Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤርምያስ 48:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 በአ​ሮ​ዔር የም​ት​ኖሪ ሆይ! በመ​ን​ገድ አጠ​ገብ ቆመሽ ተመ​ል​ከቺ፤ የሸ​ሸ​ው​ንና ያመ​ለ​ጠ​ውን፦ ምን ሆኖ​አል? ብለሽ ጠይ​ቂው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 አንቺ በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ፤ በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፤ የሚሸሸውን ወንድ፣ የምታመልጠውንም ሴት፣ ‘ምን ተፈጠረ?’ ብለሽ ጠይቂ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ! በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፤ የሸሸውንና ያመለጠችውን፦ ምን ሆኖአል?፥ ብለሽ ጠይቂ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በዓሮዔር የምትኖሩ ሁሉ፥ በመንገድ ዳር ቆማችሁ ተጠባበቁ፤ የሚሸሹትን ወንዶችና የሚያመልጡትን ሴቶች ሁሉ በመጠየቅ፥ የሆነውን ነገር ሁሉ ዕወቁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 በአሮዔር የምትኖሪ ሆይ፥ በመንገድ አጠገብ ቆመሽ ተመልከቺ፥ የሸሸውንና ያመለጠችውን፦ ምን ሆኖአል? ብለሽ ጠይቂ።

Ver Capítulo Cópia de




ኤርምያስ 48:19
10 Referências Cruzadas  

ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ተሻ​ገሩ፤ በጋድ ሸለቆ መካ​ከል ባለ​ች​ውም በኢ​ያ​ዜር ከተማ ቀኝ በኩል በአ​ሮ​ዔር ላይ ሰፈሩ።


እስከ ናባ​ውና እስከ በኣ​ል​ሜ​ዎን ድረስ በአ​ሮ​ዔር የተ​ቀ​መ​ጠው የኢ​ዩ​ኤል ልጅ የሰ​ማዕ ልጅ የዖ​ዛዝ ልጅ ቤላ፤


የጋድ ልጆች ዲቦ​ንን፥ አጣ​ሮ​ትን፥ አሮ​ዔ​ርን፤


በአ​ር​ኖን ሸለቆ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔ​ርና በሸ​ለ​ቆ​ውም ውስጥ ካለ​ችው ከተማ ጀም​ረን እስከ ገለ​ዓድ ተራራ ድረስ ማን​ኛ​ዪ​ቱም ከተማ አላ​መ​ለ​ጠ​ች​ንም፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁሉን አሳ​ልፎ በእ​ጃ​ችን ሰጠን።


በሐ​ሴ​ቦን የተ​ቀ​መ​ጠው፥ በአ​ር​ኖ​ንም ሸለቆ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር፥ ከሸ​ለ​ቆ​ውም መካ​ከል ጀምሮ የገ​ለ​ዓ​ድን እኩ​ሌታ እስከ ኢያ​ቦቅ ወንዝ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ፤


እስ​ራ​ኤ​ልም በሐ​ሴ​ቦ​ንና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ፥ በአ​ሮ​ዔ​ርና በመ​ን​ደ​ሮ​ችዋ፥ በአ​ር​ኖ​ንም አቅ​ራ​ቢያ ባሉት ከተ​ሞች ሁሉ ሦስት መቶ ዓመት ተቀ​ምጦ በነ​በረ ጊዜ፥ በዚያ ዘመን ስለ ምን አላ​ዳ​ን​ሃ​ቸ​ውም ነበር?


ሰው​ዬ​ው​ንም፥ “አንተ ከወ​ዴት ነህ?” አለው። እር​ሱም፥ “ጦር​ነቱ ከአ​ለ​በት ስፍራ የመ​ጣሁ እኔ ነኝ፥ ዛሬም ከሰ​ልፍ ሸሸሁ” አለ። እር​ሱም፥ “ልጄ ሆይ! ነገ​ሩስ እን​ዴት ሆነ?” አለው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios