Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 9:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ተራራ ላይ እር​ሱን በመ​ቃ​ወም የሚ​ነ​ሡ​ትን ይበ​ት​ና​ቸ​ዋል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ነገር ግን እግዚአብሔር የረአሶንን ጠላቶች አጠንክሯል፤ በርሱም ላይ ባላጋራዎቹን ያነሣሣበታል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሶርያውያን ከምሥራቅ፤ ፍልስጥኤማውያን ከምዕራብ፤ አፋቸውን ከፍተው እስራኤልን ይቦጫጭቋታል። ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም፤ እጁ እንደ ተዘረጋ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ስለዚህ እግዚአብሔር ተቀናቃኞችን በእነርሱ ላይ ያስነሣባቸዋል፤ ጠላቶቻቸውንም በእነርሱ ላይ ያነሣሣባቸዋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ስለዚህ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ ላይ ተቋቋሚ ያስነሳበታል፥

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 9:11
10 Referências Cruzadas  

በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በፋ​ቁሔ ዘመን የአ​ሶር ንጉሥ ቴል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶር መጣ፤ ኢዮ​ንና አቤ​ል​ቤ​ት​መ​ዓ​ካን፥ ያኖ​ዋ​ንም፥ ቃዴ​ስ​ንና አሶ​ር​ንም፥ ገለ​ዓ​ድ​ንና ገሊ​ላ​ንም፥ የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶ​ርም አፈ​ለ​ሳ​ቸው።


የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ሰማው፤ የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ወደ ደማ​ስቆ ወጣ፤ ያዛ​ትም፤ ሕዝ​ብ​ዋ​ንም ወደ ቂር አፈ​ለ​ሳ​ቸው፤ ረአ​ሶ​ን​ንም ገደ​ለው።


በሐ​ሣር እን​ዳ​ት​ወ​ድቁ፥ ክብ​ራ​ች​ሁን ወዴት ትተ​ዉ​ታ​ላ​ችሁ? በዚ​ህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።


ለኤ​ፍ​ሬም ምን​ደ​ኞች ትዕ​ቢት አክ​ሊል፥ ያለ ወይን ጠጅ ለሰ​ከሩ፥ በወ​ፍ​ራም ተራራ ራስ ላይ ላለ​ችም ለረ​ገ​ፈች ለክ​ብር ጌጥ አበባ ወዮ!


ስለ​ዚህ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝቡ ላይ ታላቅ ቍጣን ተቈጣ፤ እጁ​ንም በላ​ያ​ቸው ዘር​ግቶ መት​ቶ​አ​ቸ​ዋል፤ ተራ​ሮ​ችም ተን​ቀ​ጠ​ቀጡ፤ ሬሳ​ቸ​ውም በመ​ን​ገድ መካ​ከል እንደ ጕድፍ ሆኖ​አል። በዚ​ህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በይ​ሁዳ ንጉሥ በዖ​ዝ​ያን ልጅ በኢ​ዮ​አ​ታም ልጅ በአ​ካዝ ዘመን የአ​ራም ንጉሥ ረአ​ሶን፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ የሮ​ሜ​ልዩ ልጅ ፋቁሔ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ሊወጉ ወጡ፤ ሊይ​ዙ​አ​ትም አል​ቻ​ሉም።


የአ​ራም ራስ ደማ​ስቆ ነው፤ የደ​ማ​ስ​ቆም ራስ ረአ​ሶን ነው፤ በስ​ድሳ አም​ስት ዓመት ውስጥ የኤ​ፍ​ሬም መን​ግ​ሥት ከሕ​ዝብ ይጠ​ፋል፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios