Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤርምያስ 48:46 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

46 ሞአብ ሆይ! ወዮ​ልሽ! የካ​ሞሸ ወገን ጠፍ​ቶ​አል፤ ወን​ዶች ልጆ​ችሽ ተማ​ር​ከው ተወ​ስ​ደ​ዋ​ልና፥ ሴቶች ልጆ​ች​ሽም ወደ ምርኮ ሄደ​ዋ​ልና።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

46 ሞዓብ ሆይ፤ ወዮልህ! የካሞሽ ሕዝብ ተደምስሷል፤ ወንዶች ልጆችህ በምርኮ ተወስደዋል፤ ሴቶች ልጆችህም ተግዘዋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

46 ሞዓብ ሆይ! ወዮልህ! የካሞሽ ሰዎች ጠፍቶአል፤ ወንዶች ልጆችህ ተማርከዋልና፥ ሴቶች ልጆችህም ወደ ምርኮ ሄደዋልና።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

46 ለሞአብ ሕዝብ ወዮላችሁ! ካሞሽ ለተባለው ጣዖት የሚሰግዱ ሕዝብ ተደመሰሱ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም ተማርከው ተወሰዱ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

46 ሞዓብ ሆይ፥ ወዮልህ! የካሞሽ ወገን ጠፍቶአል፥ ወንዶች ልጆችህ ተማርከዋልና፥ ሴቶች ልጆችህም ወደ ምርኮ ሄደዋልና።

Ver Capítulo Cópia de




ኤርምያስ 48:46
7 Referências Cruzadas  

ያን​ጊ​ዜም ሰሎ​ሞን ለሞ​አብ ርኵ​ሰት ለኮ​ሞስ፥ ለአ​ሞን ልጆች ርኵ​ሰት ለሞ​ሎክ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አን​ጻር በአ​ለው ተራራ ላይ መስ​ገ​ጃን ሠራ።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ፊት ለፊት በር​ኵ​ስት ተራራ ቀኝ የነ​በ​ሩ​ትን፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሰሎ​ሞን ለሲ​ዶ​ና​ው​ያን ርኵ​ስት ለአ​ስ​ታ​ሮት፥ ለሞ​ዓ​ብም ርኵ​ሰት ለካ​ሞሽ፥ ለአ​ሞ​ንም ልጆች ርኵ​ሰት ለሞ​ሎክ ያሠ​ራ​ቸ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎች ንጉሡ ርኩስ አደ​ረገ።


ጫጩ​ቶ​ች​ዋን አሳ​ድጋ እንደ ተወች ወፍ ሆና​ለ​ችና፤ የሞ​ዓብ ሴት ልጅም እንደ ሰባ የበግ ጠቦት ሆነች።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ይታ​መ​ን​ባት ከነ​በ​ረው ከቤ​ቴል እን​ዳ​ፈረ፥ እን​ዲሁ ሞአብ ከካ​ሞሽ ታፍ​ራ​ለች።


በሥ​ራ​ሽና በመ​ዝ​ገ​ብሽ ታም​ነ​ሻ​ልና አንቺ ደግሞ ትያ​ዢ​ያ​ለሽ፤ ካሞ​ሽም ከካ​ህ​ና​ቱና ከአ​ለ​ቆቹ ጋር በአ​ን​ድ​ነት ይማ​ረ​ካል።


ሞዓብ ሆይ፥ ወዮ​ልህ! የካ​ሞስ ሕዝብ ሆይ፥ ጠፋህ፤ ወን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለማ​ደን፥ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለም​ርኮ፤ ለአ​ሞ​ራ​ው​ያን ንጉሥ ለሴ​ዎን ሰጠ።


አም​ላ​ክህ ኮሞስ የሚ​ሰ​ጥ​ህን የም​ት​ወ​ርስ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? እኛም አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊ​ታ​ችን ያስ​ወ​ጣ​ቸ​ውን የእ​ነ​ር​ሱን ምድር የም​ን​ወ​ርስ አይ​ደ​ለ​ን​ምን?


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios