Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤርምያስ 50:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና የይ​ሁዳ ልጆች በአ​ን​ድ​ነት ተገ​ፍ​ተ​ዋል፤ የማ​ረ​ኩ​አ​ቸ​ውም ሁሉ በኀ​ይል ይይ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፤ ይለ​ቅ​ቁ​አ​ቸ​ውም ዘንድ እንቢ ብለ​ዋል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የእስራኤል ሕዝብና የይሁዳ ሕዝብ፣ በአንድነት ተጨቍነዋል፤ የማረኳቸውም ሁሉ አጥብቀው ይዘዋቸዋል፤ ይለቅቋቸውም ዘንድ እንቢ ብለዋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል ልጆችና የይሁዳ ልጆች በአንድነት ተጨቊነዋል፥ የማረኳቸውም ሁሉ በኃይል ይዘዋቸዋል፥ እነርሱንም ለመልቀቅ እንቢ ብለዋል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ ተጨቊነዋል፤ ማርከው የወሰዱአቸውም ሁሉ አጥብቀው ይዘዋቸዋል፤ ሊለቁአቸውም አልፈለጉም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል ልጆችና የይሁዳ ልጆች በአንድነት ተገፍተዋል፥ የማረኳቸውም ሁሉ በኃይል ይይዙአቸዋል፥ ይለቅቁአቸውም ዘንድ እንቢ ብለዋል።

Ver Capítulo Cópia de




ኤርምያስ 50:33
16 Referências Cruzadas  

ፈር​ዖ​ንም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እለ​ቅቅ ዘንድ ቃሉን የም​ሰ​ማው እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማን ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ው​ቅም፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ደግሞ አል​ለ​ቅ​ቅም” አለ።


ለመ​ል​ቀቅ እንቢ ብትል ግን እነሆ፥ ሀገ​ር​ህን ሁሉ በጓ​ጕ​ን​ቸ​ሮች እመ​ታ​ለሁ፤


ዓለ​ሙን ሁሉ ባድማ ያደ​ረገ፥ ከተ​ሞ​ች​ንም ያፈ​ረሰ፥ ምር​ኮ​ኞ​ቹ​ንም ወደ ቤታ​ቸው ያል​ሰ​ደደ ሰው ይህ ነውን?


በሕ​ዝቤ ላይ ተቈ​ጥቼ ነበር፤ ርስ​ቴ​ንም አረ​ከ​ስሽ፤ በእ​ጅ​ሽም አሳ​ልፌ ሰጠ​ኋ​ቸው፤ ለሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸው አል​ራ​ራ​ሽም፤ ቀን​በ​ራ​ቸ​ው​ንም እጅግ አክ​ብ​ደ​ሻል።


ወደ በደ​ሉ​ሽና ወደ አጐ​ሰ​ቈ​ሉሽ ሰዎች እጅ፥ ሰው​ነ​ት​ሽ​ንም ዝቅ በዪ፥ ድል​ድይ አድ​ር​ገን እን​ሻ​ገ​ር​ብሽ ወደ​ሚ​ሏት ሰዎች እጅ እመ​ል​ሰ​ዋ​ለሁ።” በም​ድ​ርም ላይ በሆ​ድሽ አስ​ተ​ኙሽ፤ መን​ገ​ደ​ኞ​ችም ሁሉ ረገ​ጡሽ።


ይህን ጾም የመ​ረ​ጥሁ አይ​ደ​ለም ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነገር ግን የበ​ደ​ልን እስ​ራት ፍታ፤ ጠማ​ማ​ውን ሁሉ አቅና፤ የተ​ጨ​ነ​ቀ​ው​ንም ሁሉ አድን፤ የዐ​መፃ ደብ​ዳ​ቤ​ንም ተው።


ልጆ​ቻ​ቸ​ውም እንደ ቀድ​ሞው ይሆ​ናሉ፤ ምስ​ክ​ር​ነ​ታ​ቸ​ውም በፊቴ ጸንቶ ይኖ​ራል፤ የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ቸ​ው​ንም ሁሉ እቀ​ጣ​ለሁ።


ያገ​ኙ​አ​ቸው ሁሉ በሉ​አ​ቸው፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፦ በጽ​ድቅ ማደ​ሪያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ፥ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ተስፋ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኀጢ​አት ስለ ሠሩ እኛ አና​ሳ​ር​ፋ​ቸ​ውም አሉ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios