Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 9:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በም​ድ​ያም ጊዜ እንደ ሆነ በላ​ያ​ቸው የነ​በ​ረው ቀን​በር ተነ​ሥ​ቶ​አ​ልና፥ በጫ​ን​ቃ​ቸው የነ​በ​ረ​ው​ንም፥ የአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ዎ​ች​ንም በትር መል​ሶ​አ​ልና።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ምድያም ድል በተመታ ጊዜ እንደ ሆነው፣ የከበዳቸውን ቀንበር፣ በትከሻቸው ላይ የነበረውን በትር፣ የተጨቈኑበትንም ዘንግ ሰብረህላቸዋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የጦረኞች ጫማ ሁሉ፤ በደም የተለወሰ ልብስም ሁሉ፤ ለእሳት ይዳረጋል፤ ይማገዳልም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በቀድሞ ዘመን ምድያማውያንን ድል እንዳደረግህ ሁሉ፥ አሁንም በሕዝብህ ላይ የተጫነውን የአገዛዝ ቀንበርና በትከሻቸው ላይ የተቃጣውን በትር ሰባበርክ፤ ሕዝብህን በማስጨነቅ ይገዛ የነበረውን ድል አደረግህ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በምድያም ጊዜ እንደሆነ የሸክሙን ቀንበር የጫንቃውንም በትር ያስጨናቂውንም ዘንግ ሰብረሃል።

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 9:4
24 Referências Cruzadas  

በሰ​ይ​ፍ​ህም ትኖ​ራ​ለህ፤ ለወ​ን​ድ​ም​ህም ትገ​ዛ​ለህ፤ ነገር ግን ቀን​በ​ሩን ከአ​ን​ገ​ትህ ልት​ጥል ብት​ወ​ድድ ከእ​ርሱ ጋር ተስ​ማማ።”


ደስ​ተ​ኞ​ችም ሆን።


እኔ ግን እላ​ለሁ፥ “አማ​ል​ክት ናችሁ፥ ሁላ​ች​ሁም የል​ዑል ልጆች ናችሁ፤”


ስለ​ዚ​ህም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በክ​ብ​ርህ ላይ ውር​ደ​ትን፥ በጌ​ጥህ ላይም የሚ​ነ​ድና የሚ​ያ​ቃ​ጥል እሳ​ትን ይሰ​ድ​ዳል።


ለቍ​ጣዬ በትር ለሆኑ፥ ለመ​ዓ​ቴም ጨን​ገር በእ​ጃ​ቸው ላለ ለአ​ሦ​ራ​ው​ያን ወዮ​ላ​ቸው!


አሦ​ርን በም​ድሬ ላይ እሰ​ብ​ረ​ዋ​ለሁ፤ በተ​ራ​ራ​ዬም ላይ እረ​ግ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ ቀን​በ​ሩም ከእ​ነ​ርሱ ላይ ይነ​ሣል፤ ሸክ​ሙም ከጫ​ን​ቃ​ቸው ላይ ይወ​ገ​ዳል።”


ከሚ​ከ​ቧ​ችሁ ጋር ጠላ​ቶች እን​ዳ​ይ​ሆ​ኗ​ችሁ ከሞ​ዓብ የተ​ሰ​ደ​ዱ​ትን ከእ​ና​ንተ ጋር አታ​ስ​ቀ​ምጡ፤ ሰል​ፈ​ኞች አል​ቀ​ዋ​ልና፤ በሀ​ገ​ሪቱ ሁሉ የነ​በ​ረ​ውም አለቃ ጠፍ​ቶ​አ​ልና።


በሕ​ዝቤ ላይ ተቈ​ጥቼ ነበር፤ ርስ​ቴ​ንም አረ​ከ​ስሽ፤ በእ​ጅ​ሽም አሳ​ልፌ ሰጠ​ኋ​ቸው፤ ለሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸው አል​ራ​ራ​ሽም፤ ቀን​በ​ራ​ቸ​ው​ንም እጅግ አክ​ብ​ደ​ሻል።


የአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ዎ​ች​ሽ​ንም ሥጋ​ቸ​ውን ይበ​ላሉ፤ እንደ ጣፋጭ ወይን ጠጅም ደማ​ቸ​ውን ጠጥ​ተው ይሰ​ክ​ራሉ፤ ሥጋ ለባ​ሹም ሁሉ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መድ​ኀ​ኒ​ት​ሽና ታዳ​ጊሽ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብን ኀይል የም​ደ​ግፍ እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”


አንቺ ግን ሰማ​ያ​ትን የፈ​ጠ​ረ​ውን፥ ምድ​ር​ንም የመ​ሠ​ረ​ታ​ትን ፈጣ​ሪ​ሽን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረስ​ተ​ሻል፤ ያጠ​ፋሽ ዘንድ ባዘ​ጋጀ ጊዜ ከአ​ስ​ጨ​ና​ቂው ቍጣ የተ​ነሣ ሁል​ጊዜ ቀኑን ሁሉ ፈር​ተ​ሻል፤ ይቈ​ጣሽ ዘንድ መክ​ሮ​አ​ልና፤ አሁን የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቅሽ ቍጣው የት አለ?


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ትቢ​ያን አራ​ግፊ፤ ተነሺ፥ ተቀ​መጪ፤ ምር​ኮ​ኛ​ዪቱ የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ የአ​ን​ገ​ት​ሽን እስ​ራት ፍቺ።


እነሆ፥ በጽ​ድቅ ትታ​ነ​ጺ​ያ​ለሽ፤ ከግፍ ራቂ፤ አት​ፈ​ሪም፤ ድን​ጋ​ጤም ወደ አንቺ አይ​ቀ​ር​ብም።


በደም የተ​ለ​ወሰ ልብስ በእ​ሳት ከሚ​ቃ​ጠል በቀር ለም​ንም አይ​ጠ​ቅ​ምም።


በዚያ ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ቀን​በ​ርን ከአ​ን​ገ​ትህ እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ እስ​ራ​ት​ህ​ንም እበ​ጥ​ሳ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ለሌላ አት​ገ​ዛም።


በዙ​ሪ​ያው ያላ​ችሁ ሁሉ ስሙ​ንም የም​ታ​ውቁ ሁሉ፦ ታላቁ በትር፥ ጠን​ካ​ራ​ውም ሽመል፥ እን​ዴት ተሰ​በረ! ብላ​ችሁ አል​ቅ​ሱ​ለት።


ባሪ​ያ​ዎች ከነ​በ​ራ​ች​ሁ​በት ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኋ​ችሁ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ፤ የባ​ር​ነ​ታ​ች​ሁን ቀን​በር ሰብ​ሬ​አ​ለሁ፤ በግ​ል​ጽም አወ​ጣ​ኋ​ችሁ።


አሁንም ቀንበሩን ከአንተ እሰብራለሁ፥ እስራትህንም እበጥሳለሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios