Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 9:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የዚ​ህም ጊዜው እስ​ከ​ሚ​ደ​ርስ የተ​ቸ​ገ​ረው ሁሉ አያ​መ​ል​ጥም፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዘመን የዛ​ብ​ሎ​ን​ንና የን​ፍ​ታ​ሌ​ምን ምድር አቃ​ለለ፤ በኋ​ለ​ኛው ዘመን ግን በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በባ​ሕር መን​ገድ ያለ​ውን የአ​ሕ​ዛ​ብን ገሊላ ያከ​ብ​ራል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ነገር ግን ተጨንቀው የነበሩ ከእንግዲህ ተስፋ ቢስ አይሆኑም። በቀደመው ዘመን የዛብሎንንና የንፍታሌምን ምድር አዋረደ፤ በሚመጣው ዘመን ግን ከዮርዳኖስ ማዶ፣ በባሕር መንገድ አጠገብ ያለውን የአሕዛብን ገሊላ ያከብራል፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በጨለማ የሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ ምድር ለኖሩትም ብርሃን ወጣላቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እነዚያ የተሠቃዩት ግን ዳግመኛ ችግር አይደርስባቸውም። በቀድሞ ዘመን የዛብሎንና የንፍታሌም ምድር ተዋርዳ ትኖር ነበር፤ በኋለኛው ዘመን ግን ከሜዲቴራኒያን ባሕር ምሥራቅ ጀምሮ እስከ ዮርዳኖስ ማዶ ያለው በተለይም አሕዛብ ሰፍረውበት የነበረው የገሊላ ምድር ክብርን ይጐናጸፋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ነገር ግን ተጨንቃ ለነበረች ጨለማ አይሆንም። በመጀመሪያው ዘመን የዛብሎንንና የንፍታሌምን ምድር አቃለለ፥ በኋለኛው ዘመን ግን የዮርዳኖስ ማዶ በባሕር መንገድ ያለውን የአሕዛብን ገሊላ ያከብራል።

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 9:1
10 Referências Cruzadas  

በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በፋ​ቁሔ ዘመን የአ​ሶር ንጉሥ ቴል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶር መጣ፤ ኢዮ​ንና አቤ​ል​ቤ​ት​መ​ዓ​ካን፥ ያኖ​ዋ​ንም፥ ቃዴ​ስ​ንና አሶ​ር​ንም፥ ገለ​ዓ​ድ​ንና ገሊ​ላ​ንም፥ የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶ​ርም አፈ​ለ​ሳ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ የአ​ሦ​ርን ንጉሥ የፋ​ሎ​ክን መን​ፈስ፥ የአ​ሦ​ር​ንም ንጉሥ የቴ​ል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶ​ርን መን​ፈስ አስ​ነሣ፤ የሮ​ቤ​ል​ንና የጋ​ድን ልጆች የም​ና​ሴ​ንም ነገድ እኩ​ሌታ አፈ​ለሰ፥ እስከ ዛሬም ወዳ​ሉ​በት ወደ አላ​ሔና ወደ ኦቦር፥ ወደ ሃራ​ንና ወደ ጎዛን ወንዝ አመ​ጣ​ቸው።


ወልደ አዴ​ርም ንጉ​ሡን አሳን ሰማው፤ የሠ​ራ​ዊ​ቱ​ንም አለ​ቆች በእ​ስ​ራ​ኤል ከተ​ሞች ላይ ሰደደ፤ እነ​ር​ሱም አእ​ዮ​ን​ንና ዳንን፥ አቤ​ል​ማ​ይ​ም​ንና የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም አው​ራጃ ከተ​ሞች ሁሉ መቱ።


ወደ ታችም ወደ ምድር ትመ​ለ​ከ​ታ​ላ​ችሁ፤ ድቅ​ድቅ ጨለ​ማ​ንም ታያ​ላ​ችሁ፤ ታላቅ መከ​ራ​ንም ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ፤ ትጨ​ነ​ቃ​ላ​ችሁ፤ ትቸ​ገ​ራ​ላ​ች​ሁም፤ በፊ​ታ​ች​ሁም ጨለማ ይሆ​ናል፤ አታ​ዩ​ምም፤ በመ​ከ​ራም ያለ ጊዜው እስ​ኪ​ደ​ርስ አይ​ድ​ንም።


እኔ ደግሞ አግ​ድሜ በቍጣ እሄ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም ሰባት እጥፍ እበ​ቀ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


እኔ ደግሞ አግ​ድሜ በቍጣ እሄ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እንደ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም ሰባት እጥፍ እቀ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ።


እር​ሱም ከሙ​ሴና ከነ​ቢ​ያት፥ ከመ​ጻ​ሕ​ፍ​ትም ሁሉ ስለ እርሱ የተ​ነ​ገ​ረ​ውን ይተ​ረ​ጕ​ም​ላ​ቸው ጀመር።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios