Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤርምያስ 33:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለም​ሽ​ግና ለመ​ከ​ላ​ከያ ስለ ፈረ​ሱት ስለ​ዚ​ህች ከተማ ቤቶች፥ ስለ ይሁ​ዳም ነገ​ሥ​ታት ቤቶች እን​ዲህ ይላ​ልና፦

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ከባቢሎናውያን ጋራ ባለው ውጊያ፣ ዐፈር በመደልደልና በሰይፍ የሚደረገውን ጥቃት ለመከላከል ስለ ፈረሱት ስለዚህች ከተማ ቤቶችና ስለ ይሁዳ ነገሥታት ቤተ መንግሥት እንዲህ ይላል፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከሰይፍ ፊትና ከከበባት የአፈር ድልድል ለመከላከል ስለ ፈረሱ ስለዚህች ከተማ ቤቶች፥ ስለ ይሁዳም ነገሥታት ቤቶች የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላልና፦

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በከበባውና በጦርነቱ ጥቃት ምክንያት የኢየሩሳሌም ቤቶችና የይሁዳ ቤተ መንግሥት ይፈራርሳሉ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለአፈር ድልድልና ለምሽግ ስለ ፈረሱ ስለዚህች ከተማ ቤቶች፥ ስለ ይሁዳም ነገሥታት ቤቶች እንዲህ ይላልና፦

Ver Capítulo Cópia de




ኤርምያስ 33:4
11 Referências Cruzadas  

የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ቤቶች ቈጠ​ራ​ችሁ፤ ቅጥ​ሩ​ንም ለማ​ጽ​ናት ቤቶ​ችን አፈ​ረ​ሳ​ችሁ።


በሕ​ዝቤ ምድር ላይ በእ​ር​ሻ​ቸ​ውም ላይ እሾ​ህና አሜ​ከላ ይበ​ቅ​ላሉ፤ ደስ​ታም ከቤ​ታ​ቸው ሁሉ ይጠ​ፋል።


የበ​ለ​ጸ​ገች ከተ​ማና ቤቶ​ችዋ ምድረ በዳ ይሆ​ናሉ። የከ​ተ​ማ​ውን ሀብ​ትና ያማሩ ቤቶ​ችን ይተ​ዋሉ፤ አን​ባ​ዎ​ችም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዋሻ፥ የም​ድረ በዳም አህያ ደስታ፥ የመ​ን​ጎ​ችም ማሰ​ማ​ሪያ ይሆ​ናሉ።


አሕ​ዛ​ብም መጥ​ተው ይህ​ችን ሀገር ያዟት፤ ይህ​ችም ከተማ ከረ​ኃ​ቡና ከጦሩ የተ​ነሣ በወ​ጓት በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሰዎች እጅ ወደ​ቀች፤ እንደ ተና​ገ​ር​ኸ​ውም ሆነ።


ኀያል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ዛፎ​ች​ዋን ቍረጡ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ላይ ኀይ​ልን አፍ​ስሱ ይህች ከተማ የሐ​ሰት ከተማ ናት፤ መካ​ከ​ልዋ ሁሉ ግፍ ብቻ ነው።


ዛይ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊ​ያ​ውን ጣለ፤ መቅ​ደ​ሱ​ንም ጠላው፤ የአ​ዳ​ራ​ሾ​ች​ዋ​ንም ቅጥር በጠ​ላት እጅ ሰበረ። እንደ ዓመት በዓል ቀን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ድም​ፃ​ቸ​ውን በዕ​ል​ልታ አሰሙ።


የቅ​ጥ​ሩን ማፍ​ረሻ ያደ​ርግ ዘንድ፥ አፍ​ንም በጩ​ኸት ይከ​ፍት ዘንድ፥ በው​ካ​ታም ድም​ፅን ከፍ ያደ​ርግ ዘንድ፥ የቅ​ጥ​ሩን ማፍ​ረሻ በበ​ሮች ላይ ያደ​ርግ ዘንድ፥ አፈ​ርን ይደ​ለ​ድል ዘንድ፥ ምሽ​ግም ይሠራ ዘንድ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ምዋ​ርት በቀኝ እጁ ውስጥ ነበረ።


እርሱ በም​ድረ በዳ ያሉ ሴቶች ልጆ​ች​ሽን በሰ​ይፍ ይገ​ድ​ላ​ቸ​ዋል፤ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ንም በአ​ንቺ ላይ ያስ​ቀ​ም​ጣል፤ በዙ​ሪ​ያ​ሽም ግንብ ይሠ​ራል፤ የጦር መሣ​ሪ​ያም ይዘው ይከ​ቡ​ሻል፤ በጦ​ራ​ቸ​ውም ይወ​ጉ​ሻል፤


በው​ስ​ጧም የሚ​ዋ​ጉ​በት ግን​ብን ሥራ፤ በሠ​ራ​ዊ​ትም ክበ​ባት፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ጦር አስ​ፍር፤ የሚ​ዋጋ ጦር​ንም ወደ አደ​ባ​ባ​ይዋ ላክ።


በነገሥታት ላይ ያላግጣሉ፥ መሳፍንትም ዋዛ ሆነውላቸዋል፣ በምሽጉ ሁሉ ይስቃሉ፥ አፈሩንም ከምረው ይወስዱታል።


ለመ​ብል የማ​ይ​ሆ​ኑ​ትን የም​ታ​ው​ቃ​ቸ​ውን ዛፎች ታጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ትቈ​ር​ጣ​ቸ​ው​ማ​ለህ፤ እስ​ክ​ታ​ሸ​ን​ፋ​ትም ድረስ በም​ት​ዋ​ጋህ ከተማ ላይ ምሽግ ትመ​ሽ​ጋ​ለህ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios