Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 47:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እነ​ርሱ ረዳ​ቶ​ችሽ ይሆ​ናሉ፤ ከሕ​ፃ​ን​ነ​ትሽ ጀም​ረሽ ደከ​ምሽ፤ ሰው በራሱ ይሳ​ሳ​ታል፤ ለአ​ንቺ ግን መድ​ኀ​ኒት የለ​ሽም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከልጅነት ጀምሮ ዐብረሻቸው የደከምሽው፣ ዐብረሽ የተገበያየሻቸው፣ ሊያደርጉ የሚችሉት ይህንኑ ብቻ ነው። እያንዳንዱ በስሕተቱ ይገፋበታል፤ አንቺን ግን የሚያድን የለም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የደከምሽባቸው ነገሮች እንዲህ ይሆኑብሻል፤ ከሕፃንነትሽ ጀምረው ከአንቺ ጋር ይነግዱ የነበሩ እያንዳንዳቸው ወደ ስፍራቸው ይሄዳሉ፥ የሚያድንሽ አይገኝም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ከወጣትነትሽ ጀምሮ ከአንቺ ጋር ለመጠንቈል ይመላለሱ የነበሩት አስማተኞችም ሁሉ እንደዚሁ በተሳሳተ መንገድ ይባክናሉ፤ ስለዚህ አንቺን ማንም ሊያድንሽ አይችልም።”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የደከምሽባቸው ነገሮች እንዲህ ይሆኑብሻል፥ ከሕፃንነትሽ ጀምረው ከእንቺ ጋር ይነግዱ የነበሩ እያንዳንዳቸው ወደ ስፍራቸው ይሄዳሉ፥ የሚያድንሽም የለም።

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 47:15
8 Referências Cruzadas  

ከጥ​ንት ጀምሮ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከእ​ጄም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም፤ እሠ​ራ​ለሁ፤ ወደ ኋላስ የሚ​መ​ልስ ማን ነው?


በጫ​ን​ቃ​ቸው ላይ ተሸ​ክ​መ​ውት ይሄ​ዳሉ፤ በስ​ፍ​ራ​ውም በአ​ኖ​ሩት ጊዜ በዚያ ይቆ​ማል፤ ከስ​ፍ​ራ​ውም ፈቀቅ አይ​ልም፤ ሰውም ወደ እርሱ ቢጮህ አይ​ሰ​ማ​ውም፤ ከክ​ፉም አያ​ድ​ነ​ውም።


በክፉ ምክ​ርሽ ደክ​መ​ሻል፤ አሁ​ንም የሰ​ማ​ይን ከዋ​ክ​ብት የሚ​ቈ​ጥሩ፥ ከዋ​ክ​ብ​ት​ንም የሚ​መ​ለ​ከቱ ይነሡ፤ ያድ​ኑ​ሽም፤ ምን እን​ደ​ሚ​መ​ጣ​ብ​ሽም ይን​ገ​ሩሽ፤


ጩኸ​ታ​ቸው እንደ አን​በሳ ነው፤ እንደ አን​በሳ ደቦ​ሎ​ችም ይቆ​ማሉ፤ ከጕ​ድ​ጓዱ እን​ደ​ሚ​ወጣ አው​ሬም ይነ​ጥ​ቃሉ፤ ይጮ​ሃሉ፤ የሚ​ድ​ንም የለም።


ሁሉም ከቶ የማ​ይ​ጠ​ግቡ የረ​ከሱ ውሾች ናቸው፤ እነ​ር​ሱም ያስ​ተ​ውሉ ዘንድ የማ​ይ​ችሉ ክፉ​ዎች ናቸው፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው እንደ ፈቃ​ዳ​ቸው መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ተከ​ት​ለ​ዋል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios