Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 34:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ኀያ​ላን ከእ​ነ​ርሱ ጋር፥ ወይ​ፈ​ኖ​ችም ከኮ​ር​ማ​ዎች ጋር ይወ​ድ​ቃሉ፤ ምድ​ራ​ቸ​ውም በደም ትሰ​ክ​ራ​ለች፤ በስ​ባ​ቸ​ውም ትወ​ፍ​ራ​ለች።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ጐሽ ዐብሯቸው፣ ኰርማም ከወይፈን ጋራ ይወድቃል፤ ምድራቸው በደም ትርሳለች፤ ዐፈራቸውም ሥብ በሥብ ይሆናል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ጎሽ ከእነርሱ ጋር፥ ወይፈኖችም ከኮርማዎች ጋር ይወድቃሉ፤ ምድራቸውም በደም ትርሳለች፥ አፈራቸውም በስብ ትወፍራለች።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የኤዶም ሕዝብ እንደ ጐሽ፥ እንደ ኰርማና እንደ ወይፈን ይወድቃሉ፤ ነገር ግን ከሌሎች ጋር አብረው ይሞታሉ፤ ሀገሪቱም በደማቸው ትነከራለች፤ ምድሪቱም በስባቸው ትዳብራለች።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ጎሽ ከእነርሱ ጋር፥ ወይፈኖችም ከኮርማዎች ጋር ይወድቃሉ፥ ምድራቸውም በደም ትረካለች፥ አፈራቸውም በስብ ትወፍራለች።

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 34:7
15 Referências Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም በዝ​ማሬ አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፥ በም​ስ​ጋ​ናም ከፍ ከፍ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።


በመ​ቅ​ሠ​ፍቴ ረገ​ጥ​ኋ​ቸው፤ ደማ​ቸ​ው​ንም ወደ ምድር አፈ​ሰ​ስ​ሁት።


ትታ​ረ​ዱና ትበ​ተኑ ዘንድ ቀና​ችሁ ደር​ሶ​አ​ልና፥ እንደ ተወ​ደደ የሸ​ክላ ዕቃ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ች​ሁና እና​ንተ እረ​ኞች! አል​ቅሱ፤ እና​ን​ተም የበ​ጎች አው​ራ​ዎች! ጩኹ።


በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ የተ​ቀ​ጠሩ ሠራ​ተ​ኞች በእ​ር​ስዋ ተቀ​ል​በው እንደ ሰቡ ወይ​ፈ​ኖች ናቸው፤ የጥ​ፋ​ታ​ቸው ቀንና የቅ​ጣ​ታ​ቸው ጊዜ መጥ​ቶ​ባ​ቸ​ዋ​ልና ተመ​ለሱ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ሸሹ፤ አል​ቆ​ሙ​ምም።


“ርስ​ቴን የም​ት​በ​ዘ​ብዙ እና​ንተ ሆይ! ደስ ብሎ​አ​ች​ኋ​ልና፥ ሐሤ​ት​ንም አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና፥ በመ​ስክ ላይም እን​ዳ​ለች ጊደር ሆና​ችሁ ተቀ​ና​ጥ​ታ​ች​ኋ​ልና፥ እንደ ብር​ቱ​ዎ​ችም በሬ​ዎች ቷጋ​ላ​ች​ሁና፤


ፍሬ​ዋን ሁሉ አድ​ር​ቁ​ባት፤ ወደ መታ​ረ​ድም ይው​ረዱ፤ ቀና​ቸው ደር​ሳ​ለ​ችና፥ እነ​ሱን የሚ​በ​ቀ​ሉ​በት ጊዜ ደር​ሷ​ልና ወዮ​ላ​ቸው!


የም​ቷ​ኝ​ባ​ት​ንም ምድር እስከ ተረ​ራ​ሮች ድረስ በደ​ምህ አጠ​ጣ​ለሁ፤ መስ​ኖ​ዎ​ችም ከአ​ንተ ይሞ​ላሉ።


“አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ለሚ​በ​ርሩ ወፎች ሁሉና ለም​ድር አራ​ዊት ሁሉ እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ኑ፤ ተከ​ማቹ፤ ሥጋ​ንም ትበሉ ዘንድ፥ ደም​ንም ትጠጡ ዘንድ በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ላይ ወደ​ማ​ር​ድ​ላ​ችሁ መሥ​ዋ​ዕት፥ እር​ሱም ታላቅ መሥ​ዋ​ዕት፥ ከየ​ሰ​ፍ​ራው ሁሉ ተሰ​ብ​ሰቡ።


የኀ​ያ​ላ​ኑን ሥጋ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ የም​ድ​ር​ንም አለ​ቆች፥ የአ​ውራ ፍየ​ሎ​ች​ንና የአ​ውራ በጎ​ችን፥ የወ​ይ​ፈ​ኖ​ች​ንና፥ የባ​ሳ​ንን ፍሪ​ዳ​ዎች ሁሉ፥ ደም ትጠ​ጣ​ላ​ችሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ ያወ​ጣው እርሱ ጕል​በቱ አንድ ቀንድ እን​ዳ​ለው ክብር ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ መርቶ አው​ጥ​ቶ​ታል፤ አንድ ቀንድ እን​ዳ​ለው ክብር አለው፤ ጠላ​ቶ​ቹን አሕ​ዛ​ብን ይበ​ላል፤ አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይሰ​ባ​ብ​ራል፤ በፍ​ላ​ጾ​ቹም ጠላ​ቱን ይወ​ጋ​ዋል።


ውበቱ እንደ ላም በኵር ነው፤ ቀን​ዶቹ አንድ ቀንድ እን​ዳ​ለው ናቸው፤ በእ​ነ​ርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ያሉ​ትን አሕ​ዛብ ሁሉ ይወ​ጋል፤ የኤ​ፍ​ሬም እልፍ አእ​ላ​ፋት፥ የም​ና​ሴም አእ​ላ​ፋት እነ​ርሱ ናቸው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios