Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤርምያስ 41:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የና​ታ​ንያ ልጅ እስ​ማ​ኤል ግን ከስ​ም​ንት ሰዎች ጋር ከዮ​ሐ​ናን አመ​ለጠ፥ ወደ አሞ​ንም ልጆች ሄደ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የናታንያ ልጅ እስማኤል ግን ዐብረውት ከነበሩት ስምንት ሰዎች ጋራ ከዮሐናን አመለጠ፤ ሸሽቶም ወደ አሞናውያን ገባ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የናታንያ ልጅ እስማኤል ግን ከስምንት ሰዎች ጋር ከዮሐናን አመለጠ ወደ አሞንም ልጆች ሄደ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እስማኤልና ስምንት ሰዎቹ ግን ከዮሐናን እጅ አምልጠው ወደ ዐሞን ምድር ኰበለሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የናታንያ ልጅ እስማኤል ግን ከስምንት ሰዎች ጋር ከዮሐናን አመለጠ ወደ አሞንም ልጆች ሄደ።

Ver Capítulo Cópia de




ኤርምያስ 41:15
9 Referências Cruzadas  

አክ​ዓ​ብም ኤል​ያ​ስን፥ “ጠላቴ ሆይ! አገ​ኘ​ኸ​ኝን?” አለው። እር​ሱም እን​ዲህ ብሎ መለ​ሰ​ለት፥ “አግ​ኝ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ታስ​ቈ​ጣው ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦


በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ግን የመ​ን​ግ​ሥት ዘር የነ​በረ የኤ​ል​ሴማ ልጅ የና​ታ​ንዩ ልጅ እስ​ማ​ኤል መጣ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ዐሥር ሰዎች ነበሩ፤ ጎዶ​ል​ያ​ንም መታው፤ ሞተም፤ ከእ​ር​ሱም ጋር በመ​ሴፋ የነ​በ​ሩ​ትን አይ​ሁ​ድ​ንና ከለ​ዳ​ው​ያ​ን​ንም ገደ​ላ​ቸው።


ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ክፉ ቀን ትጠ​ብ​ቀ​ዋ​ለች፤ በቍጣ ቀንም ይወ​ስ​ዱ​ታል።


እስ​ማ​ኤ​ልም ከመ​ሴፋ የማ​ረ​ካ​ቸው ሕዝብ ሁሉ ተመ​ል​ሰው ወደ ቃር​ሔም ልጅ ወደ ዮሐ​ናን ሔዱ።


የና​ታ​ን​ያም ልጅ እስ​ማ​ኤል ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ዐሥሩ ሰዎች ተነ​ሥ​ተው የሳ​ፋ​ንን ልጅ የአ​ኪ​ቃ​ምን ልጅ ጎዶ​ል​ያ​ስን በሰ​ይፍ መቱ፤ የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ በሀ​ገሩ ላይ የሾ​መ​ውን ገደሉ።


አረ​ማ​ው​ያ​ንም እፉ​ኝቱ በጳ​ው​ሎስ እጅ ላይ ተን​ጠ​ል​ጥላ ባዩ ጊዜ እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ይመ​ስ​ላል፤ ከባ​ሕር እንኳ በደ​ኅና ቢወ​ጣም በሕ​ይ​ወት ይኖር ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ አል​ተ​ወ​ውም” አሉ።


ዳዊ​ትም ሄዶ የአ​ጥ​ቢያ ኮከብ ከሚ​ወ​ጣ​በት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ዳግ​መ​ኛም በማ​ግ​ሥቱ መታ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በግ​መል ተቀ​ም​ጠው ከሸ​ሹት አራት መቶ ጐል​ማ​ሶች በቀር አን​ድም ያመ​ለጠ የለም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios