Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 30:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 “ከዚህ መን​ገድ መል​ሱን፤ ከዚ​ህም ፈቀቅ አድ​ር​ጉን በሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቅዱስ ትም​ህ​ርት ከእኛ ዘንድ አስ​ወ​ግዱ” ይሏ​ቸ​ዋል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከዚህ መንገድ ፈቀቅ በሉ፤ ከጐዳናውም ራቁ፤ ከእስራኤል ቅዱስ ጋራ ፊት ለፊት አታጋጥሙን!”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ከመንገድ ፈቀቅ በሉ፥ ከጐዳናውም ዘወር በሉ፥ የእስራኤልንም ቅዱስ ከእኛ ዘንድ አስወግዱ” ይሏቸዋል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ከመንገዳችን ወዲያ ዘወር በሉልን፤ ለእርምጃችንም መሰናክል አትሁኑብን፤ እኛ ስለ እስራኤል ቅዱስ ዳግመኛ መስማት አንፈልግም።’ ”

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ከመንገድ ፈቀቅ በሉ፥ ከጐዳናውም ዘወር በሉ፥ የእስራኤልንም ቅዱስ ከእኛ ዘንድ አስወግዱ ይሉአቸዋል።

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 30:11
12 Referências Cruzadas  

የተ​ገ​ዳ​ደ​ር​ኸው፥ የሰ​ደ​ብ​ኸ​ውስ ማን ነው? ቃል​ህ​ንስ ከፍ ከፍ ያደ​ረ​ግ​ኸው፥ ዐይ​ን​ህ​ንም ወደ ላይ ያነ​ሣ​ኸው በማን ላይ ነው? በእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ላይ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፦ እን​ዲህ ይሉ​ታል፦ ከእኛ ዘንድ ራቅ፤ መን​ገ​ድ​ህ​ንም እና​ውቅ ዘንድ አን​ወ​ድ​ድም።


ጌታም አለ፥ “ይህ ሕዝብ በከ​ን​ፈ​ሮቹ ያከ​ብ​ረ​ኛ​ልና፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነውና፥ በከ​ንቱ ያመ​ል​ኩ​ኛል፤ ሰው ሠራሽ ትም​ህ​ር​ትም ያስ​ተ​ም​ራሉ፤


እነ​ዚ​ህም ሰውን በነ​ገር በደ​ለኛ የሚ​ያ​ደ​ርጉ፥ በበ​ርም ለሚ​ገ​ሥ​ጸው አሽ​ክላ የሚ​ያ​ኖሩ፥ ጻድ​ቁ​ንም በከ​ንቱ ነገር የሚ​ያ​ስቱ ናቸው።


ነገር ግን ቤቴል የን​ጉሥ መቅ​ደ​ስና የመ​ን​ግ​ሥት ቤት ናትና ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በዚህ ደግሞ ትን​ቢት አት​ና​ገር” አለው።


ነፋስንም ተከትሎ፦ ስለ ወይን ጠጅና ስለ ስካር ትንቢት እናገርልሃለሁ ብሎ ሐሰትን የሚናገር ሰው ቢኖር እርሱ ለዚህ ሕዝብ ነቢይ ይሆናል።


አስ​ማ​ተ​ኛው ኤል​ማ​ስም የስሙ ትር​ጓሜ እን​ዲህ ነበ​ረና፥ ገዥ​ውን ከማ​መን ሊከ​ለ​ክ​ለው ፈልጎ ተቃ​ወ​ማ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​ወቅ ባል​ወ​ደዱ መጠን እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን የማ​ይ​ገ​ባ​ውን ይሠሩ ዘንድ ሰነፍ አእ​ም​ሮን ሰጣ​ቸው።


ሐሜ​ተ​ኞች፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ጠሉ፥ ተሳ​ዳ​ቢ​ዎች፥ ትዕ​ቢ​ተ​ኞች፥ ትም​ክ​ሕ​ተ​ኞች፥ ክፋ​ትን የሚ​ፈ​ላ​ለጉ፥ ለወ​ላ​ጆ​ቻ​ቸ​ውም የማ​ይ​ታ​ዘዙ ናቸው።


የሥጋ ዐሳብ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላቱ ነውና፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ ስለ​ማ​ይ​ገዛ፥ መፈ​ጸም አይ​ቻ​ለ​ውም።


ልቡ​ና​ቸው የተ​ጨ​ፈነ ነው፤ በስ​ን​ፍ​ና​ቸ​ውና በድ​ን​ቍ​ር​ና​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ሰ​ጣ​ቸው ሕይ​ወት የተ​ለዩ ናቸው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios