Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 5:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ይህ በሠ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጆሮ ተሰ​ም​ቶ​አ​ልና፦ ቤቶች ቢሠሩ ባድማ ይሆ​ናሉ፤ ታላ​ላ​ቅና የሚ​ያ​ምሩ ቤቶ​ችም የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸው አይ​ኖ​ርም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ጆሮዬ እየሰማ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ “ታላላቅ ቤቶች ወና ይቀራሉ፣ የሚያማምሩም ቤቶች ኗሪ ያጣሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ጆሮዬ እየሰማ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ “ታላላቅ ቤቶች ወና ይቀራሉ፤ የሚያማምሩም ቤቶች ነዋሪ ያጣሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እነሆ የሠራዊት አምላክ እንዲህ ብሎ በመሐላ ሲያረጋግጥ ሰምቼአለሁ፦ “የተዋቡ ታላላቅ ቤቶች ሁሉ ፈርሰው ወና ይሆናሉ፤ የሚኖርባቸው ሰውም አይገኝም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጆሮዬ እንዲህ አለ፦ በእውነት ብዙ ታላቅና መልካም ቤት ባድማ ይሆናል፥ የሚቀመጥበትም አይገኝም።

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 5:9
14 Referências Cruzadas  

በኤ​ር​ም​ያስ አፍ የተ​ነ​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እን​ዲ​ፈ​ጸም፥ ምድ​ሪቱ ሰን​በ​ትን በማ​ድ​ረ​ግዋ እስ​ክ​ታ​ርፍ ድረስ፥ በተ​ፈ​ታ​ች​በ​ትም ዘመን ሁሉ፥ ሰባ ዓመት እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ፥ ሰን​በ​ትን አገ​ኘች።


በተ​ፈ​ቱም ከተ​ሞች ውስጥ ይኖ​ራል፥ ሰውም በሌ​ለ​ባ​ቸው ቤቶች ይገ​ባል፥ እርሱ ያዘ​ጋ​ጀ​ው​ንም ሌሎች ይወ​ስ​ዱ​ታል።


ለሀ​ብቱ ትርፍ የለ​ውም፤ ስለ​ዚህ በረ​ከቱ አት​ከ​ና​ወ​ን​ለ​ትም።


መማለጃን የሚቀበል ራሱን ያጠፋል፤ መማለጃ መቀበልን የሚጠላ ግን ይድናል። በምጽዋትና በእምነት ኀጢአት ይሰረያል። እግዚአብሔርንም በመፍራት ክፉ ሁሉ ይወገዳል።


ይህም ነገር በሠ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጆሮ ተሰማ፥ “እስ​ክ​ት​ሞቱ ድረስ ይህ በደል በእ​ው​ነት አይ​ሰ​ረ​ይ​ላ​ች​ሁም” ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በዚ​ያም የተ​ሰ​ማ​ራው መንጋ እንደ ተተወ መንጋ ይሆ​ናል፤ ምድ​ሩም ለብዙ ዘመን መሰ​ማ​ሪያ ይሆ​ናል፤ በዚ​ያም መን​ጋው ይሰ​ማ​ራል፤ ያር​ፋ​ልም።


ባድማ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ አይ​ገ​ረ​ዝም፤ አይ​ኰ​ተ​ኰ​ትም፤ እንደ ጠፍ ቦታ ኵር​ን​ች​ትና እሾህ ይበ​ቅ​ል​በ​ታል፤ ዝና​ብ​ንም እን​ዳ​ያ​ዘ​ን​ቡ​በት ደመ​ና​ዎ​ችን አዝ​ዛ​ለሁ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለባ​ሪ​ያ​ዎቹ ለነ​ቢ​ያት ያል​ገ​ለ​ጠ​ው​ንና ያል​ነ​ገ​ረ​ውን ምንም አያ​ደ​ር​ግ​ምና።


ድሃ​ው​ንም ደብ​ድ​ባ​ች​ኋ​ልና፤ መማ​ለ​ጃ​ንም ከእ​ርሱ ወስ​ዳ​ች​ኋ​ልና፤ ያማሩ ቤቶ​ች​ንም መር​ጣ​ችሁ ሠር​ታ​ች​ኋ​ልና፥ ነገር ግን አት​ኖ​ሩ​ባ​ቸ​ውም፤ ያማሩ የወ​ይን ቦታ​ዎ​ችም ተክ​ላ​ች​ኋል፤ ነገር ግን ወይ​ንን አት​ጠ​ጡም።


እነ​ሆም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዝ​ዛል፤ ታላ​ቁ​ንም ቤት በማ​ፍ​ረስ፥ ታና​ሹ​ንም ቤት በመ​ሰ​ባ​በር ይመ​ታል።


ንጉሡም ተቈጣ፤ ጭፍሮቹንም ልኮ እነዚያን ገዳዮች አጠፋ፤ ከተማቸውንም አቃጠለ።


እነሆ፥ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል።


እነሆ እርሻችሁን ያጨዱት የሠራተኞች ደመወዝ በእናንተ ተቀምቶ ይጮኻል፤ የአጫጆችም ድምፅ ወደ ጌታ ጸባዖት ጆሮ ገብቶአል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios