Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 34:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በዚ​ያም አጋ​ን​ን​ትና ጂኖች ይገ​ና​ኛሉ፤ እነ​ር​ሱም እርስ በር​ሳ​ቸው ይጠ​ራ​ራሉ፤ ጂኖ​ችም በዚያ ይኖ​ራሉ፤ ለራ​ሳ​ቸ​ውም ማረ​ፊ​ያን ያገ​ኛሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 የምድረ በዳ አራዊት ከጅቦች ጋራ ዐብረው ይሆናሉ፤ በበረሓ ፍየል የሚመሰሉ አጋንንትም እርስ በእርስ ይጠራራሉ፤ የሌሊት ፍጥረታት ማረፊያቸውን በዚያ ያደርጋሉ፤ ለራሳቸውም የማረፊያ ቦታ ያገኛሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የምድረ በዳም አራዊት ከጅቦች ጋር ይገናኛሉ፤ አጋንንትም እርስ በርሳቸው ይጠራራሉ፤ ጅንም በዚያም ትኖራለች፤ ለእርሷም ማረፊያ ታገኛለች።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 አነሮች ከጅቦች ጋር አብረው ይኖራሉ፤ አጋንንትም እርስ በርሳቸው ይጠራራሉ፤ የሌሊት ምትሐቶች በፍርስራሾች መካከል ይኖራሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የምድረ በዳም አራዊት ከተኵሎች ጋር ይገናኛሉ፥ አጋንንትም እርስ በርሳቸው ይጠራራሉ፥ ጅንም በዚያም ትኖራለች፥ ለእርስዋም ማረፊያ ታገኛለች።

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 34:14
5 Referências Cruzadas  

አሦ​ርም የወ​ፎች መኖ​ሪ​ያና የዘ​ለ​ዓ​ለም ባድማ ትሆ​ና​ለች፤ በዚ​ያም ሰው አይ​ኖ​ርም፤ የሰው ልጅም አይ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም።


ስለ​ዚህ የዱር አራ​ዊት ከተ​ኵ​ላ​ዎች ጋር ይቀ​መ​ጡ​ባ​ታል፤ ሰጎ​ኖ​ችም ይቀ​መ​ጡ​ባ​ታል፤ ሰውም ከዚያ ወዲያ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም፤ እስከ ልጅ ልጅም ድረስ የሚ​ኖ​ር​ባት የለም።


ባቢ​ሎ​ንም ባድ​ማና የቀ​በሮ ማደ​ሪያ፥ ማፍ​ዋ​ጫም ትሆ​ና​ለች፤ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም ሰው አይ​ገ​ኝም።


ተራሮቹንም በረሃ አደረግኋቸው፥ ርስቱንም ለምድረ በዳ ቀበሮች አሳልፌ ሰጠኋቸው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios