Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤርምያስ 50:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር በባ​ቢ​ሎን ላይ በነ​ቢዩ በኤ​ር​ም​ያስ የተ​ና​ገ​ረው ቃል ይህ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር ስለ ባቢሎንና ስለ ባቢሎናውያን ምድር፣ በነቢዩ ኤርምያስ በኩል የተናገረው ቃል ይህ ነው፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ጌታ ስለ ከለዳውያን ምድር ስለ ባቢሎን በነቢዩ በኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ስለ ባቢሎንና ስለ ሕዝብዋ እግዚአብሔር በነቢዩ በኤርምያስ አማካይነት የተናገረው ቃል ይህ ነው፦

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እግዚአብሔር ስለ ከለዳውያን ምድር ስለ ባቢሎን በነቢዩ በኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው።

Ver Capítulo Cópia de




ኤርምያስ 50:1
22 Referências Cruzadas  

የግ​ዛ​ቱም መጀ​መ​ሪያ በሰ​ና​ዖር ሀገር ባቢ​ሎን፥ ኦሬክ፥ አር​ካድ፥ ካሌ​ድን ናቸው።


ታራም ልጁን አብ​ራ​ም​ንና የልጅ ልጁን የአ​ራ​ንን ልጅ ሎጥን፥ የል​ጁ​ንም የአ​ብ​ራ​ምን ሚስት ምራ​ቱን ሦራን ወሰደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ወደ ከነ​ዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር አወ​ጣ​ቸው። ወደ ካራ​ንም መጡ፤ በዚ​ያም ተቀ​መጡ።


ስለ​ዚ​ህም ስምዋ ባቢ​ሎን ተባለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ የም​ድ​ርን ቋንቋ ሁሉ ደባ​ል​ቆ​አ​ልና፤ ከዚ​ያም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ሁሉ ፊት ላይ እነ​ር​ሱን በት​ኖ​አ​ቸ​ዋል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በእኔ ተና​ገረ፤ ቃሉም በአ​ን​ደ​በቴ ላይ ነበረ።


የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ከባ​ቢ​ሎ​ንና ከኩታ፥ ከአ​ዋና ከሐ​ማት፥ ከሴ​ፌ​ር​ዋ​ይም ሰዎ​ችን አመጣ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ፋንታ በሰ​ማ​ርያ ከተ​ሞች አኖ​ራ​ቸው፤ ሰማ​ር​ያ​ንም ወረ​ሱ​አት፤ በከ​ተ​ሞ​ች​ዋም ተቀ​መጡ።


እር​ሱም ገና ይህን ሲና​ገር ሦስ​ተ​ኛው መል​እ​ክ​ተኛ መጥቶ ለኢ​ዮብ እን​ዲህ አለው፥ “ፈረ​ሰ​ኞች በሦ​ስት ረድፍ ከብ​በው ግመ​ሎ​ችን ማር​ከው ወሰዱ፥ ብላ​ቴ​ኖ​ች​ህ​ንም በሰ​ይፍ ስለት ገደሉ፤ እኔም ብቻ​ዬን አም​ልጬ እነ​ግ​ርህ ዘንድ መጣሁ።”


ይህ​ንም ሙሾ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ላይ ታነ​ሣ​ለህ፤ እን​ዲ​ህም ትላ​ለህ፥ “አስ​ጨ​ናቂ እን​ዴት ዐረፈ! አስ​ገ​ባ​ሪም እን​ዴት ጸጥ አለ!


እነሆ፥ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን ሀገር አሦ​ራ​ው​ያን አጥ​ፍ​ተ​ዋ​ታ​ልና፤ ግን​ብ​ዋም ወድ​ቆ​አል፤


“ሰባው ዓመ​ትም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፥ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉ​ሥና ያን ሕዝብ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው እቀ​ጣ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ን​ንም ምድር ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


የገዛ ራሱም ምድር ጊዜ እስ​ኪ​መጣ ድረስ አሕ​ዛብ ሁሉ ለእ​ር​ሱና ለልጁ ለልጅ ልጁም ይገ​ዛሉ፤ በዚ​ያን ጊዜም ብዙ አሕ​ዛ​ብና ታላ​ላ​ቆች ነገ​ሥ​ታት ለእ​ርሱ ይገ​ዙ​ለ​ታል።


ከዚ​ህም በኋላ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሀገር ወጥቶ በካ​ራን ተቀ​መጠ፤ ከዚ​ያም አባቱ ከሞተ በኋላ፥ ዛሬ እና​ንተ ወደ አላ​ች​ሁ​ባት ወደ​ዚች ሀገር አመ​ጣው።


ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፤ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።


ሌላም ሁለተኛ መልአክ “አሕዛብን ሁሉ የዝሙትዋን ቍጣ ወይን ጠጅ ያጠጣች ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች!” እያለ ተከተለው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios