Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤርምያስ 19:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ይህ​ች​ንም ከተማ ለጥ​ፋ​ትና ለማ​ፍ​ዋጫ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ያ​ልፍ ሁሉ ስለ ተደ​ረ​ገ​ባት መቅ​ሠ​ፍት ሁሉ ይደ​ነ​ግ​ጣል፤ ያፍ​ዋ​ጫ​ልም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ይህችን ከተማ ድምጥማጧን አጠፋለሁ፤ የድንጋጤና መሣለቂያም ምልክት አደርጋታለሁ፤ በዚያም የሚያልፉ ሁሉ ከቍስሎቿም የተነሣ ወይ ጉድ! ይላሉ፣ ያሾፋሉም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ይህችንም ከተማ ለመሣቀቂና ለማፍዋጫ አደርጋታለሁ፤ የሚያልፍባትም ሁሉ ይሣቀቃል፥ ስለ ተደረገባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጭባታል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ይህችን ከተማ የፍርስራሽ ክምር አደርጋታለሁ፤ በዚያ በኩል የሚያልፍ ሁሉ ይደነግጣል፤ በደረሰባት ችግርም ይገረማል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ይህችንም ከተማ ለመደነቂያና ለማፍዋጫ አደርጋታለሁ፥ የሚያልፍባትም ሁሉ ስለ ተደረገባት መቅሠፍት ሁሉ ይደነቃል ከንፈሩንም ይመጥጣል።

Ver Capítulo Cópia de




ኤርምያስ 19:8
14 Referências Cruzadas  

ከፍ ከፍ ብሎ የነ​በ​ረ​ውም ይህ ቤት ባድማ ይሆ​ናል፤ በዚ​ያም የሚ​ያ​ልፍ ሁሉ እያ​ፍ​ዋጨ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ሀገ​ርና በዚህ ቤት ስለ ምን እን​ዲህ አደ​ረገ? ብሎ ይደ​ነ​ቃል።


ምድ​ራ​ቸ​ውን ለጥ​ፋ​ትና ለዘ​ለ​ዓ​ለም ማፍ​ዋጫ አድ​ር​ገ​ዋል፤ የሚ​ያ​ል​ፍ​ባት ሁሉ ይደ​ነ​ቃል፤ ራሱ​ንም ያነ​ቃ​ን​ቃል።


ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ፈጽሞ ምድረ በዳ ይሆኑ ዘንድ፥ ለር​ግ​ማ​ንም አደ​ር​ጋ​ቸው ዘንድ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንና የይ​ሁ​ዳን ከተ​ሞች፥ ነገ​ሥ​ታ​ቷ​ንም፥ አለ​ቆ​ች​ዋ​ንም አጠ​ጣ​ኋ​ቸው።


ባሶራ ምድረ በዳ፥ መሰ​ደ​ቢ​ያና መረ​ገ​ሚ​ያም እን​ድ​ት​ሆን በራሴ ምያ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከተ​ሞ​ች​ዋም ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ባድማ ይሆ​ናሉ።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ የተ​ነሣ ባድማ ትሆ​ና​ለች እንጂ ሰው አይ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም፤ በባ​ቢ​ሎ​ንም በኩል የሚ​ያ​ልፍ ሁሉ ይደ​ነ​ቃል፤ በመ​ጣ​ባ​ትም መቅ​ሠ​ፍት ሁሉ ያፍ​ዋ​ጫል።


የአ​ሕ​ዛብ ነጋ​ዴ​ዎ​ችም አፍ​ዋ​ጩ​ብሽ፤ አን​ቺም ፈጽ​መሽ ትጠ​ፊ​ያ​ለሽ፤ ከእ​ግ​ዲ​ህም ወዲያ እስከ ዘለ​ዓ​ለም አት​ኖ​ሪም።”


ምድ​ሪ​ቱ​ንም የተ​ፈ​ታች አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባት ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ከእ​ር​ስዋ የተ​ነሣ ይደ​ነ​ቃሉ።


አንተን ለጥፋት፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ለማፍዋጫ እሰጥ ዘንድ የዘንበሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቃችኋል፥ በምክራቸውም ሄዳችኋል፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።


ተዘልላ የተቀመጠች፥ በልብዋም፦ እኔ ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለም ያለች ደስተኛይቱ ከተማ ይህች ናት፣ አራዊት የሚመሰጉባት ባድማ እንዴት ሆነች! በእርስዋ በኩል የሚያልፈው ሁሉ እጁን እያወዛወዘ ያፍዋጫል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ እነ​ርሱ በሚ​ወ​ስ​ድህ አሕ​ዛብ መካ​ከል ሁሉ የደ​ነ​ገ​ጥህ፥ ለም​ሳ​ሌና ለተ​ረ​ትም ትሆ​ና​ለህ።


“ከዚ​ያም በኋላ የሚ​ነሣ ትው​ልድ፥ ከእ​ና​ን​ተም በኋላ የሚ​ሆኑ ልጆ​ቻ​ችሁ ከሩቅ ሀገ​ርም የሚ​መጣ እን​ግዳ፥ የዚ​ችን ሀገር መቅ​ሠ​ፍት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በላ​ይዋ የላ​ከ​ውን ሥቃ​ይ​ዋን፥


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios