Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 33:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ዛሬ ታያ​ላ​ችሁ፤ ዛሬ ታደ​ን​ቃ​ላ​ችሁ፤ የመ​ን​ፈ​ሳ​ች​ሁም ኀይል ከንቱ ይሆ​ናል፤ እሳ​ትም ትበ​ላ​ች​ኋ​ለች።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ገለባን ፀነሳችሁ፤ እብቅንም ወለዳችሁ፤ እስትንፋሳችሁም የሚበላችሁ እሳት ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ገለባን ትጸንሳላችሁ፥ ዕብቅንም ትወልዳላችሁ፤ እስትንፋሳችሁ የምትበላችሁ እሳት ናት።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ገለባን ፀንሳ እብቅ እንደምትወልድ እስትንፋሳችሁ እንደ እሳት ሆኖ ያጋያችኋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ገለባን ትጸንሳላችሁ፥ ዕብቅንም ትወልዳላችሁ፥ እስትንፋሳችሁ የምትበላችሁ እሳት ናት።

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 33:11
20 Referências Cruzadas  

በሆ​ዳ​ቸው ጭን​ቅ​ትን ይፀ​ን​ሳሉ፥ ከንቱ ነገ​ር​ንም ይወ​ል​ዳሉ። ሆዳ​ቸ​ውም ተን​ኰ​ልን ያዘ​ጋ​ጃል።”


አሕ​ዛብ ለምን ዶለቱ? ወገ​ኖ​ችስ ለምን ከንቱ ይና​ገ​ራሉ?


እነሆ፥ ዐመ​ፀኛ በዐ​መፁ ተጨ​ነቀ፤ ጭን​ቅን ፀነሰ፤ ኀጢ​አ​ት​ንም ወለደ።


ጕድ​ጓ​ድ​ንም ማሰ፥ ቈፈ​ረም። ባደ​ረ​ገ​ውም ጕድ​ጓድ ይወ​ድ​ቃል።


ኀይ​ላ​ቸ​ውም እንደ መቃ መስዬ፥ ሥራ​ቸ​ውም እንደ ጠለ​ሸት ይሆ​ናል፤ ኃጥ​አ​ንና ዐማ​ፅ​ያ​ንም አብ​ረው ይቃ​ጠ​ላሉ፤ እሳ​ቱ​ንም የሚ​ያ​ጠ​ፋ​ላ​ቸው ያጣሉ።”


ብዙ​ዎች አሕ​ዛብ እንደ ብዙ ውኃ ናቸው፤ ከፏ​ፏቴ ውስጥ በኀ​ይል እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ እንደ ብዙ ውኃ ፈሳሽ ይጮ​ኻሉ፤ ያጠ​ፉ​ታ​ልም፤ እነ​ር​ሱም ከሩቅ ይወ​ር​ዳሉ፤ በተ​ራ​ራም ላይ እን​ዳለ እብቅ፥ በነ​ፋስ ፊት ዐውሎ ነፋስ እን​ደ​ሚ​ያ​ዞ​ረው እንደ መን​ኰ​ራ​ኵር ትቢ​ያም ይበ​ተ​ናሉ።


አን​ተን በመ​ፍ​ራት አቤቱ፥ እኛ ፀን​ሰ​ናል፤ ምጥም ይዞ​ናል፤ በም​ድ​ርም የማ​ዳ​ን​ህን መን​ፈስ ወለ​ድን፤ በዓ​ለ​ምም የሚ​ኖሩ ይወ​ድ​ቃሉ።


ስለ​ዚህ ገለባ በእ​ሳት ፍም እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠል፥ በነ​በ​ል​ባ​ልም እን​ደ​ሚ​በላ፥ እን​ዲሁ የእ​ነ​ርሱ ሥር የበ​ሰ​በሰ ይሆ​ናል፤ አበ​ባ​ቸ​ውም እንደ ትቢያ ይበ​ን​ናል፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ጥለ​ዋ​ልና፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቅዱስ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል አቃ​ል​ለ​ዋ​ልና።


ጽድ​ቅን የሚ​ና​ገር በእ​ው​ነ​ትም የሚ​ፈ​ርድ የለም፤ በከ​ንቱ ነገር ታም​ነ​ዋል፤ የማ​ይ​ጠ​ቅ​ማ​ቸ​ው​ንም ተና​ግ​ረ​ዋል፤ ኀጢ​አ​ትን ፀን​ሰ​ዋል፤ በደ​ል​ንም ወል​ደ​ዋል።


ሰው ሁሉ ክፉና በደ​ለኛ ነውና፥ አፍም ሁሉ ዐመ​ፅን ይና​ገ​ራ​ልና፥ ስለ​ዚህ ጌታ በጐ​ል​ማ​ሶ​ቻ​ቸው ደስ አይ​ለ​ውም፤ ለሙት ልጆ​ቻ​ቸ​ውና ለመ​በ​ለ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አይ​ራ​ራም። በዚህ ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።


ጥን​ቱን ሳት​ሸ​ጠው ያንተ አል​ነ​በ​ረ​ምን? ከሸ​ጥ​ኸ​ውስ በኋላ በፈ​ቃ​ድህ አል​ነ​በ​ረ​ምን? ይህን ነገር በል​ብህ ለምን ዐሰ​ብህ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንጂ ሰውን አላ​ታ​ለ​ል​ህም” አለው።


ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኀጢአትን ትወልዳለች፤ ኀጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios