Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 51:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ባሕ​ርን የማ​ና​ውጥ፥ ሞገ​ዱም እን​ዲ​ተ​ምም የማ​ደ​ርግ አማ​ላ​ክሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝና፥ ስሜም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሞገዱ እንዲተምም ባሕሩን የማናውጥ፣ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝና፤ ስሙም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ሞገዱም እንዲተምም ባሕርን የማናውጥ አምላክህ ጌታ እኔ ነኝ፥ ስሜም የሠራዊት ጌታ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 “ማዕበሉ ይጮኽ ዘንድ ባሕሩን የማናውጥ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ ስሜም የሠራዊት አምላክ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ሞገዱም እንዲተምም ባሕርን የማናውጥ አምላክህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፥ ስሜም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 51:15
16 Referências Cruzadas  

ከፊ​ታ​ቸ​ውም ባሕ​ሩን ከፈ​ልህ፤ በባ​ሕ​ሩም መካ​ከል በደ​ረቅ ዐለፉ፤ የተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውን ግን ድን​ጋይ በጥ​ልቅ ውኃ እን​ዲ​ጣል በቀ​ላይ ውስጥ ጣል​ሃ​ቸው።


በኀ​ይሉ ባሕ​ርን ጸጥ ያደ​ር​ጋል፥ በማ​ስ​ተ​ዋ​ሉም ዐን​በ​ሪ​ውን ይገ​ለ​ብ​ጠ​ዋል።


ለእ​ኔም ሕዝብ እን​ድ​ት​ሆኑ እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ አም​ላ​ክም እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን ባር​ነት ያወ​ጣ​ኋ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


ታዳ​ጊሽ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ስሙ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ነው።


በቅ​ድ​ስት ከተማ ስም የተ​ጠ​ራ​ችሁ፥ ስሙም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ባል በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የም​ት​ደ​ገፉ፥ ይህን ስሙ።


ባሕ​ሩን ያደ​ረ​ቅሽ፥ ጥል​ቁ​ንም ውኃ ያደ​ረ​ቅ​ሽው፥ የዳ​ኑ​ትም ይሻ​ገሩ ዘንድ ጥል​ቁን ባሕር ጥር​ጊያ ጎዳና ያደ​ረ​ግሽ አይ​ደ​ለ​ሽ​ምን?


ፈጣ​ሪሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ስሙም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ታዳ​ጊሽ ነው፤ እር​ሱም በም​ድር ሁሉ እን​ደ​ዚሁ ይጠ​ራል።


የያ​ዕ​ቆብ ዕድል ፈንታ እንደ እነ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ እርሱ ሁሉን የፈ​ጠረ ነውና እስ​ራ​ኤ​ልም የር​ስቱ ነገድ ነውና፤ ስሙም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።


ስሙ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የሚ​ባል፥ ፀሐ​ይን በቀን፥ ጨረ​ቃ​ንና ከዋ​ክ​ብ​ት​ንም በሌ​ሊት ብር​ሃን አድ​ርጎ የሚ​ሰጥ፥ እን​ዲ​ተ​ም​ሙም የባ​ሕ​ርን ሞገ​ዶች የሚ​ያ​ና​ውጥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦


“ምድ​ራ​ቸው በእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ላይ በተ​ሠ​ራው በደል የተ​ሞ​ላች ብት​ሆ​ንም፥ እስ​ራ​ኤል መበ​ለት አል​ሆ​ነ​ችም፤ ይሁ​ዳም ከአ​ም​ላኩ ከሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ አል​ራ​ቀም።


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ቀድሱ፤ ቅዱ​ሳ​ንም ሁኑ፤ እኔ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ነኝና፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios