Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤርምያስ 48:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 በሞ​አብ የሚ​ኖሩ ከተ​ሞ​ችን ትተው በዓ​ለት ውስጥ ተቀ​መጡ፤ በገ​ደል አፋ​ፍም ቤቷን እን​ደ​ም​ት​ሠራ እንደ ርግብ ሆኑ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 እናንተ በሞዓብ የምትኖሩ ሆይ፤ ከከተማ ወጥታችሁ በዐለት መካከል ኑሩ፤ በገደል አፋፍ ላይ ጐጆዋን እንደምትሠራ፣ እንደ ርግብ ሁኑ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 እናንተ በሞዓብ የምትኖሩ ሆይ! ከተሞችን ትታችሁ በዓለት ንቃቃት መካከል ተቀመጡ፥ በገደል አፋፍም ቤትዋን እንደምትሠራ እንደ ርግብ ሁኑ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 “የሞአብ ነዋሪዎች ሆይ! ከተሞቻችሁን ለቃችሁ በገደል አፋፍ ጎጆዋን እንደምትሠራ እንደ ርግብ በመሆን በቋጥኞች መካከል ኑሩ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 እናንተ በሞዓብ የምትኖሩ ሆይ፥ ከተሞችን ትታችሁ በዓለት ውስጥ ተቀመጡ፥ በገደል አፋፍም ቤትዋን እንደምትሠራ እንደ ርግብ ሁኑ።

Ver Capítulo Cópia de




ኤርምያስ 48:28
10 Referências Cruzadas  

ደግሞ ሰባት ቀን ቆይቶ፥ ርግ​ብን ላካት፤ ዳግ​መ​ኛም ወደ እርሱ አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም።


ፊት​ህን አሳ​የኝ፥ ቃል​ህ​ንም አሰ​ማኝ፤ ቃልህ ያማረ፥ ፊት​ህም የተ​ዋበ ነውና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምድ​ርን ያና​ውጥ ዘንድ በተ​ነሣ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ፍ​ራ​ትና ከግ​ር​ማው ክብር የተ​ነሣ ወደ ድን​ጋይ ዋሻና ወደ ምድር ንቃ​ቃት ውስጥ ያገ​ቡ​አ​ቸ​ዋል።


በርራ እን​ድ​ት​ወጣ ለሞ​አብ ክንፍ ስጡ​አት፤ ከተ​ሞ​ች​ዋም ባድማ ይሆ​ናሉ፤ የሚ​ኖ​ር​ባ​ቸ​ውም የለም።


በዓ​ለት ንቃ​ቃት ውስጥ የም​ት​ቀ​መጥ፥ የተ​ራ​ራ​ውን ከፍታ የም​ት​ይዝ ሆይ! ድፍ​ረ​ት​ህና የል​ብህ ኵራት አነ​ሣ​ሥ​ተ​ው​ሃል። ቤት​ህ​ንም ምንም እንደ ንስር ከፍ ብታ​ደ​ርግ፥ ከዚያ አወ​ር​ድ​ሃ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እና​ንተ በድ​ዳን የም​ት​ኖሩ ሆይ! የዔ​ሳ​ውን ጥፋት፥ የም​ጐ​በ​ኝ​በ​ትን ጊዜ አመ​ጣ​በ​ታ​ለ​ሁና ሽሹ፤ ወደ ኋላም ተመ​ለሱ፤ በጥ​ል​ቅም ጕድ​ጓድ ውስጥ ተቀ​መጡ።


የም​ድ​ያ​ምም እጅ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ጠነ​ከ​ረች፤ ከም​ድ​ያ​ምም ፊት የተ​ነሣ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በተ​ራ​ሮ​ችና በገ​ደ​ሎች ላይ ጕድ​ጓ​ድና ዋሻ፥ ምሽ​ግም አበጁ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ወደ እነ​ርሱ መሄድ እን​ደ​ሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ በዋ​ሻና በግ​ንብ፥ በገ​ደ​ልና በቋ​ጥኝ፥ በጕ​ድ​ጓ​ድም ውስጥ ተሸ​ሸጉ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios