Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 26:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የፀ​ነ​ሰች ሴት ለመ​ው​ለድ ስት​ቀ​ርብ እን​ደ​ም​ት​ጨ​ነ​ቅና በምጥ እን​ደ​ም​ት​ጮህ፥ አቤቱ፥ እን​ዲሁ በፊ​ትህ ለወ​ዳ​ጅህ ሆነ​ናል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እግዚአብሔር ሆይ፤ የፀነሰች ሴት ልትወልድ ስትል፣ በምጥ እንደምትጨነቅና እንደምትጮኽ፣ እኛም በፊትህ እንዲሁ ሆነናል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የፀነሰች ሴት ለመውለድ ስትቀርብ እንደምትጨነቅና በምጥ አንደምትጮኽ፥ አቤቱ ጌታ፥ በፊትህ እንዲሁ ሆነናል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 አምላክ ሆይ! ምጥ የያዛት ሴት በሕመሙ ተጨንቃ እንደምትጮኽ፥ እኛም በፊትህ እንዲሁ ሆነናል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የፀነሰች ሴት ለመውለድ ስትቀርብ እንደምትጨነቅና በምጥ አንደምትጮኽ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ በፊትህ ሆነናል።

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 26:17
11 Referências Cruzadas  

ለሴ​ቲ​ቱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አላት፥ “ጭን​ቅ​ሽን እጅግ አበ​ዛ​ለሁ፤ በጭ​ንቅ ትወ​ል​ጃ​ለሽ፤ ከወ​ለ​ድ​ሽም በኋላ ፈቃ​ድሽ ወደ ባልሽ ይሆ​ናል፤ እር​ሱም ይገ​ዛ​ሻል።”


በኀ​ይ​ላ​ቸው የሚ​ታ​መኑ፥ በባ​ለ​ጠ​ግ​ነ​ታ​ቸ​ውም ብዛት የሚ​ኮሩ፤


ሽማ​ግ​ሎች ይደ​ነ​ግ​ጣሉ፤ እን​ደ​ም​ት​ወ​ልድ ሴትም ምጥ ይይ​ዛ​ቸ​ዋል፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ይገ​ዳ​ደ​ላሉ፤ ይደ​ነ​ቃሉ፤ ፊታ​ቸ​ውም እንደ እሳት ይን​በ​ለ​በ​ላል።


ስለ​ዚ​ህም ወገቤ ሕማም ተሞላ፤ እን​ደ​ም​ት​ወ​ልድ ሴትም ምጥ ያዘኝ፤ ከሕ​ማሜ የተ​ነሣ አል​ሰ​ማም፤ ከድ​ን​ጋ​ጤም የተ​ነሣ አላ​ይም።


እነ​ር​ሱም፥ “ሕዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ይላል፦ ይህ ቀን የመ​ከ​ራና የተ​ግ​ሣጽ፥ የዘ​ለ​ፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚ​ወ​ለ​ዱ​በት ጊዜ ደር​ሶ​አል፤ ለመ​ው​ለ​ድም ኀይል የለም።


ጠይቁ፤ ወንድ ይወ​ልድ እንደ ሆነ ተመ​ል​ከቱ፤ ስለ ምን ሰው ሁሉ እንደ ወላድ እጁን በወ​ገቡ ላይ አድ​ርጎ፥ ፊቱም ሁሉ ወደ ጥቍ​ረት ተለ​ውጦ አየሁ?


እን​ደ​ም​ታ​ምጥ፥ የበ​ኵር ልጅ​ዋ​ንም እን​ደ​ም​ት​ወ​ልድ ሴት ጩኸት፥ ጩኸ​ት​ሽን ሰም​ቻ​ለ​ሁና፤ የጽ​ዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድ​ካም ሰለለ፤ እጆ​ች​ዋ​ንም ትዘ​ረ​ጋ​ለች፤ ተገ​ድ​ለው ከሞ​ቱት የተ​ነሣ ነፍሴ ዝላ​ለ​ችና ወዮ​ልኝ! አለች።


ጩኸ​ታ​ቸ​ውን ሰም​ተን፥ እጃ​ችን ደክ​ማ​ለች፤ ወላ​ድን ሴት ምጥ እን​ደ​ሚ​ይ​ዛት ጭን​ቀት ይዞ​ናል።


ሴት በም​ት​ወ​ል​ድ​በት ጊዜ ወራቷ ስለ ደረሰ ታዝ​ና​ለች፤ ነገር ግን ልጅ​ዋን ከወ​ለ​ደች በኋላ ስለ ደስ​ታዋ ከዚያ ወዲያ ምጥ​ዋን አታ​ስ​በ​ውም፤ በዓ​ለም ወንድ ልጅን ወል​ዳ​ለ​ችና።


ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ያን ጊዜ ምጥ እርጕዝን እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ከቶም አያመልጡም።


እርስዋም ፀንሳ ነበር፤ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጭንቃ ጮኸች።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios