Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




ኢሳይያስ 2:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምድ​ርን ያና​ውጥ ዘንድ በተ​ነሣ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ፍ​ራ​ትና ከግ​ር​ማው ክብር የተ​ነሣ ወደ ድን​ጋይ ዋሻና ወደ ተሰ​ነ​ጠቁ ዓለ​ቶች ውስጥ ያገ​ባሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እግዚአብሔር ምድርን ለማናወጥ በሚነሣበት ጊዜ፣ ሰዎች ከአስፈሪነቱ እንዲሁም ከግርማው የተነሣ፣ ወደ ድንጋይ ዋሻ፣ ወደ ዐለት ስንጣቂ ሮጠው ይገባሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ጌታ ምድርን ለማናወጥ በሚነሣበት ጊዜ፤ ሰዎች ከአስፈሪነቱ እንዲሁም ከግርማው የተነሣ፤ ወደ ድንጋይ ዋሻ፤ ወደ ዐለት ስንጣቂ ሮጠው ይገባሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እግዚአብሔር ምድርን ለማናወጥ በሚመጣበት ጊዜ ከቊጣውና ከአስፈሪ ግርማው ተሰውረው ለማምለጥ በድንጋይ ዋሻና በተሰነጠቀ አለት ውስጥ ይሸሸጋሉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ ከማስደንገጡና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻና ወደ ተሰነጠቁ ዓለቶች ውስጥ ይገባሉ።

Ver Capítulo Cópia de




ኢሳይያስ 2:21
12 Referências Cruzadas  

የባ​ዕድ ልጆች አረጁ፤ ከማ​ን​ከ​ሳ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ተሰ​ና​ከሉ።


በሸ​ለ​ቆው ፈረ​ፈ​ርና በም​ድር ጕድ​ጓድ ውስጥ በዓ​ለ​ትም ዋሻ ውስጥ ይኖ​ራሉ፤


ምድ​ርን ከሰ​ማይ በታች ከመ​ሠ​ረቷ ያና​ው​ጣ​ታል፥ ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ዋም ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ።


ክብ​ሬም በአ​ለፈ ጊዜ በአ​ለቱ ስን​ጥቅ ውስጥ አኖ​ር​ሃ​ለሁ፤


ፊት​ህን አሳ​የኝ፥ ቃል​ህ​ንም አሰ​ማኝ፤ ቃልህ ያማረ፥ ፊት​ህም የተ​ዋበ ነውና።


አሁ​ንም ምድ​ርን ያነ​ዋ​ው​ጣት ዘንድ በተ​ነሣ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ፍ​ራ​ትና ከግ​ር​ማው ክብር የተ​ነሣ ወደ ድን​ጋይ ዋሻ ግቡ፤ በመ​ሬት ውስ​ጥም ተሸ​ሸጉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምድ​ርን ያና​ውጥ ዘንድ በተ​ነሣ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ፍ​ራ​ትና ከግ​ር​ማው ክብር የተ​ነሣ ወደ ድን​ጋይ ዋሻና ወደ ምድር ንቃ​ቃት ውስጥ ያገ​ቡ​አ​ቸ​ዋል።


የሰ​ማይ መስ​ኮ​ቶ​ችም ተከ​ፍ​ተ​ዋ​ልና፥ የም​ድ​ርም መሠ​ረት ተና​ው​ጣ​ለ​ችና ከፍ​ር​ሀት ድምፅ የሸሸ በገ​ደል ይወ​ድ​ቃል፤ ከገ​ደ​ልም የወጣ በወ​ጥ​መድ ይያ​ዛል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “አሁን እነ​ሣ​ለሁ፤ አሁን እከ​ብ​ራ​ለሁ፤ አሁን ከፍ ከፍ እላ​ለሁ።


ይመ​ጡ​ማል፤ እነ​ር​ሱም ሁሉ በሸ​ለቆ፥ በመ​ን​ደ​ሮች፥ በም​ድር ጕድ​ጓድ፥ በድ​ን​ጋ​ይም ዋሻ ውስጥ በጫካ ሁሉ ላይ ይሰ​ፍ​ራሉ።


“እነሆ፥ ብዙ ዓሣ አጥ​ማ​ጆ​ችን እል​ካ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ር​ሱም ያጠ​ም​ዱ​አ​ቸ​ዋል፤ ከዚ​ያም በኋላ ብዙ አድ​ዳ​ኞ​ችን እል​ካ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ከየ​ተ​ራ​ራ​ውና ከየ​ኮ​ረ​ብ​ታው ሁሉ ከየ​ድ​ን​ጋ​ዩም ስን​ጣቂ ውስጥ ያድ​ድ​ኑ​አ​ቸ​ዋል።


የእ​ስ​ራ​ኤል ኀጢ​አት የሆ​ኑት የአ​ዎን የኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች ይፈ​ር​ሳሉ፤ እሾ​ህና አሜ​ከ​ላም በመ​ሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቻ​ቸው ላይ ይበ​ቅ​ላሉ፤ ተራ​ሮ​ች​ንም፥ “ክደ​ኑን፤ ኮረ​ብ​ቶ​ች​ንም፦ ውደ​ቁ​ብን” ይሉ​አ​ቸ​ዋል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios