Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤርምያስ 46:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ብዛ​ታ​ቸ​ውም ደከመ፤ ወደ​ቀም፤ አን​ዱም አንዱ ለጓ​ደ​ኛው፦ ተነሥ፤ ከአ​ረ​ማ​ው​ያን ሰይፍ ፊት ወደ ወገ​ና​ችን ወደ ተወ​ለ​ድ​ን​ባት ምድር እን​መ​ለስ አለው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ደጋግመው ይሰናከላሉ፣ አንዱም በሌላው ላይ ይወድቃል፤ ‘ተነሡ እንሂድ፤ ወደ ሕዝባችንና ወደ ትውልድ አገራችን እንመለስ፤ ከጠላትም ሰይፍ እናምልጥ’ ይላሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እርሱም ብዙዎችን አሰነካከለ፥ እርሱም ደግሞ ወደቀ፤ እርስ በርሳቸውም፦ ተነሡ፥ የአስጨናቂው ሰው ከሆነው ሰይፍ ፊት ወደ ወገናችን ወደ ተወለድንባትም ምድር እንመለስ ተባባሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ጀሌዎቻቸው ተሰናክለው አንዱ በአንዱ ላይ ይወድቃሉ፤ እርስ በርሱም አንዱ ሌላውን፥ ‘ከጠላት ሰይፍ አምልጠን ከሀገራችን ሕዝብ መቀላቀል እንድንችል እንፍጠን’ ይለዋል።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ብዛታቸውም ተሰናከለ፥ ሰውም አንዱ በአንዱ ላይ ወደቀ፥ እነርሱም፦ ተነሡ፥ ከሚያስጨንቅ ሰይፍ ፊት ወደ ወገናችን ወደ ተወለድንባት ምድር እንመለስ አሉ።

Ver Capítulo Cópia de




ኤርምያስ 46:16
5 Referências Cruzadas  

በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ የተ​ቀ​ጠሩ ሠራ​ተ​ኞች በእ​ር​ስዋ ተቀ​ል​በው እንደ ሰቡ ወይ​ፈ​ኖች ናቸው፤ የጥ​ፋ​ታ​ቸው ቀንና የቅ​ጣ​ታ​ቸው ጊዜ መጥ​ቶ​ባ​ቸ​ዋ​ልና ተመ​ለሱ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ሸሹ፤ አል​ቆ​ሙ​ምም።


ፈጣ​ኑም አያ​መ​ል​ጥም፤ ኀያ​ሉም አይ​ድ​ንም፤ በሰ​ሜን በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ በኩል ደክ​መው ወደቁ።


ዘሪ​ው​ንና በመ​ከር ጊዜ ማጭድ የሚ​ይ​ዘ​ውን ከባ​ቢ​ሎን አጥፉ፤ ከአ​ረ​ማ​ዊው ሰይፍ ፊት የተ​ነሣ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ወገኑ ይመ​ለ​ሳል፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ ሀገሩ ይሸ​ሻል።


ባቢ​ሎ​ንን ፈወ​ስ​ናት፥ እር​ስዋ ግን አል​ተ​ፈ​ወ​ሰ​ችም፤ ፍር​ድዋ እስከ ሰማይ ደር​ሶ​አ​ልና፥ እስከ ከዋ​ክ​ብ​ትም ድረስ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና፥ እን​ተ​ዋት፤ ሁላ​ች​ንም ወደ ሀገ​ራ​ችን እን​ሂድ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios