Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤርምያስ 23:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነቢ​ያት ዘንድ ርኵ​ሰት በም​ድር ሁሉ ላይ ወጥ​ቶ​አ​ልና ሕማ​ምን አበ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ መራራ ውኃ​ንም አጠ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።”

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ስለዚህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ነቢያት እንዲህ ይላል፤ “ከኢየሩሳሌም ነቢያት፣ በምድሪቱ ሁሉ ርኩሰት ተሠራጭቷልና፤ መራራ ምግብ አበላቸዋለሁ፤ የተመረዘም ውሃ አጠጣቸዋለሁ።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ስለዚህ ስለ ነብያት የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ከኢየሩሳሌም ነቢያት ዘንድ ርኩሰት በምድር ሁሉ ላይ ወጥቶአልና፥ እሬትን አበላቸዋለሁ የሐሞትንም ውኃ አጠጣቸዋለሁ።”

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 “እንግዲህ እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኢየሩሳሌም ነቢያት የምለው ይህ ነው፦ ‘በምድሪቱ ሁሉ ላይ የክሕደትን መንፈስ ስላሠራጩ፥ መራራ ቅጠል እንዲበሉና መርዝ እንዲጠጡ አደርጋቸዋለሁ።’ ”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ከኢየሩሳሌም ነቢያት ዘንድ ርኵሰት በምድር ሁሉ ላይ ወጥቶአልና እሬትን አበላቸዋለሁ የሐሞትንም ውኃ አጠጣቸዋለሁ።

Ver Capítulo Cópia de




ኤርምያስ 23:15
12 Referências Cruzadas  

ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በስሜ የሐ​ሰት ትን​ቢት ስለ​ሚ​ና​ገሩ ነቢ​ያት ስላ​ላ​ክ​ኋ​ቸው፦ በዚ​ህች ሀገር ሰይ​ፍና ረሃብ አይ​ሆ​ንም ስለ​ሚሉ ነቢ​ያት እን​ዲህ ይላል፥ “እነ​ዚያ ነቢ​ያት በሰ​ይ​ፍና በራብ ይጠ​ፋሉ።


“ዝም ብለን ለምን እን​ቀ​መ​ጣ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ በደ​ልን አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አጥ​ፍ​ቶ​ና​ልና፥ የሐ​ሞ​ት​ንም ውኃ አጠ​ጥ​ቶ​ና​ልና ተሰ​ብ​ስ​ባ​ችሁ ወደ ተመ​ሸጉ ከተ​ሞች እን​ግባ በዚ​ያም እን​ጥፋ።


ነገር ግን የል​ባ​ቸ​ውን ምኞ​ትና አባ​ቶ​ቻ​ቸው ያስ​ተ​ማ​ሩ​አ​ቸ​ውን ጣዖት ተከ​ት​ለ​ዋል፤


ስለ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ፥ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ይህን ሕዝብ መከ​ራን አበ​ላ​ዋ​ለሁ፤ የሐ​ሞ​ት​ንም ውኃ አጠ​ጣ​ዋ​ለሁ።


ምሬ​ትን አጠ​ገ​በኝ፤ በሐ​ሞ​ትም አሰ​ከ​ረኝ።


ዛይ። ስደ​ቴ​ንና ችግ​ሬን፥ እሬ​ት​ንና ሐሞ​ትን አስብ።


በዙ​ሪ​ያዬ ቅጥር ሠራ​ብኝ፤ የመ​ከ​ራ​ው​ንም ጎዳና በእኔ ላይ አቀና።


በዚያ ቀን፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ የጣዖታትን ስም ከምድር አጠፋለሁ፥ ከዚያም በኋላ አይታሰቡም፣ ደግሞም ሐሰተኞችን ነቢያትና ርኩስ መንፈስን ከምድር ላይ አስወግዳለሁ።


በሐሞት የተደባለቀ የወይን ጠጅ ሊጠጣ አቀረቡለት፤ ቀምሶም ሊጠጣው አልወደደም።


ሄዶ የእ​ነ​ዚ​ያን አሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ያመ​ልክ ዘንድ ከአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቡን ዛሬ የሚ​ያ​ስት ወንድ ወይም ሴት ወይም ወገን ወይም ነገድ አይ​ኑ​ር​ባ​ችሁ፤ ሐሞ​ትና እሬ​ትም የሚ​ያ​በ​ቅል ሥር አይ​ሁ​ን​ባ​ችሁ።


የኮከቡም ስም እሬቶ ይባላል፤ የውሃውም ሲሶ መራራ ሆነ፤ መራራም ስለተደረገ በውሃው ጠንቅ ብዙ ሰዎች ሞቱ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios