Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 41:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ከሰ​ሜ​ንና ከፀ​ሐይ መውጫ የሚ​መ​ጡ​ትን አስ​ነ​ሣሁ፤ በስ​ሜም ይጠ​ራሉ፤ አለ​ቆች ይምጡ፤ እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃና ጭቃን እን​ደ​ሚ​ረ​ግጥ ሸክላ ሠሪ እን​ዲሁ ይረ​ግ​ጡ​አ​ቸ​ዋል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “አንዱን ከሰሜን አስነሣሁት፤ እርሱም ይመጣል፤ ከፀሓይ መውጫ የሚመጣው፣ ስሜን የሚጠራ ነው፤ ሸክላ ሠሪ ዐፈር እንደሚረግጥ፣ አለቆችን እንዲሁ እንደ ጭቃ ይረግጣል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 አንዱን ከሰሜን አነሣሁ መጥቶአልም፤ አንዱም ከፀሐይ መውጫ ስሜን የሚጠራ ይመጣል፤ በጭቃ ላይ እንደሚመጣ ሰው አፈርም እንደሚረግጥ ሸክለኛ በአለቆች ላይ ይመጣል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 “እኔ እግዚአብሔር አንድ መሪ ከሰሜን አስነሥቼአለሁ፤ መጥቶአልም። እርሱም ስሜን የሚጠራና ከፀሐይ መውጫ በኩል የሚመጣ ነው። ሸክላ ሠሪ የሸክላውን ዐፈር እንደሚረግጥ መሪዎችን ይረግጣል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 አንዱን ከሰሜን አነሣሁ መጥቶአልም፥ አንዱም ከፀሐይ መውጫ ስሜን የሚጠራ ይመጣል፥ በጭቃ ላይ እንደሚመጣ ሰው አፈርም እንደሚረግጥ ሸክለኛ በአለቆች ላይ ይመጣል።

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 41:25
15 Referências Cruzadas  

በነ​ፋስ ፊት እን​ዳለ እንደ ምድር ትቢያ ፈጨ​ኋ​ቸው፤ እንደ ጎዳ​ናም ጭቃ ረገ​ጥ​ኋ​ቸው፤ ደቀ​ደ​ቅ​ኋ​ቸ​ውም።


ቍጣ​ዬን በኀ​ጢ​አ​ተኛ ሕዝብ ላይ እል​ካ​ለሁ፤ ይማ​ር​ኳ​ቸ​ውና ይበ​ዘ​ብ​ዙ​አ​ቸው ዘንድ፥ ከተ​ሞ​ች​ንም ይረ​ግ​ጡ​አ​ቸ​ውና እንደ ትቢያ ያደ​ር​ጓ​ቸው ዘንድ ሕዝ​ቤን አዝ​ዛ​ለሁ።


ከባድ ራእይ ተነ​ገ​ረኝ፤ ወን​ጀ​ለ​ኛው ይወ​ነ​ጅ​ላል፤ በደ​ለ​ኛ​ውም ይበ​ድ​ላል። የኤ​ላም ሰዎ​ችና የሜ​ዶን መል​እ​ክ​ተኛ በእኔ ላይ ይመ​ጣሉ። ዛሬ ግን እጨ​ነ​ቃ​ለሁ፤ እረ​ጋ​ጋ​ለ​ሁም።


ከም​ሥ​ራቅ ጽድ​ቅን ያስ​ነሣ፥ ይከ​ተ​ለ​ውም ዘንድ ወደ እግሩ የጠ​ራው ማን ነው? በአ​ሕ​ዛ​ብና በነ​ገ​ሥ​ታት ፊት ድን​ጋ​ጤን ያመ​ጣል። ጦሮ​ቻ​ቸ​ውን በም​ድር ያስ​ጥ​ላ​ቸ​ዋል፤ ቀስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እንደ ገለባ ይረ​ግ​ፋሉ።


ቂሮ​ስ​ንም፥ “ብልህ ሁን፤ እር​ሱም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን፦ ትታ​ነ​ጺ​ያ​ለሽ ቤተ መቅ​ደ​ስ​ንም እመ​ሠ​ር​ታ​ለሁ ብሎ ፈቃ​ዴን ሁሉ ይፈ​ጽ​ማል” ይላል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ለቀ​ባ​ሁት፥ አሕ​ዛ​ብ​ንም በፊቱ አስ​ገዛ ዘንድ የነ​ገ​ሥ​ታ​ት​ንም ኀይል እጥል ዘንድ፥ በሮ​ቹም እን​ዳ​ይ​ዘጉ መዝ​ጊ​ያ​ዎ​ቹን በፊቱ እከ​ፍት ዘንድ፥ ቀኝ እጁን ለያ​ዝ​ሁት ለቂ​ሮስ እን​ዲህ ይላል፦


እኔ ቂሮ​ስን በጽ​ድቅ አስ​ነ​ሥ​ቼ​ዋ​ለሁ፤ መን​ገ​ዱ​ንም ሁሉ አቀ​ና​ለሁ፤ እርሱ ከተ​ማ​ዬን ይሠ​ራል፤ በዋ​ጋም ወይም በጉቦ ሳይ​ሆን ምር​ኮ​ኞ​ችን ያወ​ጣል፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ከሰ​ሜን ወገን ክፉ ነገር በም​ድ​ሪቱ በተ​ቀ​መጡ ሁሉ ላይ ይፈ​ስ​ሳል።


ሕዝቤ ከሰ​ሜን በእ​ር​ስዋ ላይ ወጥ​ት​ዋል፤ ምድ​ር​ዋ​ንም ባድማ ያደ​ር​ጋል፤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም አይ​ገ​ኝም፤ ከሰው ጀምሮ እስከ እን​ስሳ ድረስ ሸሽ​ተው ሄደ​ዋል።


ጠላቴም ታያለች፥ እኔንም፦ አምላክህ እግዚአብሔር ወዴት ነው? ያለች በእፍረት ትከደናለች።


በሰልፍም ጊዜ ጠላቶቻቸውን በመንገድ ጭቃ ውስጥ እንደሚረግጡ ኃያላን ይሆናሉ፣ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ነውና ይዋጋሉ፥ ፈረሰኞችም ያፍራሉ።


ስድስተኛውም ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከፀሐይም መውጫ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲሰናዳላቸው ውሃው ደረቀ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios