Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 23:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በጢ​ሮስ ላይ ይህን የመ​ከረ ማን ነው? እር​ስዋ ከሁሉ የም​ት​ሻ​ልና የም​ት​በ​ልጥ አይ​ደ​ለ​ች​ምን? ነጋ​ዴ​ዎ​ችዋ የከ​በሩ የም​ድር አለ​ቆች ናቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 አክሊል በምታቀዳጀዋ፣ ነጋዴዎቿ መሳፍንት በሆኑ፣ በምድር የከበሩ ሻጮችና ለዋጮች በነበሯት፣ በጢሮስ ላይ ይህን ያሰበ ማን ነበር?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አክሊል በተቀዳጀች፥ ነጋዴዎችዋ መሳፍንት በሆኑ፥ በምድር የከበሩ ሻጮችና ለዋጮች በነበሯት፥ በጢሮስ ላይ ይህን ያሰበ ማን ነበር?

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ዘውድን ታቀዳጅ በነበረችው ከተማ፥ ልዑላን የሆኑና በዓለም የተከበሩ ነጋዴዎች በነበርዋት በጢሮስ ላይ ይህን ሁሉ ያቀደ ማነው?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 አክሊል ባስጫነች ከተማ በጢሮስ ላይ ይህን የወሰነ ማን ነው? ነጋዴዎችዋ አለቆች ናቸው፥ በእርስዋ የሚሸጡና የሚለወጡ የምድር ክቡራን ናቸው።

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 23:8
11 Referências Cruzadas  

“አንተ ብቻ​ህን አለቃ ነህን?” ቢሉ​ትም፥ የሔ​ማ​ትን መን​ደር ወሰ​ድሁ ይላል።


ከታ​ና​ና​ሾቹ ከጌ​ታዬ አገ​ል​ጋ​ዮች የሚ​ያ​ን​ሰ​ውን የአ​ን​ዱን ጭፍራ ፊት መመ​ለስ እን​ዴት ትች​ላ​ለህ? ስለ ሰረ​ገ​ሎ​ችና ፈረ​ሰ​ኞች በግ​ብፅ የሚ​ታ​መኑ ለጌ​ታዬ ባሮች ናቸው።


ገን​ዘ​ብ​ሽን ይበ​ረ​ብ​ራሉ፤ መን​ጋ​ሽ​ንም ይዘ​ር​ፋሉ፤ አም​ባ​ሽ​ንም ይን​ዳሉ፤ የተ​ወ​ደዱ ቤቶ​ች​ሽ​ንም ያፈ​ር​ሳሉ፤ እን​ጨ​ቶ​ች​ሽ​ንና ድን​ጋ​ይ​ሽን፥ መሬ​ት​ሽ​ንም በባ​ሕሩ ጥልቅ ውስጥ ይጥ​ሉ​ታል።


ነጋዴዎችሽን ከሰማይ ከዋክብት ይልቅ አበዛሽ፣ ደጎብያ ተዘረጋ፥ በረረም።


ጢሮስም ምሽግን ለራስዋ ሠርታለች፥ ብሩንም እንደ አፈር ጥሩውንም ወርቅ እንደ መንገድ ጭቃ አከማችታለች።


የመብራትም ብርሃን ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይበራም፤ የሙሽራና የሙሽራይቱም ድምጽ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የምድር መኳንንት ነበሩና፤ በአስማትሽም አሕዛብ ሁሉ ስተዋልና።”


ስለዚህ በአንድ ቀን ሞትና ሐዘን ራብም የሆኑ መቅሰፍቶችዋ ይመጣሉ፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios