Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤርምያስ 33:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 በዙ​ፋኑ ላይ የሚ​ነ​ግሥ ልጅ እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ለት ከባ​ሪ​ያዬ ከዳ​ዊት ጋር፥ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ከሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ደግሞ ይፈ​ር​ሳል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በዚያ ጊዜ ከአገልጋዬ ከዳዊት ጋራ የገባሁትን ኪዳን፣ እንዲሁም በፊቴ በክህነት ከሚያገለግሉት ሌዋውያን ጋራ የገባሁትን ኪዳን ማፍረስ ይቻላል፤ ዳዊትም ከእንግዲህ በዙፋኑ ላይ የሚነግሥ ዘር አይኖረውም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በዙፋኑ ላይ የሚነግሥ ልጅ እንዳይሆንለት ከአገልጋዬ ከዳዊት ጋር፥ ከአገልጋዮቼም ከሌዋውያን ካህናት ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ደግሞ ይፈርሳል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በዙፋኑ ላይ የሚነግሥ ልጅ እንዳይሆንለት ከባሪያዬ ከዳዊት ጋር፥ ከአገልጋዮቼም ከሌዋውያን ካህናት ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ደግሞ ይፈርሳል።

Ver Capítulo Cópia de




ኤርምያስ 33:21
16 Referências Cruzadas  

በውኑ ቤቴ በኀ​ያሉ ዘንድ እን​ዲሁ አይ​ደ​ለ​ምን? ከእ​ኔም ጋር በዘ​መኑ ሁሉ የተ​ዘ​ጋ​ጀና የተ​ጠ​በቀ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል ኪዳን አድ​ር​ጎ​አል፤ መድ​ኀ​ኒ​ቴም ፈቃ​ዴም ሁሉ ይህ ነውና። ዐመ​ፀ​ኛም አይ​በ​ቅ​ል​ምና።


ነገር ግን ከዳ​ዊት ጋር ስላ​ደ​ረ​ገው ቃል ኪዳን፥ ለእ​ር​ሱና ለል​ጆ​ቹም በዘ​መ​ናት ሁሉ መብ​ራ​ትን ይሰ​ጠው ዘንድ ስለ ሰጠው ተስፋ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዳ​ዊ​ትን ቤት ያጠፋ ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም።


ከአ​ባ​ትህ ከዳ​ዊት ጋር፦ ‘በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ የሚ​ሆን ከዘ​ርህ አይ​ታ​ጣም’ ብዬ ቃል ኪዳን እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ የመ​ን​ግ​ሥ​ት​ህን ዙፋን አጸ​ና​ለሁ።


ስሙኝ፤ ጎዳ​ና​ዬን ተከ​ተሉ፤ አድ​ም​ጡ​ኝም፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁም በበ​ረ​ከት ትኖ​ራ​ለች፤ የታ​መ​ነ​ች​ዪ​ቱን የዳ​ዊ​ትን ምሕ​ረት፥ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምን ቃል ኪዳን ከእ​ና​ንተ ጋር አደ​ር​ጋ​ለሁ።


“እኔ የም​ሠ​ራ​ቸው አዲስ ሰማ​ይና አዲስ ምድር በፊቴ ጸን​ተው እን​ደ​ሚ​ኖሩ፥ እን​ዲሁ ዘራ​ች​ሁና ስማ​ችሁ ጸን​ተው ይኖ​ራሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ቀ​ርብ፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን የሚ​ያ​ቃ​ጥል፥ ሁል​ጊ​ዜም የሚ​ሠዋ ሰው ከሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት ዘንድ በእኔ ፊት አይ​ታ​ጣም።”


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios