Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኤርምያስ 10:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ድን​ኳ​ኔም ተበ​ዘ​በዘ፤ አው​ታ​ሬም ሁሉ ተቈ​ረጠ፤ ልጆ​ችና በጎ​ችም የሉም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ለድ​ን​ኳ​ኔም ቦታ የለም ለመ​ን​ጎ​ችም መሰ​ማ​ሪያ የለም፤

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ድንኳኔ ፈርሷል፤ ገመዶቹም ሁሉ ተበጣጥሰዋል፤ ልጆቼ ጥለውኝ ሄደዋል፤ ከእንግዲህም አይመለሱም፤ ድንኳኔን ለመትከል፣ መጋረጃዬንም ለመዘርጋት ማንም የቀረ የለም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ድንኳኔ ተበዘበዘ አውታሬም ሁሉ ተቈረጠ፤ ልጆቼም ከእኔ ወጥተው አይገኙም፤ ድንኳኔንም ከእንግዲህ ወዲህ የሚዘረጋ መጋረጃዎችንም የሚያነሣ የለም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ድንኳኖቻችን ፈራረሱ፤ መወጠሪያ ገመዶችም ተቈራረጡ፤ ልጆቻችን በሙሉ ተሰደው ስለ ሄዱ፥ ድንኳኖቻችንን መልሶ የሚተክልልንና መጋረጃዎቻችንን የሚሰቅልልን አንድ እንኳ አልቀረም።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ድንኳኔ ተበዘበዘ አውታሬም ሁሉ ተቈረጠ፥ ልጆቼም ከእኔ ወጥተው አይገኙም፥ ድንኳኔንም ከእንግዲህ ወዲህ የሚዘረጋ መጋረጃዎችንም የሚያነሣ የለም።

Ver Capítulo Cópia de




ኤርምያስ 10:20
12 Referências Cruzadas  

የሚ​ያ​የኝ ሰው ዐይን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አያ​የ​ኝም፤ ዐይ​ንህ በእኔ ላይ ይሆ​ናል፤ እኔም አል​ገ​ኝም።


ኀጢአተኛ በተገለበጠበት ይጠፋል፥ የጻድቃን ቤቶች ግን ጸንተው ይኖራሉ።


ቃሌን በአ​ፍሽ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ሰማ​ይን በዘ​ረ​ጋ​ሁ​በ​ትና ምድ​ርን በመ​ሠ​ረ​ት​ሁ​በት በእጄ ጥላ እጋ​ር​ድ​ሻ​ለሁ፤ ጽዮ​ን​ንም አንቺ ሕዝቤ ነሽ እላ​ታ​ለሁ።


ከወ​ለ​ድ​ሻ​ቸው ልጆ​ችሽ ሁሉ የሚ​ያ​ረ​ጋ​ጋሽ አጣሽ፤ ከአ​ሳ​ደ​ግ​ሻ​ቸ​ውም ልጆ​ችሽ ሁሉ እጁን ሰጥቶ የሚ​ያ​ነ​ሣሽ የለም።


የድ​ን​ኳ​ን​ሽን ስፍራ አስፊ፤ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ች​ሽ​ንም ዘርጊ፤ አት​ቈ​ጥቢ፤ አው​ታ​ሮ​ች​ሽን አስ​ረ​ዝሚ፤ ካስ​ሞ​ች​ሽ​ንም ትከዪ።


እኔ ከክፉ ቍስ​ልሽ እፈ​ው​ስ​ሻ​ለሁ፤ ጤና​ሽን እመ​ል​ስ​ል​ሻ​ለሁ፤ ቍስ​ል​ሽ​ንም እፈ​ው​ሳ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ማንም የማ​ይ​ሻት፥ የተ​ጣ​ለች ጽዮን ብለው ጠር​ተ​ው​ሻ​ልና።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የኀ​ዘን፥ የል​ቅ​ሶና የጩ​ኸት ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆ​ችዋ አለ​ቀ​ሰች፤ የሉ​ምና ስለ ልጆ​ችዋ መጽ​ና​ና​ትን እንቢ አለች።


መከራ በመ​ከራ ላይ ተጠ​ር​ቶ​አል፤ ምድር ሁሉ ተዋ​ር​ዳ​ለ​ችና፤ በድ​ን​ገ​ትም ድን​ኳኔ ጠፋ፤ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ችም ተቀ​ዳ​ደዱ።


ሄ። ስለ ኀጢ​አቷ ብዛት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዋ​ር​ዶ​አ​ታ​ልና የሚ​ዘ​ባ​በ​ቱ​ባት በራ​ስዋ ላይ ሆኑ፤ ጠላ​ቶ​ች​ዋም ተደ​ሰቱ፤ ሕፃ​ና​ቶ​ች​ዋም በአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች ፊት ተማ​ር​ከ​ዋል።


የሕዝቤንም ሴቶች ከተሸለሙ ቤቶቻቸው አሳደዳችኋቸው፥ ከሕፃናቶቻቸውም ክብሬን ለዘላለም ወሰዳችሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios