Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 36:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ራፋ​ስ​ቂ​ስን ከብዙ ሠራ​ዊት ጋር ከለ​ኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ላከው፤ እር​ሱም በአ​ጣ​ቢው እርሻ መን​ገድ ባለ​ችው በላ​ይ​ኛ​ዪቱ ኵሬ መስኖ አጠ​ገብ ቆመ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 የአሦር ንጉሥ የጦር አዛዡን ከብዙ ሰራዊት ጋራ ከለኪሶ፣ ንጉሡ ሕዝቅያስ ወዳለበት፣ ወደ ኢየሩሳሌም ላከው። የጦር አዛዡም ወደ ልብስ ዐጣቢው ዕርሻ በሚወስደው መንገድ፣ በላይኛው ኵሬ ቦይ አጠገብ ደርሶ ቆመ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ከዚያ የአሦር ንጉሥ ራፋስቂስን ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ ወደ ንጉሡ ሕዝቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም ላከው። እርሱም በልብስ አጣቢው እርሻ መንገድ ላይ ባለችው በላይኛይቱ ኩሬ መስኖ አጠገብ በቆመ ጊዜ፥

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ንጉሥ ሕዝቅያስ እጁን እንዲሰጥ ይጠይቀው ዘንድ የአሦር ንጉሥ የጦር አዛዡን፥ ከብዙ ሠራዊት ጋር ከላኪሽ ወደ ኢየሩሳሌም ላከው፤ እርሱም ሄዶ የላይኛው ኲሬ ውሃ በሚተላለፍበት ቦይ አካባቢ በሚገኘው በልብስ አጣቢው ቦታ አጠገብ ቆመ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የአሦርም ንጉሥ ራፋስቂስን ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም ላከ፥ እርሱም በአጣቢው እርሻ መንገድ ባለችው በላይኛይቱ ኵሬ መስኖ አጠገብ ቆመ።

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 36:2
10 Referências Cruzadas  

አክ​ዓ​ብም ናቡ​ቴን፥ “በቤቴ አቅ​ራ​ቢያ ነውና የአ​ት​ክ​ልት ቦታ አደ​ር​ገው ዘንድ የወ​ይን ቦታ​ህን ስጠኝ፤ ስለ እር​ሱም ከእ​ርሱ የተ​ሻለ የወ​ይን ቦታ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ ወይም ብት​ወ​ድድ ዋጋ​ውን ወርቅ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ” ብሎ ተና​ገ​ረው።


የአ​ሦ​ርም ንጉሥ እስ​ራ​ኤ​ልን ወደ አሦር አፈ​ለሰ፤ በአ​ላ​ሔና በአ​ቦር በጎ​ዛ​ንም ወንዝ፥ በሜ​ዶ​ንም አው​ራ​ጃ​ዎች አኖ​ራ​ቸው፤


አሁን እን​ግ​ዲህ ከጌ​ታዬ ከአ​ሦር ንጉሥ ጋር ተስ​ማማ፤ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ው​ንም ሰዎች ማግ​ኘት ቢቻ​ልህ እኔ ሁለት ሺህ ፈረ​ሶ​ችን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢሳ​ይ​ያ​ስን አለው፥ “አን​ተና ልጅህ ያሱብ አካ​ዝን ትገ​ና​ኙት ዘንድ በል​ብስ አጣ​ቢው እርሻ መን​ገድ ወዳ​ለው ወደ ላይ​ኛው መታ​ጠ​ቢያ ቦታ ውጡ፤


የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ሠራ​ዊት ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንና የቀ​ሩ​ትን የይ​ሁ​ዳን ከተ​ሞች ሁሉ፥ ለኪ​ሶ​ንና አዚ​ቃ​ንም ይወጋ ነበር። እነ​ዚህ የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞች በይ​ሁዳ ከተ​ሞች መካ​ከል ቀር​ተው ነበ​ርና።


በለኪሶ የምትቀመጪ ሆይ፥ ሰረገላውን ለፈረስ እሰሪ፥ እርስዋ ለጽዮን ሴት ልጆች የኃጢአት መጀመሪያ ነበረች፥ የእስራኤል በደል በአንቺ ዘንድ ተገኝቶአልና።


ቁስልዋ የማይፈወስ ነውና፥ እስከ ይሁዳም ደርሶአልና፥ ወደ ሕዝቤም በር ወደ ኢየሩሳሌም ቀርቦአልና።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios