Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤርምያስ 25:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 በዚ​ያም ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግዳ​ዮች ከም​ድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆ​ናሉ፤ አይ​ለ​ቀ​ስ​ላ​ቸ​ውም፤ በም​ድር ላይ እንደ ጕድፍ ይሆ​ናሉ እንጂ አይ​ሰ​በ​ሰ​ቡም፤ አይ​ቀ​በ​ሩ​ምም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 በዚያ ጊዜ በእግዚአብሔር የተገደሉት ከምድር ዳር እስከ ምድር ዳር በሁሉ ስፍራ ተረፍርፈው ይታያሉ፤ እንደ ጕድፍ በምድር ላይ ይጣላሉ እንጂ፣ አይለቀስላቸውም፤ ሬሳቸውም አይሰበሰብም፤ አይቀበርምም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 በዚያም ቀን ጌታ የገደላቸው ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆናሉ፤ አይለቀስላቸውም፤ በምድር ላይ እንደ ጉድፍ ይሆናሉ እንጂ አይሰበሰቡም አይቀበሩምም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 በዚያን ቀን እግዚአብሔር በሞት የሚቀጣቸው ሰዎች ሬሳ ከምድር ዳርቻ እስከ ምድር ዳርቻ ይረፈረፋል፤ የሚያለቅስላቸውም ሆነ ሰብስቦ የሚቀብራቸው አያገኙም፤ ስለዚህ እንደ ጥራጊ በሜዳ ላይ ተጥለው ይቀራሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ግዳዮች ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆናሉ፥ አይለቀስላቸውም፥ በምድር ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ እንጂ አይከማቹም አይቀበሩምም።

Ver Capítulo Cópia de




ኤርምያስ 25:33
19 Referências Cruzadas  

የኤ​ል​ዛ​ቤ​ልም ሬሳ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል እርሻ መሬት ላይ እንደ ፍግ ይሆ​ና​ልና ማንም፦ ይህች ኤል​ዛ​ቤል ናት ይል ዘንድ አይ​ች​ልም ብሎ የተ​ና​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነው” አለ።


የኀ​ያ​ላን አም​ላክ፥ መል​ሰን፥ ፊት​ህ​ንም አብራ፥ እኛም እን​ድ​ና​ለን።


ከአ​እ​ላፍ ይልቅ በአ​ደ​ባ​ባ​ዮ​ችህ አን​ዲት ቀን ትሻ​ላ​ለች፤ በኃ​ጥ​ኣን ድን​ኳ​ኖች ከመ​ቀ​መጥ ይልቅ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እጣል ዘንድ መረ​ጥሁ።


ስለ​ዚህ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝቡ ላይ ታላቅ ቍጣን ተቈጣ፤ እጁ​ንም በላ​ያ​ቸው ዘር​ግቶ መት​ቶ​አ​ቸ​ዋል፤ ተራ​ሮ​ችም ተን​ቀ​ጠ​ቀጡ፤ ሬሳ​ቸ​ውም በመ​ን​ገድ መካ​ከል እንደ ጕድፍ ሆኖ​አል። በዚ​ህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።


ምድ​ርም ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሳት ሰውም ሁሉ በሰ​ይፉ ይፈ​ረ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተቀ​ሥ​ፈው የሞ​ቱት ይበ​ዛሉ።


በወ​ደ​ዱ​አ​ቸ​ውና በአ​መ​ለ​ኳ​ቸው፥ በተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውና በፈ​ለ​ጓ​ቸው፥ በሰ​ገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም በፀ​ሐ​ይና በጨ​ረቃ፥ በከ​ዋ​ክ​ብ​ትም፥ በሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ ፊት ይዘ​ረ​ጓ​ቸ​ዋል፤ አያ​ለ​ቅ​ሱ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ቀ​ብ​ሯ​ቸ​ው​ምም፤ በም​ድ​ርም ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆ​ናሉ።


በእ​ጁም ይይ​ዛት ዘንድ ለአ​ር​በኛ ተሰ​ጠች፤ ሰይፍ በገ​ዳይ እጅ እን​ድ​ት​ሰጥ ተሳ​ለ​ችና ተዘ​ጋ​ጀች።


በመ​ን​ጋ​ጋ​ዎ​ችህ መቃ​ጥን አገ​ባ​ብ​ሃ​ለሁ፤ የወ​ን​ዞ​ች​ህ​ንም ዓሦች ሁሉ ወደ ቅር​ፊ​ትህ አጣ​ብ​ቃ​ለሁ፤ ከወ​ን​ዞ​ች​ህም መካ​ከል አወ​ጣ​ሃ​ለሁ፤ የወ​ን​ዞ​ች​ህም ዓሦች ሁሉ ወደ ቅር​ፊ​ትህ ይጣ​በ​ቃሉ።


አን​ተ​ንና የወ​ን​ዞ​ች​ህን ዓሦች ሁሉ ወደ ምድረ በዳ እጥ​ላ​ለሁ፤ በም​ድ​ርም ፊት ላይ ትወ​ድ​ቃ​ለህ እንጂ አት​ከ​ማ​ችም፤ አት​ሰ​በ​ሰ​ብ​ምም፤ መብ​ልም አድ​ርጌ ለም​ድር አራ​ዊ​ትና ለሰ​ማይ ወፎች ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ።


እናንተም ኢትዮጵያውያን ደግሞ፥ በሰይፌ ትገደላላችሁ።


ከወገኖችና ከነገዶችም ከቋንቋዎችም ከአሕዛብም የሆኑ ሰዎች ሦስት ቀን ተኵል በድናቸውን ይመለከታሉ፤ በድናቸውም ወደ መቃብር ሊገባ አይፈቅዱም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios