Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤርምያስ 3:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እንደ ልቤም የሚ​ሆኑ ጠባ​ቂ​ዎ​ችን እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዕ​ው​ቀ​ትና በማ​ስ​ተ​ዋ​ልም ይጠ​ብ​ቁ​አ​ች​ኋል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እንደ ልቤም የሆኑ፣ በዕውቀትና በማስተዋል የሚመሯችሁን እረኞች እሰጣችኋለሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እንደ ልቤም የሆኑ እረኞችን እሰጣችኋለሁ፥ በእውቀትና በማስተዋልም ያሰማርዋችኋል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ለእኔ የሚታዘዙ ጠባቂዎችን እሰጣችኋለሁ፤ እነርሱም በጥበብና በማስተዋል ይመሩአችኋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እንደ ልቤም በግ ጠባቆችን እሰጣችኋለሁ፥ በእውቀትና በማስተዋልም ይጠብቁአችኋል።

Ver Capítulo Cópia de




ኤርምያስ 3:15
20 Referências Cruzadas  

የጻድቃን ከንፈሮች የሩቁን ያውቃሉ፤ ሰነፎች ግን በድህነት ይሞታሉ።


የሚ​ጠ​ብ​ቋ​ቸ​ውን እረ​ኞች አስ​ነ​ሣ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ዳግ​መ​ኛም አይ​ፈ​ሩም፤ አይ​ደ​ነ​ግ​ጡ​ምም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


አሕ​ዛብ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ በሩ​ቅም ላሉ ደሴ​ቶች አው​ሩና፥ “እስ​ራ​ኤ​ልን የበ​ተነ እርሱ ይሰ​በ​ስ​በ​ዋል፤ እረ​ኛም መን​ጋ​ውን እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቅ ይጠ​ብ​ቀ​ዋል በሉ።


“የሰው ልጅ ሆይ! ትን​ቢት ተና​ገር፤ በእ​ስ​ራ​ኤል እረ​ኞች ላይ ትን​ቢት ተና​ገር፤ እረ​ኞ​ች​ንም እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ራሳ​ቸ​ውን ለሚ​ያ​ሰ​ማሩ ለእ​ስ​ራ​ኤል እረ​ኞች ወዮ​ላ​ቸው! እረ​ኞች ራሳ​ቸ​ውን ያሰ​ማ​ራ​ሉን? እረ​ኞች በጎ​ችን ያሰ​ማሩ ዘንድ አይ​ገ​ባ​ቸ​ው​ምን?


በላ​ያ​ቸ​ውም አንድ እረኛ አቆ​ማ​ለሁ፤ እር​ሱም ያሰ​ማ​ራ​ቸ​ዋል፤ እር​ሱም ባሪ​ያዬ ዳዊት ነው፤ እረ​ኛም ይሆ​ና​ቸ​ዋል።


“ባሪ​ያ​ዬም ዳዊት በላ​ያ​ቸው ንጉሥ ይሆ​ናል፤ ለሁ​ሉም አንድ እረኛ ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ በፍ​ር​ዴም ይሄ​ዳሉ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ይጠ​ብ​ቃሉ፤ ያደ​ር​ጓ​ት​ማል።


ጌታ​ች​ንም እን​ዲህ አለው፥ “ምግ​ባ​ቸ​ውን በየ​ጊ​ዜው ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ጌታው በቤ​ተ​ሰቡ ላይ የሚ​ሾ​መው ደግ ታማ​ኝና ብልህ መጋቢ ማን ይሆን?


አሁ​ንም በገዛ ደሙ የዋ​ጃ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ትጠ​ብቁ ዘንድ መን​ፈስ ቅዱስ እና​ን​ተን ጳጳ​ሳት አድ​ርጎ ለሾ​መ​ባት ለመ​ን​ጋው ሁሉና ለራ​ሳ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ።


ለዐ​ዋ​ቆች ጥበ​ብን እን​ነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለን፤ ነገር ግን የዚ​ህን ዓለም ጥበብ ወይም ያልፉ ዘንድ ያላ​ቸ​ውን የዚ​ህን ዓለም ሹሞች ጥበብ አይ​ደ​ለም።


ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።


ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ ግን መን​ግ​ሥ​ትህ አይ​ጸ​ናም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ልቡ የሆነ ሰው መር​ጦ​አል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያዘ​ዘ​ህን አል​ጠ​በ​ቅ​ህ​ምና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝቡ ላይ ንጉ​ሥን ያነ​ግ​ሣል” አለው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios