Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 40:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እርሱ የም​ድ​ርን ክበብ ያጸ​ናል፤ በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ኖ​ሩት እንደ አን​በጣ ናቸው፤ ሰማ​ያ​ትን እንደ መጋ​ረጃ የሚ​ዘ​ረ​ጋ​ቸው፥ እንደ ድን​ኳ​ንም ለመ​ኖ​ሪያ የሚ​ዘ​ረ​ጋ​ቸው፤

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እርሱ ከምድር ክበብ በላይ በዙፋን ላይ ይቀመጣል፤ ሕዝቦቿም እንደ አንበጣ ናቸው። ሰማያትን እንደ ድባብ ይዘረጋቸዋል፤ እንደ መኖሪያ ድንኳንም ይተክላቸዋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እርሱ በምድር ክበብ ላይ ይቀምጣል፥ በእርሷም የሚኖሩት እንደ አንበጣ ናቸው፤ ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚዘረጋቸው እንደ ድንኳንም ለመኖርያ የሚዘረጋቸው፥

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እግዚአብሔር ከምድር ክበብ በላይ ዙፋኑን ዘርግቶ መቀመጡን ሰማይን እንደ መጋረጃ መወጠሩንና፥ እንደ መኖሪያ ድንኳን መዘርጋቱን የምድርም ሕዝቦች እንደ ፌንጣ አነስተኞች መሆናቸውን።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እርሱ በምድር ክበብ ላይ ይቀምጣል፥ በእርስዋም የሚኖሩት እንደ አንበጣ ናቸው፥ ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚዘረጋቸው እንደ ድንኳንም ለመኖርያ የሚዘረጋቸው፥

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 40:22
28 Referências Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በው​ኃው መካ​ከል ጠፈር ይሁን፤ በው​ኃና በውኃ መካ​ከ​ልም ይለይ” አለ፤ እን​ዲ​ሁም ሆነ።


የጠ​ቈረ ደመና ጋር​ዶ​ታል አያ​ይ​ምም፤ በሰ​ማይ ክበብ ላይ ይራ​መ​ዳል።


ሰማ​ይን በባዶ ስፍራ ላይ ይዘ​ረ​ጋል፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አን​ዳች አልባ ያን​ጠ​ለ​ጥ​ላል።


አንድ ሰው የደ​መ​ና​ውን መዘ​ር​ጋት፥ ወይም የማ​ደ​ሪ​ያ​ውን ልክ ቢያ​ውቅ፥


እንደ ቀለጠ መስ​ተ​ዋት ብርቱ የሆ​ኑ​ትን ሰማ​ያት ከእ​ርሱ ጋር ልት​ዘ​ረጋ ትች​ላ​ለ​ህን?


ሰማ​ያ​ትን ብቻ​ውን ይዘ​ረ​ጋል፥ በም​ድር ላይ እን​ደ​ሚ​ሄድ በማ​ዕ​በል ላይ ይሄ​ዳል።


ተቀ​ኙ​ለት፥ ዘም​ሩ​ለት፥ ተአ​ም​ራ​ቱ​ንም ሁሉ ተና​ገሩ።


ባሪ​ያህ ደግሞ ይጠ​ብ​ቀ​ዋል፤ በመ​ጠ​በ​ቁም ብዙ ዋጋ ይቀ​በ​ላል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ልብህ ይስ​ጥህ ፈቃ​ድ​ህ​ንም ሁሉ ይፈ​ጽ​ም​ልህ።


በሰ​ማይ የሚ​ኖር እርሱ ይሥ​ቅ​ባ​ቸ​ዋል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሣ​ለ​ቅ​ባ​ቸ​ዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰማ፥ ይቅ​ርም አለኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳቴ ሆነኝ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድሆ​ችን ሰም​ቶ​እ​ቸ​ዋ​ልና፥ እስ​ረ​ኞ​ች​ንም አል​ና​ቃ​ቸ​ው​ምና።


ሰማዮችን በዘረጋ ጊዜ አብሬ ነበርሁ፥ ዙፋኑን በነፋሳት ላይ ባጸና ጊዜ፥


ስለ ግብፅ የተ​ነ​ገረ ራእይ። እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ጣን ደመና ተቀ​ምጦ ወደ ግብፅ ይመ​ጣል፤ የግ​ብ​ፅም የእ​ጆ​ቻ​ቸው ሥራ​ዎች በፊቱ ይዋ​ረ​ዳሉ፤ የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ልብ በው​ስ​ጣ​ቸው ይቀ​ል​ጣል።


“አቤቱ፥ በኪ​ሩ​ቤል ላይ የም​ት​ቀ​መጥ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ ሆይ፥ አንተ ብቻ​ህን የም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ አም​ላክ ነህ፤ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ፈጥ​ረ​ሃል።


እነሆ፥ አሕ​ዛብ በገ​ንቦ እን​ዳ​ለች ጠብታ ናቸው፤ እንደ ሚዛ​ንም ውል​ብ​ል​ቢት ተቈ​ጥ​ረ​ዋል፤ እንደ ኢም​ን​ትም ናቸው።


አሕ​ዛብ ሁሉ በፊቱ እን​ዳ​ል​ነ​በሩ ናቸው፤ እንደ ከንቱ ነገ​ርም ይመ​ስ​ላሉ።


በም​ድ​ርም ፍር​ድን እስ​ኪ​ያ​ደ​ርግ ድረስ ያበ​ራል እንጂ አይ​ጠ​ፋም፤ አሕ​ዛ​ብም በስሙ ይታ​መ​ናሉ።


ሰማ​ይን የፈ​ጠረ፥ የዘ​ረ​ጋ​ውም፥ ምድ​ር​ንና በው​ስ​ጥዋ ያለ​ውን ሁሉ ያጸና፥ በእ​ር​ስዋ ላይ ለሚ​ኖሩ ሕዝብ እስ​ት​ን​ፋ​ስን፥ ለሚ​ሄ​ዱ​ባ​ትም መን​ፈ​ስን የሚ​ሰጥ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦


ከማ​ኅ​ፀን የሠ​ራህ፥ የሚ​ቤ​ዥህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሁሉን ለብ​ቻዬ የፈ​ጠ​ርሁ፥ ሰማ​ያ​ትን የዘ​ረ​ጋሁ፥ ምድ​ር​ንም ያጸ​ናሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ፤


አንቺ ግን ሰማ​ያ​ትን የፈ​ጠ​ረ​ውን፥ ምድ​ር​ንም የመ​ሠ​ረ​ታ​ትን ፈጣ​ሪ​ሽን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረስ​ተ​ሻል፤ ያጠ​ፋሽ ዘንድ ባዘ​ጋጀ ጊዜ ከአ​ስ​ጨ​ና​ቂው ቍጣ የተ​ነሣ ሁል​ጊዜ ቀኑን ሁሉ ፈር​ተ​ሻል፤ ይቈ​ጣሽ ዘንድ መክ​ሮ​አ​ልና፤ አሁን የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቅሽ ቍጣው የት አለ?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድ​ርም የእ​ግሬ መረ​ገጫ ናት፤ የም​ት​ሠ​ሩ​ልኝ ቤት ምን ዓይ​ነት ነው? የማ​ር​ፍ​በ​ትስ ስፍራ ምን​ድን ነው?


ምድ​ርን በኀ​ይሉ የፈ​ጠረ፥ ዓለ​ሙን በጥ​በቡ ያጸና፥ ሰማ​ያ​ት​ንም በማ​ስ​ተ​ዋሉ የዘ​ረጋ እርሱ ነው።


ስለ እስራኤል የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ሸክም ይህ ነው። ሰማያትን የዘረጋ፥ ምድርንም የመሠረተ፥ የሰውንም መንፈስ በውስጡ የሠራ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦


በዚ​ያም ግዙ​ፋን የሆ​ኑ​ትን አየን፤ እኛም በእ​ነ​ርሱ ፊት እንደ አን​በ​ጣ​ዎች ሆን፤ እን​ዲ​ሁም በፊ​ታ​ቸው ነበ​ርን፤” እያሉ የሰ​ለ​ሉ​አ​ትን ምድር ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አስ​ፈሪ አደ​ረ​ጓት።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios