Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 25:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሕ​ዝቡ ሁሉ ግብ​ዣን ያደ​ር​ጋል፤ በዚህ ተራራ ላይ ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋሉ፤ የወ​ይን ጠጅ​ንም ይጠ​ጣሉ፤ ዘይ​ት​ንም ይቀ​ባሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በዚህ ተራራ ላይ፣ ለሕዝብ ሁሉ ታላቅ የምግብ ግብዣ፣ የበሰለ የወይን ጠጅ ድግስ፣ ማለፊያ ጮማና ምርጥ የወይን ጠጅ ያዘጋጃል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የሠራዊት ጌታም ለሕዝብ ሁሉ በዚህ ተራራ ላይ ታላቅ የሰባ ግብዣ፥ ያረጀ የወይን ጠጅ፥ ቅልጥም የሞላባቸው የሰቡ ነገሮች፥ መልካምና የበሰለ የወይን ጠጅ ግብዣ ያደርጋል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የሠራዊት አምላክ በዚህች በጽዮን ተራራ ለዓለም ሕዝቦች ሁሉ ታላቅ ግብዣ ያዘጋጃል፤ በግብዣውም ላይ ምርጥ የወይን ጠጅና፥ የተሟላ ምግብ ይዘጋጃል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ለሕዝብ ሁሉ በዚህ ተራራ ላይ ታላቅ የሰባ ግብዣ፥ ያረጀ የወይን ጠጅ፥ ቅልጥም የሞላባቸው የሰቡ ነገሮች፥ የጥሩና ያረጀ የወይን ጠጅ ግብዣ ያደርጋል።

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 25:6
30 Referências Cruzadas  

መዓ​ትን ተዋት፤ ቍጣ​ንም ጣላት፥ እን​ዳ​ት​በ​ድ​ልም አት​ቅና።


ለእ​ነ​ርሱ ለራ​ሳ​ቸው ክፉ ነገ​ርን አጸኑ፤ ወጥ​መ​ድን ይሰ​ውሩ ዘንድ ተማ​ከሩ፤ የሚ​ያ​ም​ንም የለም ይላሉ።


በአፉ አሳ​ሳም ይስ​መ​ኛል፥ ጡቶ​ችሽ ከወ​ይን ይልቅ ያማሩ ናቸው።


ከወደ ኋላ​ህም ሳቡህ፥ በሽ​ቱህ መዓ​ዛም እን​ሮ​ጣ​ለን፤ ንጉሡ ወደ እል​ፍኙ አገ​ባኝ፤ በአ​ንቺ ደስ ይለ​ኛል፥ ሐሤ​ትም እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ ከወ​ይን ጠጅ ይልቅ ጡቶ​ች​ሽን እን​ወ​ዳ​ለን፤ አን​ቺ​ንም መው​ደድ የተ​ገባ ነው።


እኅቴ ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ወደ ገነቴ ገባሁ፥ ከር​ቤ​ዬን ከሽ​ቱዬ ጋር ለቀ​ምሁ፥ እን​ጀ​ራ​ዬን ከማሬ ጋር በላሁ፥ የወ​ይን ጠጄን ከወ​ተቴ ጋር ጠጣሁ። ባል​ን​ጀ​ሮች በሉ፥ ጠገ​ቡም፤ የወ​ን​ድ​ሞች ልጆች ጠጡ፥ ሰከ​ሩም፥ ልባ​ቸው የጠፋ ነውና።


እሽ ብት​ሉና ብት​ሰ​ሙኝ የም​ድ​ርን በረ​ከት ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ተራራ ላይ ዕረ​ፍ​ትን ይሰ​ጠ​ናል፤ እህ​ልም በመ​ን​ኰ​ራ​ኵር ጭድም በጭቃ እን​ደ​ሚ​በ​ራይ እን​ዲሁ ሞዓብ ይረ​ገ​ጣል።


ወደ ተቀ​ደሰ ተራ​ራዬ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በጸ​ሎ​ቴም ቤት ደስ አሰ​ኛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቤቴ ለአ​ሕ​ዛብ ሁሉ የሚ​ሆን የጸ​ሎት ቤት ይባ​ላ​ልና፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውና ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም በመ​ሠ​ዊ​ያዬ ላይ የተ​መ​ረጠ ይሆ​ናል።


“ሞአብ ከል​ጅ​ነቷ ጀምራ ዐረ​ፈች፤ በክ​ብ​ር​ዋም ቅም​ጥል ነበ​ረች፤ ወይ​ን​ዋም ከዕቃ ወደ ዕቃ አል​ተ​ገ​ላ​በ​ጠም፤ ወደ ምር​ኮም አል​ሄ​ደ​ችም፤ ስለ​ዚህ ቃናው በእ​ር​ስዋ ውስጥ ቀር​ቶ​አል፤ መዓ​ዛ​ዋም አል​ተ​ለ​ወ​ጠም።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ጽዮን ተመልሻለሁ፥ በኢየሩሳሌምም መካከል እኖራለሁ፣ ኢየሩሳሌምም የእውነት ከተማ ትባላለች፣ የሠራዊትም ጌታ የእግዚአብሔር ተራራ የተቀደሰ ተራራ ይባላል።


ነገር ግን እላችኋለሁ፤ በአባቴ መንግሥት ከእናንተ ጋር ከዚህ ከወይን ፍሬ አዲሱን እስከምጠጣበት እስከዚያ ቀን ድረስ ከዛሬ ጀምሬ አልጠጣም።”


እላችኋለሁም፥ ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ፤ ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር በመንግሥተ ሰማያት ይቀመጣሉ፤


እንዲህም አላቸው “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።


በመ​ን​ግ​ሥቴ በማ​ዕዴ ትበ​ሉና ትጠጡ ዘንድ፥ በወ​ን​በ​ሮ​ችም ተቀ​ም​ጣ​ችሁ በዐ​ሥራ ሁለቱ ነገደ እስ​ራ​ኤል ትፈ​ርዱ ዘንድ።”


የከ​ረ​መ​ውን የወ​ይን ጠጅ ሊጠጣ ወድዶ አዲ​ሱን የሚሻ የለም፤ የከ​ረ​መው ይሻ​ላል ይላ​ልና።”


እና​ንተ ግን፥ የሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተማ ወደ​ም​ት​ሆን ወደ ጽዮን ተራራ፥ በሰ​ማ​ያት ወደ አለ​ችው ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ደስ ብሎ​አ​ቸው ወደ​ሚ​ኖሩ አእ​ላፍ መላ​እ​ክ​ትም ደር​ሳ​ች​ኋል።


መልአኩም “ወደ በጉ ሰርግ እራት የተጠሩ ብፁዓን ናቸው፤” ብለህ ጻፍ፤ አለኝ። ደግሞም “ይህ የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃል ነው፤” አለኝ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios