Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤርምያስ 10:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በአ​ንድ ጊዜ ሰን​ፈ​ዋል፥ ደን​ቍ​ረ​ው​ማል፤ ጣዖ​ታት የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩት የእ​ን​ጨት ነገር ብቻ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከከንቱ የዕንጨት ጣዖት ትምህርት የሚቀሥሙ ሁሉ፣ ጅሎችና ሞኞች ናቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በአንድ ጊዜ ቂላ ቂሎችና ሞኞች ሆነዋል፤ ጣዖታት የሚያስተምሩት ከግዑዝ እንጨት የማይሻልን ነገር ብቻ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ሁሉም ሞኞችና አላዋቂዎች ሆነው ነው እንጂ ከእንጨት ከተሠሩ ምስሎች ከቶ ምን ትምህርት ማግኘት ይችላሉ?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በአንድ ጊዜ ሰንፈዋል፥ ደንቍረውማል፥ ጣዖታት የሚያስተምሩት የእንጨት ነገር ብቻ ነው።

Ver Capítulo Cópia de




ኤርምያስ 10:8
16 Referências Cruzadas  

ለአ​ንተ የም​ስ​ጋና መሥ​ዋ​ዕ​ትን እሠ​ዋ​ለሁ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም እጠ​ራ​ለሁ።


ጽኑ​ዓን ነገ​ሥ​ታ​ትን የገ​ደለ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


የሚ​ሠ​ሩ​አ​ቸ​ውም በከ​ንቱ ይሠ​ሩ​አ​ቸ​ዋል።


አያ​ው​ቁም፤ አያ​ስ​ቡም፤ እን​ዳ​ያዩ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው፥ እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ው​ሉም ልቦ​ቻ​ቸው ተጋ​ር​ደ​ዋል።


ማንም በልቡ አያ​ስ​ብም፥ “ግማ​ሽ​ዋን በእ​ሳት አቃ​ጥ​ያ​ለሁ፤ በፍ​ም​ዋም ላይ እን​ጀ​ራን ጋግ​ሬ​አ​ለሁ፤ ሥጋም ጠብሼ በል​ቻ​ለሁ፤ የቀ​ረ​ው​ንም አስ​ጸ​ያፊ ነገር አደ​ር​ጋ​ለ​ሁን? ለዛ​ፍስ ግንድ እሰ​ግ​ዳ​ለ​ሁን? እን​ዲ​ልም ዕው​ቀ​ትና ማስ​ተ​ዋል የለ​ውም።


ሰው ሁሉ ዕው​ቀት አጥቶ ሰን​ፎ​አል፤ አን​ጥ​ረ​ኛም ሁሉ ከቀ​ረ​ጸው ምስል የተ​ነሣ አፍ​ሮ​አል፤ ቀልጦ የተ​ሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስ​ት​ን​ፋ​ስም የለ​ው​ምና።


ግን​ዱን፥ “አንተ አባቴ ነህ፤ ድን​ጋ​ዩ​ንም፦ አንተ ወለ​ድ​ኸኝ” ይላሉ፤ ፊታ​ቸ​ው​ንም ሳይ​ሆን ጀር​ባ​ቸ​ውን ሰጡኝ፤ በመ​ከ​ራ​ቸው ጊዜ ግን፥ “ተነ​ሥ​ተህ አድ​ነን ይላሉ።


ዝሙ​ቷም ከንቱ ሆነ፤ እር​ስ​ዋም ከድ​ን​ጋ​ይና ከግ​ንድ ጋር አመ​ነ​ዘ​ረች።


የሕ​ዝቤ አለ​ቆች አላ​ወ​ቁ​ኝም፤ እነ​ርሱ ሰነ​ፎች ልጆች ናቸው፤ ማስ​ተ​ዋ​ልም የላ​ቸ​ውም፤ ክፉ ነገ​ርን ለማ​ድ​ረግ ብል​ሃ​ተ​ኞች ናቸው፤ በጎ ነገ​ርን ማድ​ረግ ግን አያ​ው​ቁም።


እኔም እን​ዲህ አልሁ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገ​ድና የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን ፍርድ አላ​ወ​ቁ​ምና እነ​ዚህ በእ​ው​ነት ድሆ​ችና ደካ​ሞች ናቸው፤


ሕዝቤ በዝ​ሙት መን​ፈስ ስተ​ዋ​ልና ከአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውም ርቀው አመ​ን​ዝ​ረ​ዋ​ልና በት​ርን ይጠ​ይ​ቃሉ፤ በት​ሩም ይመ​ል​ስ​ላ​ቸ​ዋል።


ነፍሴ በዛ​ለ​ች​ብኝ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አሰ​ብ​ሁት፤ ጸሎ​ቴም ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅ​ደ​ስህ ትግባ።


የተቀረጸውን ምስል ሠሪው የቀረጸው ለምን ጥቅም ነው? ዲዳንም ጣዖት ይሠራ ዘንድ ሠሪው የታመነበቱ፥ ሐሰትን የሚያስተምር ቀልጦ የተሠራ ምን ይጠቅማል?


ተራፊም ከንቱነትን ተናግረዋልና፥ ምዋርተኞችም ውሸትን አይተዋልና፣ ሕልምንም የሚያዩ በሐሰት ተናግረዋል፥ በከንቱም ያጽናናሉ፣ እረኛም የላቸውምና እንደ በጎች ተቅበዝብዘዋል ተጨንቀውማል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios