Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 29:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ነገ​ር​ሽም በም​ድር ውስጥ ይሰ​ጥ​ማል፤ ቃል​ሽም ከም​ድር በታች እን​ደ​ሚ​ና​ገር ይሆ​ናል፤ ትደ​ክ​ሚ​ያ​ለሽ፤ ቃል​ሽም በም​ድር ውስጥ ዝቅ ይላል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ወደ ታች ትወርጃለሽ፤ ከምድርም በታች ትናገሪያለሽ፤ ንግግርሽ ከትቢያ እየተጕተመተመ ይወጣል፤ ድምፅሽ እንደ መናፍስት ድምፅ ከመሬት ወደ ላይ ይመጣል፤ ንግግርሽ ከትቢያ ያንሾካሹካል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ትዋረጃለሽ፥ መሬት ላይ ተደፍተሽ ትናገሪያለሽ፥ ቃልሽም በዝግታ ከአፈር ይወጣል፤ ድምጽሽም ከመሬት እንደሚወጣ እንደ መናፍስት ድምፅ ይሆናል፥ ንግግርሽም ከአፈር በሹክሹክታ ይወጣል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ካለችበት ከጥልቁ ጒድጓድ ትናገራለች፤ ከታች ከትቢያ ውስጥ ንግግርዋ ይመጣል፤ ድምፅዋም እንደ ምትሐት ከምድረ በዳ ይወጣል፤ ከአዋራ ውስጥም ዝቅ ያለ ድምፅዋ ይሰማል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ትዋረጅማለሽ፥ በመሬትም ላይ ሆነሽ ትናገሪያለሽ፥ ቃልሽም ዝቅ ብሎ ከአፈር ይወጣል፥ ድምጽሽም ከመሬት እንደሚወጣ እንደ መንፍስት ጠሪ ድምፅ ይሆናል፥ ቃልሽም ከአፈር ወጥቶ ይጮኸል።

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 29:4
8 Referências Cruzadas  

ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተፈ​ት​ታ​ለ​ችና፥ ይሁ​ዳም ወድ​ቃ​ለ​ችና፥ አን​ደ​በ​ታ​ቸ​ውም ዐመ​ፅን ስለ​ሚ​ና​ገር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ታ​ዘ​ዙም።


በረዶ ቢወ​ርድ አይ​ደ​ር​ስ​ባ​ች​ሁም፤ በዛፍ ሥር የሚ​ኖሩ ሰዎች በበ​ረሃ እን​ደ​ሚ​ኖሩ ሰዎች ታም​ነው ይኖ​ራሉ።


ወደ በደ​ሉ​ሽና ወደ አጐ​ሰ​ቈ​ሉሽ ሰዎች እጅ፥ ሰው​ነ​ት​ሽ​ንም ዝቅ በዪ፥ ድል​ድይ አድ​ር​ገን እን​ሻ​ገ​ር​ብሽ ወደ​ሚ​ሏት ሰዎች እጅ እመ​ል​ሰ​ዋ​ለሁ።” በም​ድ​ርም ላይ በሆ​ድሽ አስ​ተ​ኙሽ፤ መን​ገ​ደ​ኞ​ችም ሁሉ ረገ​ጡሽ።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ትቢ​ያን አራ​ግፊ፤ ተነሺ፥ ተቀ​መጪ፤ ምር​ኮ​ኛ​ዪቱ የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ የአ​ን​ገ​ት​ሽን እስ​ራት ፍቺ።


እነ​ር​ሱም፥ “ድም​ፃ​ቸ​ውን ዝቅ አድ​ር​ገው የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ችን ጠይቁ” ባሉ​አ​ችሁ ጊዜ፥ ሕዝቡ ከአ​ም​ላኩ መጠ​የቅ አይ​ገ​ባ​ው​ምን? ወይስ ለሕ​ያ​ዋን ሲሉ ሙታ​ንን ይጠ​ይ​ቃ​ሉን?


ጤት። ግዳ​ጅዋ ከእ​ግ​ርዋ በታች ነበረ፤ ፍጻ​ሜ​ዋን አላ​ሰ​በ​ችም፤ ከባድ ሸክ​ምን ተሸ​ከ​መች፤ የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ትም የለም፤ አቤቱ! ጠላት ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና መከ​ራ​ዬን ተመ​ል​ከት።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios