Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤርምያስ 29:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አሔ​ል​ማ​ዊው ስለ ሸማያ እን​ዲህ ይላል ብለህ ወደ ምር​ኮ​ኞች ሁሉ ላክ፦ እኔ ሳል​ል​ከው ሸማያ ትን​ቢት ተና​ግ​ሮ​ላ​ች​ኋ​ልና፥ በሐ​ሰ​ትም እን​ድ​ት​ታ​መኑ አድ​ር​ጓ​ች​ኋ​ልና።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 “ይህን መልእክት በምርኮ ላሉት ሁሉ እንዲህ ብለህ ላክ፤ ‘ስለ ኔሔላማዊው ስለ ሸማያ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ እኔ ሳልልከው ሸማያ ትንቢት ተናግሮላችሁ፣ በሐሰት እንድትታመኑ አድርጓችኋልና፣

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 “ወደ ተማረኩት ሁሉ እንዲህ ብለህ ላክ፦ ‘ስለ ኔሔላማዊው ስለ ሸማያ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እኔ ሳልልከው ሸማያ ትንቢት ተናግሮላችኋልና፥ በሐሰትም እንድትታመኑ አድርጎአችኋልና፥

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 “እነሆ ተሰደው በባቢሎን ወደሚኖሩት ሁሉ ስለ ሽማዕያ የተነገረውን ይህን የትንቢት ቃል እንዲህ ብለህ ላክ፥ ‘ሽማዕያ እኔ ሳልከው የትንቢት ቃል በመናገር በውሸት እንድታምኑ አድርጓችኋል፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 እግዚአብሔር ስለ ኔሔላማዊው ስለ ሸማያ እንዲህ ይላል ብለህ ወደ ምርኮኞች ሁሉ ላክ፦ እኔ ሳልልከው ሸማያ ትንቢት ተናግሮላችኋልና፥ በሐሰትም እንድትታመኑ አድርጎአችኋልና

Ver Capítulo Cópia de




ኤርምያስ 29:31
11 Referências Cruzadas  

እር​ሱም፥ “እኔ ደግሞ እን​ዳ​ንተ ነቢይ ነኝ፤ መል​አ​ክም፦ እን​ጀራ ይበላ ዘንድ ውኃም ይጠጣ ዘንድ ከአ​ንተ ጋር ወደ ቤትህ መል​ሰው ብሎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ተና​ገ​ረኝ” አለው። ዋሽ​ቶም ተና​ገ​ረው።


“እኔ ሳል​ል​ካ​ቸው እነ​ዚህ ነቢ​ያት ሮጡ፤ እኔም ሳል​ነ​ግ​ራ​ቸው ትን​ቢ​ትን ተና​ገሩ።


ስለ​ዚህ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ባቢ​ሎን የሰ​ደ​ድ​ኋ​ችሁ ምር​ኮ​ኞች ሁሉ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


በስሜ ሐሰ​ተኛ ትን​ቢ​ትን ይና​ገ​ሩ​ላ​ች​ኋ​ልና፤ እኔም አል​ላ​ክ​ኋ​ቸ​ውም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ፤ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios