Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 41:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ይኸ​ውም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ይህን ሁሉ እንደ ሠራ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቅዱስ ይህን እንደ አሳየ ያውቁ ዘንድ፥ ያስ​ተ​ው​ሉም ዘንድ፥ ይረ​ዱም ዘንድ፥ ያም​ኑም ዘንድ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ስለዚህ ሰዎች ያያሉ፤ ያውቃሉ፤ የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንዳደረገ፣ የእስራኤል ቅዱስ እንደ ፈጠረው፣ በአንድነት ይገነዘባሉ፤ ያስተውላሉም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ስለዚህ የጌታ እጅ ይህን እንዳደረገ፥ የእስራኤል ቅዱስ እንደፈጠረው፥ ሰዎች እንዲያዩና እንዲያውቁ፥ በአንድነት እንዲገነዘቡ፤ እንዲያስተውሉም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ይህን የማደርገው የእኔ የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንዳደረገና እኔም የእስራኤል ቅዱስ እንደ ፈጠርኩት ሁሉም አይተው ያውቁ ዘንድ፥ አስተውለውም ይረዱ ዘንድ ነው።”

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 41:20
20 Referências Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ይህን ሁሉ እን​ዳ​ደ​ረገ ከእ​ነ​ዚህ ሁሉ የማ​ያ​ውቅ ማን ነው?


ለእ​ኔም ሕዝብ እን​ድ​ት​ሆኑ እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ አም​ላ​ክም እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን ባር​ነት ያወ​ጣ​ኋ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


ነገር ግን ኀይ​ሌን እገ​ል​ጥ​ብህ ዘንድ፥ ስሜም በም​ድር ሁሉ ላይ ይነ​ገር ዘንድ ስለ​ዚህ ጠበ​ቅ​ሁህ።


ይህም ደግሞ ድንቅ ምክ​ርን ከሚ​መ​ክር በግ​ብ​ሩም ገናና ከሆ​ነው ከሠ​ራ​ዊት ጌታ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወጥ​ቶ​አል። እና​ንተ ግን ከንቱ መጽ​ና​ና​ትን ታበዙ ዘንድ ትሻ​ላ​ችሁ።


በመ​ን​ፈ​ስም የሳቱ ማስ​ተ​ዋ​ልን ያው​ቃሉ፤ የሚ​ያ​ጕ​ረ​መ​ር​ሙም መታ​ዘ​ዝን ይማ​ራሉ፤ ዲዳ አን​ደ​በ​ትም ሰላም መና​ገ​ርን ይማ​ራል።”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ይገ​ለጥ፤ ሥጋ ለባ​ሹም ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትድ​ግና ይይ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።”


ይህን የሠ​ራና ያደ​ረገ፥ ትው​ል​ድ​ንም ከጥ​ንት የጠራ ማን ነው? እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊተ​ኛ​ውና ኋለ​ኛው እኔ ነኝ።


ቅዱ​ሳ​ችሁ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ፈጣሪ፥ ንጉ​ሣ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ እኔ ነኝ።”


እነ​ር​ሱም ምስ​ጋ​ና​ዬን እን​ዲ​ና​ገሩ ለእኔ የፈ​ጠ​ር​ኋ​ቸው ሕዝብ ናቸው፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ምሕ​ረ​ትን አድ​ር​ጎ​አ​ልና ሰማ​ያት ደስ ይበ​ላ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዕ​ቆ​ብን ተቤ​ዥ​ቶ​አ​ልና፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ይከ​በ​ራ​ልና የም​ድር መሠ​ረ​ቶች መለ​ከ​ትን ይንፉ፤ ተራ​ሮ​ችና ኮረ​ብ​ቶች በው​ስ​ጣ​ቸው ያሉ ዛፎች ሁሉ፥ እልል ይበሉ።


ነገ​ሥ​ታ​ትም አሳ​ዳ​ጊ​ዎች አባ​ቶ​ችሽ ይሆ​ናሉ፤ እቴ​ጌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ሞግ​ዚ​ቶ​ችሽ ይሆ​ናሉ፤ ግን​ባ​ራ​ቸ​ው​ንም ወደ ምድር ዝቅ አድ​ር​ገው ይሰ​ግ​ዱ​ል​ሻል፤ የእ​ግ​ር​ሽ​ንም ትቢያ ይል​ሳሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቂ​ያ​ለሽ፤ እኔ​ንም በመ​ተ​ማ​መን የሚ​ጠ​ባ​በቁ አያ​ፍ​ሩም።”


ታያ​ላ​ችሁ፤ ልባ​ች​ሁም ሐሤት ታደ​ር​ጋ​ለች፤ አጥ​ን​ታ​ች​ሁም እንደ ለም​ለም ሣር ትበ​ቅ​ላ​ለች፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ ለሚ​ፈ​ሩት ትታ​ወ​ቃ​ለች፤ ዐላ​ው​ያ​ን​ንም ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል።”


“ሥራ​ቸ​ው​ንና አሳ​ባ​ቸ​ውን ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤ እነ​ሆም እኔ እመ​ጣ​ለሁ፤ አሕ​ዛ​ብ​ንና ልሳ​ና​ት​ንም ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይመ​ጣሉ፤ ክብ​ሬ​ንም ያያሉ።


ይህ ሁሉ የእጄ ሥራ ነው፤ ይህም ሁሉ የእኔ ነው፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “ወደ የዋ​ሁና ወደ ጸጥ​ተ​ኛው፥ ከቃ​ሌም የተ​ነሣ ወደ​ሚ​ን​ቀ​ጠ​ቀጥ ሰው ከአ​ል​ሆነ በቀር ወደ ማን እመ​ለ​ከ​ታ​ለሁ?


በያ​ዕ​ቆብ ላይ ጥን​ቆላ የለም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ምዋ​ርት የለም፤ በየ​ጊ​ዜው ስለ ያዕ​ቆ​ብና ስለ እስ​ራ​ኤል፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምን አደ​ረገ? ይባ​ላል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios