Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤርምያስ 46:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ግብፅ እንደ ወንዝ ይነ​ሣል፤ ከባ​ሕ​ሩም እን​ደ​ሚ​ታ​ወክ ማዕ​በል ይሆ​ናል፤ እር​ሱም እን​ዲህ ብሏል፥ “እነ​ሣ​ለሁ፤ ምድ​ር​ንም ሁሉ እከ​ድ​ና​ለሁ፤ ከተ​ሞ​ች​ንና የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ቸ​ውን አጠ​ፋ​ለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ግብጽ እንደ አባይ ወንዝ ሙላት ይዘልላል፤ እንደ ደራሽ ወንዝ ይወረወራል፤ ‘እወጣለሁ፤ ምድርንም እሸፍናለሁ፤ ከተሞችንና ነዋሪዎቻቸውን አጠፋለሁ’ ይላል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ግብጽ እንደ ግብጽ ወንዝ ይነሳል ውኃውም እንደ ወንዞች ይናወጣል፤ እርሱም፦ እነሣለሁ ምድርንም ሁሉ እሸፍናለሁ፤ ከተሞችንና የሚኖሩባቸውን አጠፋለሁ ብሏል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እንደ ዓባይ ወንዝ የተነሣችውና ሞልቶ በጐርፉ ዳርቻውን ሁሉ እንደሚያጥለቀልቅ ወንዝ የሆነችው ግብጽ ነች፤ ግብጽ እንዲህ ብላለች ‘እኔ ተነሥቼ ዓለምን አጥለቀልቃለሁ። ከተሞችንና የሚኖሩባቸውን ሕዝብ ሁሉ እደመስሳለሁ።’

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ግብጽ እንደ ግብጽ ወንዝ ይነሳል ውኃውም እንደ ወንዙ ይናወጣል፥ እርሱም፦ እነሣለሁ ምድርንም ሁሉ እከድናለሁ፥ ከተሞችንና የሚኖሩባቸውን አጠፋለሁ ብሎአል።

Ver Capítulo Cópia de




ኤርምያስ 46:8
7 Referências Cruzadas  

እን​ዲ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በወ​ን​ዞች መካ​ከል የሚ​ተኛ፥ ወንዙ የእኔ ነው፤ ለራ​ሴም ሠር​ቼ​ዋ​ለሁ የሚል ታላቅ ዘንዶ የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖን ሆይ! እነሆ በአ​ንተ ላይ ነኝ።


“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈር​ዖን ሙሾ አሙሽ፤ እን​ዲ​ህም በለው፦ የአ​ሕ​ዛ​ብን አን​በሳ መስ​ለህ ነበር፤ ነገር ግን እንደ ባሕር ዘንዶ ሆነ​ሃል፤ ወን​ዞ​ች​ህ​ንም ወግ​ተ​ሃል፤ ውኃ​ው​ንም በእ​ግ​ርህ አደ​ፍ​ር​ሰ​ሃል፥ ወን​ዞ​ች​ህ​ንም በተ​ረ​ከ​ዝህ ረግ​ጠ​ሃል።


በውኑ ምድ​ሪቱ ስለ​ዚህ ነገር አት​ና​ወ​ጥ​ምን? በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ኖር ሁሉ አያ​ለ​ቅ​ስ​ምን? ጦር​ነት እንደ ወንዝ ይፈ​ስ​ሳል፤ እንደ ግብ​ፅም ወንዝ ይሞ​ላል፤ ደግ​ሞም ይወ​ር​ዳል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios