Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 54:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እነሆ፥ መጻ​ተ​ኞች በእኔ ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ፤ በአ​ን​ቺም ይማ​ጸ​ናሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ማንም ጕዳት ቢያደርስብሽ፣ ከእኔ አይደለም፤ ጕዳት ያደረሰብሽ ሁሉ ለአንቺ እጁን ይሰጣል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እነሆ፥ ጥቃት ቢደርስብሽ፥ ከእኔ ዘንድ ግን አይሆንም፤ በአንቺም ላይ የሚነሡ ሁሉ ከአንቺ የተነሣ ይወድቃሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በአንቺ ላይ አደጋ ለማድረስ የተነሡ ቢኖሩ ከእኔ የተላኩ ስላልሆኑ ይወድቃሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እነሆ፥ ይሰበሰባሉ፥ ነገር ግን ከእኔ ዘንድ አይሆንም፥ በአንቺም ላይ የሚሰበሰቡ ሁሉ ከአንቺ የተነሣ ይወድቃሉ።

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 54:15
16 Referências Cruzadas  

ለእ​ግ​ሮቼ ወጥ​መ​ድን አዘ​ጋጁ፥ ሰው​ነ​ቴ​ንም አጐ​በ​ጡ​አት፤ ጕድ​ጓ​ድን በፊቴ ቈፈሩ፥ በው​ስ​ጡም ወደቁ።


ካህ​ናት ሆይ፥ ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ልቧ የሚ​ገባ ነገ​ርን ተና​ገሩ፤ ውር​ደቷ እንደ ተፈ​ጸመ፥ ኀጢ​አ​ቷም እንደ ተሰ​ረየ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ ስለ ኀጢ​አቷ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀ​በ​ለች አጽ​ና​ኑ​አት።


የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ፥ የሚ​ቤ​ዣ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ስለ እና​ንተ ወደ ባቢ​ሎን ሰድ​ጃ​ለሁ፤ ስደ​ተ​ኞ​ችን አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም በመ​ር​ከብ ውስጥ ይታ​ሰ​ራሉ።


እነሆ፥ ፍሙን በወ​ናፍ እን​ደ​ሚ​ያ​ናፋ፥ ለሥ​ራ​ውም መሣ​ሪያ እን​ደ​ሚ​ያ​ወጣ ብረት ሠሪ የፈ​ጠ​ር​ሁሽ አይ​ደ​ለም፤ እኔ ግን ለመ​ል​ካም ፈጠ​ር​ሁሽ እንጂ ለጥ​ፋት አይ​ደ​ለም።


በዚያም ቀን ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ ከባድ ድንጋይ አደርጋታለሁ፣ የሚሸከሙአት ሁሉ እጅግ ይቈስላሉ፣ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በላይዋ ላይ ይከማቻሉ።


በዚያም ቀን በኢየሩሳሌም ላይ የሚመጡትን አሕዛብ ሁሉ ለማጥፋት እጋደላለሁ።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ከክብሩ በኋላ ወደ በዘበዙአችሁ አሕዛብ ልኮኛል፣ የሚነካችሁ የዓይኑን ብሌን የሚነካ ነውና።


ምልክት እያደረጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸውና፥ በታላቁም ሁሉን በሚገዛ በእግዚአብሔር ቀን ወደሚሆነው ጦር እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios