Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 54:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አንቺ ያል​ወ​ለ​ድሽ መካን ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፤ አንቺ ያላ​ማ​ጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፤ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆ​ነ​ቺቱ ልጆች በዝ​ተ​ዋ​ልና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “አንቺ መካን፣ አንቺ ልጅ ወልደሽ የማታውቂ፣ ዘምሪ፤ እልል በዪ፤ በደስታ ጩኺ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፣ ባል ካላት ሴት ይልቅ፣ የፈቷ ልጆች ይበዛሉና” ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 አንቺ ያልወለድሽ መካን ሆይ፥ ዘምሪ፤ አንቺ ያላማጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፥ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆነቺቱ ልጆች በዝተዋልና፥ ይላል ጌታ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ባል ካላት ሴት ይልቅ ፈት የሆነችው ልጆች ብዛት ያላቸው ስለ ሆነ፥ ልጅ እንዳልወለደችና አምጣ እንደማታውቀው ሴት የሆንሽው ኢየሩሳሌም ሆይ! እልል እያልሽ ዘምሪ!

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 አንቺ ያልወለድሽ መካን ሆይ፥ ዘምሪ፥ አንቺ ያላማጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፥ ጩኺም፥ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆነቺቱ ልጆች በዝተዋልና፥ ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 54:1
21 Referências Cruzadas  

ሣራም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ አሰ​ኘኝ፤ ይህን የሚ​ሰማ ሁሉ በእኔ ምክ​ን​ያት ደስ ይሰ​ኛ​ልና” አለች።


ለእኛ አይ​ደ​ለም፥ አቤቱ፥ ለእኛ አይ​ደ​ለም፥ ነገር ግን ለስ​ምህ፥ ስለ ምሕ​ረ​ት​ህና ስለ እው​ነ​ት​ህም ምስ​ጋ​ናን እን​ስጥ


እኅ​ታ​ችን ትንሽ ናት፥ ጡትም የላ​ትም፤ ስለ እር​ስዋ በሚ​ና​ገ​ሩ​ባት ቀን ለእ​ኅ​ታ​ችን ምን እና​ድ​ር​ግ​ላት?


አንቺ የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፤ ሐሤ​ትም አድ​ርጊ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ በመ​ካ​ከ​ልሽ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና።”


እነ​ዚህ ድም​ፃ​ቸ​ውን ያነ​ሣሉ፤ በም​ድር የቀ​ሩ​ትም ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር በአ​ን​ድ​ነት ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ የባ​ሕ​ርም ውኃ ይና​ወ​ጣል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ምሕ​ረ​ትን አድ​ር​ጎ​አ​ልና ሰማ​ያት ደስ ይበ​ላ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዕ​ቆ​ብን ተቤ​ዥ​ቶ​አ​ልና፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ይከ​በ​ራ​ልና የም​ድር መሠ​ረ​ቶች መለ​ከ​ትን ይንፉ፤ ተራ​ሮ​ችና ኮረ​ብ​ቶች በው​ስ​ጣ​ቸው ያሉ ዛፎች ሁሉ፥ እልል ይበሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ይቅር ብሎ​አ​ልና፥ ከሕ​ዝ​ቡም ችግ​ረ​ኞ​ቹን አጽ​ን​ቶ​አ​ልና። ሰማ​ያት ሆይ፥ ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ምድ​ርም ደስ ይበ​ላት፤ ተራ​ሮ​ችም እልል ይበሉ።


ፈር​ሰ​ሻ​ልና፥ ፈጽ​መ​ሽም ጠፍ​ተ​ሻ​ልና በአ​ንቺ ለሚ​ኖሩ ሰዎች ዛሬ ጠባብ ትሆ​ኚ​ባ​ቸ​ዋ​ለሽ፤ ያጠ​ፉ​ሽም ከአ​ንቺ ይር​ቃሉ።


አጥ​ተ​ሻ​ቸው የነ​በ​ሩት ልጆ​ች​ሽም በጆ​ሮሽ፦ ስፍራ ጠብ​ቦ​ና​ልና የም​ን​ቀ​መ​ጥ​በት ቦታ አስ​ፊ​ልን ይላሉ።


ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ፥ “የተ​ተ​ወች” አት​ባ​ዪም፤ ምድ​ር​ሽም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ፥ “ውድማ” አት​ባ​ልም፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ንቺ ደስ ብሎ​ታ​ልና፥ ምድ​ር​ሽም ባል ታገ​ባ​ለ​ችና አንቺ፥ “ደስ​ታዬ የሚ​ኖ​ር​ባት” ትባ​ያ​ለሽ፤ ምድ​ር​ሽም፥ “ባል ያገ​ባች” ትባ​ላ​ለች።


“ሳታ​ምጥ ወለ​ደች፤ ምጥም ሳያ​ገ​ኛት ወንድ ልጅን ወለ​ደች።


የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ዘምሪ፣ እስራኤል ሆይ፥ እልል በል፣ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ በፍጹም ልብሽ ሐሴት አድርጊ ደስም ይበልሽ።


አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፣ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፣ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፣ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫንይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።


“የማ​ት​ወ​ልድ መካን ደስ ይላ​ታል፤ ምጥ የማ​ታ​ው​ቀ​ውም ደስ ብሎ​አት እልል ትላ​ለች፤ ባል ካላት ይልቅ የፈ​ቲቱ ልጆች ብዙ​ዎች ናቸ​ውና” ተብሎ ተጽ​ፎ​አል።


እን​ጀራ ጠግ​በው የነ​በሩ ተራቡ፤ ተር​በ​ውም የነ​በሩ ጠገቡ፤ መካ​ኒቱ ሰባት ወል​ዳ​ለ​ችና፥ ብዙም የወ​ለ​ደ​ችው መው​ለድ አል​ቻ​ለ​ችም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios