጐኖችም ይቀመጡባታል፥ ሰውም ከዚያ ወዲያ ለዘላለም አይቀመጥባትም፥ እስከ ልጅ ልጅም ድረስ የሚኖርባት የለም።

Ver Capítulo Cópia de




ኤርምያስ 50:39
12 Referências Cruzadas  

“ባቢ​ሎ​ንን የወ​ፎች መኖ​ሪያ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ እንደ ኢም​ን​ትም ትሆ​ና​ለች፤ በጥ​ፋ​ትም እንደ ረግ​ረግ ጭቃ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ” ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“ሰባው ዓመ​ትም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፥ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉ​ሥና ያን ሕዝብ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው እቀ​ጣ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ን​ንም ምድር ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ሕዝቤ ከሰ​ሜን በእ​ር​ስዋ ላይ ወጥ​ት​ዋል፤ ምድ​ር​ዋ​ንም ባድማ ያደ​ር​ጋል፤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም አይ​ገ​ኝም፤ ከሰው ጀምሮ እስከ እን​ስሳ ድረስ ሸሽ​ተው ሄደ​ዋል።


ከአ​ን​ተም ለማ​ዕ​ዘን የሚ​ሆን ድን​ጋ​ይ​ንና ለመ​ሠ​ረት የሚ​ሆን ድን​ጋ​ይን አይ​ወ​ስ​ዱም፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አጠ​ፋ​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ከተ​ሞ​ችዋ ባድ​ማና ደረቅ ምድር፥ ሰውም የማ​ይ​ቀ​መ​ጥ​በት፥ የሰ​ውም ልጅ የማ​ያ​ል​ፍ​በት ምድር ሆኑ።


በብርቱም ድምፅ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፤ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios